አምልኮ/Worship

ደስ ያለው ይዘምር ወይስ ካሴት ያውጣ?

ይሄ ጽሁፍ በጳውሎስ በፈቃዱ የተጻፈ ነው። በጸሃፊው ፈቃድ በደ ቀመዝሙር ብሎግ ላይ ቀርቧል።
ከጳውሎስ ፈቃዱ

guitar3-642x336ከሁለት ዘማሪዎች ጋር ወደ አዋሳ እየሄድኩ ነው (በእናታችሁ ሥማቸውን አትጠይቁኝ)። እዚያ ስንደርስ ሌላ ሦስተኛ ዘማሪ አገኘን። ይህ ዘማሪ ከእኔ ጋር ካሉ ዘማሪዎች ለአንዱ የሚሆን መዝሙር አዘጋጅቷል። ግጥሙን ካስጻፋቸው በኋላ ዜማውን ለማስለመድ ሲጀምረው ቁጭ ዘፈን ይመስላል። አብረውኝ የነበሩ ዘማሪዎችም ይህንን አውቀዋል። “ይህማ የእገሌን ዘፈን ይመስላል” አለ አንደኛው የዘፋኙን ስም ጠቅሶ። ያኛውም ለማስተባበል አልሞከረም። “አዎ ከዚህኛው ዘፈኑ ላይ ነው የወሰድኩት” በማለት ዘፈኑን ማንጎራጎር ጀመረ። ከእኔ ጋር ከሄዱት ዘማሪዎች አንዱ ቀጠል አድርጎ “እኔም እኮ ከዚያኛው ዘፈኑ ላይ ወስጃለሁ” በማለት የሆነ መዝሙር በፉጨት አሰማን። እኔ በድንጋጤ እንደ ጅብራ ከተገተርኩበት ስፍራ በዕፍረት ጉንዳን አክያለሁ ሆኖም ከምንም አልቆጠሩኝም። ዘማሪዎቻችን ግጥም እነ ኤፍሬም ታምሩ ደግሞ ዜማ በመስጠት እንደሚያገለግሉን ግን ከዚያን ቀን ጀምሮ ማወቅ ችያለሁ።

አሁን አሁንማ በአንድ የመዝሙር ካሴት ላይ ሰባትና ስምንት የዘፈን ዜማዎችን ወደ መስማት «አድገናል»።

ይህ ከሆነ ስድስት ዓመት አልፎታል። እኔም ብዙዎቹን ዘማሪዎች ለማናገርና ለመምከር ሞክሬያለሁ። ግና ጥቂት የማይባሉ ዘማሪዎች ከዚህ ዓመላቸው ፍቀቅ ማለት አልሆነላቸውም። አሁን አሁንማ በአንድ የመዝሙር ካሴት ላይ ሰባትና ስምንት የዘፈን ዜማዎችን ወደ መስማት «አድገናል»። ለመገሠጽ ሲሞከርም “በመዝሙሮቹ ተባርከንባቸዋል ለምን ትነኳቸዋላችሁ?” በማለት የሚቆጡ ከየአካባቢው ብቅ ይላሉ። የእነሱን የ«ተባርኬያለሁ» ስሜት የትክክለኛ መለኪይ ያደረገው ማን ነው? የአንድ ሰው ስም ከተጠቀሰም «ያጠፋው እሱ ብቻ አይደለም ስለዚህ እርሱ ተለይቶ ለምን ይወቀሳል?» የሚል አመክንዮታዊነት የጎደለው ተቃውሞ ይደመጣል። ኧረ ለመሆኑ ይህ ሁሉ ጥፋት ሲፈጸም የት ነበሩ? ምናልባት በእንቁላሉ ሥርቆት ጊዜ ማጨብጨባቸውን አቁመው ቢገሥጿቸው ኖሮ ከብዙ ዕፍረት ባተረፉን ነበር!

ይህንን ሁሉ የማቀርበው ግን ጠላቶቼን የማብዛትና እንጀራዬን የማጥፋት ሞኝነት ይዞኝ ወይም ብሽሽቅ አምሮኝ አይደለም። ትውልዱን የማቅናት የባለአደራነት ድርሻዬን ለመወጣት በማሰብ ብቻ ነው።

ሆን ብለው ከዘፈን ዜማ የሚወስዱ ዘማሪወችን አውቃለሁ። ጥቂቶችንም አነጋግሬአለሁ። “ዜማ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው ለሰይጣን ማን ሰጠው? ስለዚህ እንደ ፈለግን መውሰድ እንችላለን” ይላሉ። በዚሁ ከቀጠሉ በዜማ ስርቆት ተከሠው አንድ ቀን ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ እሰጋለሁ። «የዘፈን ዜማ ስንጠቀም የማያውቀውን መልእክት በሚያውቀው ዜማ ለሰይጣን እያቀረብንለት ነው» የሚሉም አሉ («ወደው አይሥቁ!» ይላል ያገሬ ሰው)። በእነርሱ ቤት ሰይጣን እንደ ሕንድ ፊልም «የሌቦች አለቃ» መሆኑ ነው። እንዲህ ከተቻለማ መዝሙር እንዲሆኑልን የምንፈልጋቸው ብዙ «ምርጥ ምርጥ» ዘፈኖች ስላሉ ከሆነ አይቀር አንደኛውኑ ጥቆማ ብንጀምር ይሻለናል። እኔ በበኩሌ «የነገን ማወቅ ፈለግሁ» የሚለውን ዘፈን መርጫለሁ።

«የዘፈን ዜማ ስንጠቀም የማያውቀውን መልእክት በሚያውቀው ዜማ ለሰይጣን እያቀረብንለት ነው» የሚሉም አሉ («ወደው አይሥቁ!» ይላል ያገሬ ሰው)። በእነርሱ ቤት ሰይጣን እንደ ሕንድ ፊልም «የሌቦች አለቃ» መሆኑ ነው።

ዜማ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው እንዴ? ክርክሩ ውሃ አያነሣም። ከቴአትር ቤትና ከዘፈኑ ዓለም አካባቢ የመጡ ሰዎችም ይህን አይነግሩንም። አንዳንዶቹ የዘፈን ዜማዎች ጫት በመቃም ሌሎቹ ደግሞ ሰይጣንን በመለማመን የሚደረሱ ናቸው። በርካቶቹ ዘፋኞች ውሎአቸው ጠንቋይ ቤት እንደ ሆነ በቅርቡ በኢትዮጵያ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲገለጽ ከነበረው የአንድ ጠንቋይ ገድል ተረድተናል።ከዘፈን ደራሲዎች መካከል አንደኛው ሲጸለይበት በውስጡ የነበረው ርኩስ መንፈስ «ዜማና ግጥም የምንሰጠው እኛ ነን» ይል ነበር። «ሳብ በለው የሃሙስ ፈረስ» የሚል ዘፈን አለ አይደል? «የሀሙስ ፈረስ» ማን ይመስላችኋል? «የበረሀው ዐውሎ ነፋስ» የሚል ዘፈንም አለ። ይሄስ ማነው? ነውር የሚተላለፍባቸው አሳፋሪ ዘፈኖች ከመብዛታቸው የተነሣ «በስምንተኛው ሺህ ዘፋኝ ይበዛል’ የሚል ንግርት አለ» እያሉ የሚያሾፉ የትምህርት ቤት ጓደኞች አሉኝ። እውን ዜማ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነውን?

ለመሆኑ የዘፈን ዜማ መዋስ የደረሱት አዲስ ዜማ መፍጠር አቅቷቸው ነው ወይ? መጽሐፍ ቅዱስም ቢሆን “ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ ዘምሩ” (መዝ 96:1 ፣ 40:3 -አ.ም.ት) በማለት በግልጽ ይናገራል። መንፈስ ቅዱስን የት አድርገነው ነው? ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነው እግዚአብሔር ብንጠይቀው በልግስና የማይሰጠን ይመስል ቅልውጥና ምን ወሰደን?
በፊት የመዝሙር ዜማ የሚወስዱ ዘፋኞች ነበር የሚበዙት ምክንያቱም መዝሙሮቻችን በዘፋኞች ዘንድ ተሰሚነት ነበራቸው። አሁን ደግሞ በዚያው መጠን የእነርሱ ዘፈን የእኛን ዘማሪዎች ቀልብ ሰርቋል። ይህም የእኛ ዘማሪዎች የዘፈንን ዜማ በመስረቅ መታማት እንዲጀምሩ አደረገ።

በፊት የመዝሙር ዜማ የሚወስዱ ዘፋኞች ነበር የሚበዙት ምክንያቱም መዝሙሮቻችን በዘፋኞች ዘንድ ተሰሚነት ነበራቸው። አሁን ደግሞ በዚያው መጠን የእነርሱ ዘፈን የእኛን ዘማሪዎች ቀልብ ሰርቋል። ይህም የእኛ ዘማሪዎች የዘፈንን ዜማ በመስረቅ መታማት እንዲጀምሩ አደረገ።

ዘፈን በመዝሙር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከልክ እያለፈ ነው። ቴዲ አፍሮ የተነሣውን ዓይነት ፎቶ ተነስቶ ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ፖስተር የሚያዘጋጅ ዘማሪ በቅርቡ ዓይተናል። በነገር ሁሉ እሱን መምሰል የሚያምራቸው የእርሱ ደቀ መዛሙርት ከመካከላችን ብቅ ማለት ጀምረዋል። አኮራረጃቸው፣ ስም ሳይቀር እንደሚገለብጥ ቀሽም ኮራጅ ተማሪ ነው። አንዳንድ ዘፋኖች መሃል ዘፋኞች የማቃሰት ድምፅ መቀላቀል ይወዳሉ። መልእክቱ ሰዎችን ለአልጋላይ ጨዋታ ለማነሣሣት ወይም እዚያ ላይ ያሉ ለማስመሰል እንደሚደረግ እገምታለሁ። አስገራሚው ግን አንዳንድ መዝሙሮችም መሃል የሚያቃስቱ ዘማሪዎችን እየሰማን መሆኑ ነው። ምን ማለት እንደሆነ አስተውለውት ይሆን? እንደ ዘፈን “የታለ እጃችሁ? እስቲ ሞቅ አድርጉት ባካችሁ?” የሚሉ ዘማሪዎችም አሉ።

ሆኖም ሁሉም ዘማሪዎች ይህን የሚያደርጉት ሆን ብለው ነው የሚል ጭፍን ግንዛቤ የለኝም። ሳያውቁ የሚሳሳቱ ይኖራሉ። የክልሎችን ሳይጨምር በአዲስ አበባ ብቻ ወደ አራት አካባቢ ኤፍ ኤም ሬዲዮዎች ያሉ ይመስላኛል። ሁሉም ሲሞዝቁ ነው የሚውሉት። ስለዚህ ሰዎች ሻይ ሲጠጡና ታክሲ ሲጠቀሙ ወደዱም ጠሉ ዘፈን ሊሰሙ ይችላሉ። በዘፈን ስሜት ውስጥ፡ሆነው ምዝሙር እንጻፍ ካሉ ደግሞ ይህ የተጠቀጠቁት ዜማ ደግሞ የመዝሙራቸው ዜማ ሆኖ ብቅ ይላል። መዝሙሩ ከዘፈን የተመሳሰለበትን አንድ ዘማሪ ይህንን ጽሁፍ ሳዘጋጅ አናግሬው ነበር። “በጓዳዬ ሆኜ ከእግዚአብሔር የተቀበልኳቸው የመሰሉኝ፡መዝሙሮች ዜማቸው የዘፈን ዜማ ሆኖ እየተገኘ የተውኳቸው ብዙ ናቸው” ብሎኛል። መቼም የችግሩ ስፋት መጣጥፍ ሳይሆን መጽሐፍ ይወጣዋል።

አሁን አሁን ወደ ክልሎች እየወጡ ከአዲስ አበባ ርቀው ጠፍተው ይሆናል እንጂ “ቆርቆሮ ያለው (ያለሽ)” እያሉ የሚዞሩ ትጉ ሠራተኞች በየሰፈራችን አይጠፉም ነበር። የወዳደቁ ብረታ ብረቶች፣ አሮጌ ብልቃጥ፣ አፈር ውስጥ፡የተቀበረ የጫማ ሶል ሁሉ ሲያገኙ ይገዛሉ። እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም። ከየትም የተሰበሰበ ኮልኮሌና ቅራቅንቦ ዜማ ለእርሱ አይቀርብለትም።  የመልእክታቸው ተወራራሽነትማ አስደንጋጭ ነው። አንዱ ዘማሪ የሌላኛውን መዝሙር በሌላ ዜማ ለውሶ ያቀርብልናል። ስለዚህ አዲስ ነገር ከመፍጠር ይልቅ ፍራሽ አዳሽይ መስል አሮጌውን መዝሙር ገረፍ ገረፍ አድርገው ለገበያ ያቀርቡታል። ከተለያዩ መዝሙሮች ተለጣጥፈው የተበጁ ድሪቶ መዝሙሮች በዝተዋልና አዲስ ፈጠራ እያማረን ከቀረ ቆየ።

እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም። ከየትም የተሰበሰበ ኮልኮሌና ቅራቅንቦ ዜማ ለእርሱ አይቀርብለትም።  የመልእክታቸው ተወራራሽነትማ አስደንጋጭ ነው። አንዱ ዘማሪ የሌላኛውን መዝሙር በሌላ ዜማ ለውሶ ያቀርብልናል።

“የሞት መልአክ አያስፈራኝም
ተሸሽጌያለሁ አያገኘኝም”።
ይህን መዝሙር ታውቁታላችሁ? ዶ/ር ደረጀ ለልደታ መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የሰጠው ዝማሬ ነው። ካልተሳሳትኩ  20 ዓመት አልፎታል። ይህንን መዝሙር በቁጥር 4 ካሴቷ ላይ ምሕረት ኢተፋ የራሷ አስመስላ ቃል በቃል አቅርባዋለች፤

“የሞት መልአክ አያስፈራኝም
ተሸፍኛለሁ አያገኘኝም” በማለት።

ልዩነቱ “ተሸሽጌያለሁ” የሚለው በ”ተሸፍኛለሁ” መቀየሩ ብቻ ነው።
ሌላ ልጨምርላችሁ። የጌጃ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን “ሀ” መዘምራን በቁጥር 1 ካሴታቸው ላይ
“ጌታ ቀድሞ ተገኝቶበት
ስፍራውን ይዞ ዐርፎበት
እንዴት ይሰጥማል መርከቡ
ምንስ ቢያይል ወጀቡ?” ብለው ዘምረዋል።
እርሷ ደግሞ ከዓመታት በኋላ፣
“ጌታ ኢየሱስ ተኝቶበት
ስፍራውን ሁሉ ተቆጣጥሮት
እንዴት ይሰጥማል መርከቡ
ምንስ ቢያይል ወጀቡ?”

በማለት የካሴት ዘመቻዋን አሐዱ ብላ ጀምራበታለች።
አጋጣሚ ይሆንን? ካልሆነ የሰው መዝሙር ደብተር ውስጥ፡ ምን ልትሰራ ገባች?! አንድ ልጨምርበት

“ጅማሬዬ ላይ ቆሞ ፍጻሜዬን ያየ
ይኼ ነው አምላኬ ከሁሉ የተለየ (ሲሳይ አበበ #2 – 1998)
“ጅማሬዬ ላይ ሆኖ ፍጻሜዬን ያየ
ይሄ ነው የኔ አባት ከሰው ይተለየ” (ምሕረት ኢተፋ ልዩ ዕትም – 1998) አንድ የመጨረሻ ብቻ ታገሡኝ ፤

“የአለ አዋቂዎች ልቦና በሰዎች ተሥፋ ያደርጋል
ግን እግዚአብሔር ብቻ ደኅንነትን ያዘጋጃል።” መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ #4 1984
“ያለ አዋቂዎች ልቦና የሚታየውን ብቻ ያያል
ግን እግዚአብሔር ብቻ መድኅኒትን ያዘጋጃል።” (ምሕረት ኢተፋ ልዩ ዕትም 1998)

“ምህረት ብቻ አይደለችም ይህንን ያደረገችው፤ የእርሷ ስም ብቻ ለምን ይጠቀሳል?” የሚለው የተለመደው ጥያቄ እንዳይነሣ አንድ ሁለት ጣል ላድርግበት።

“የምድረ በዳው ዳዊት ና ውጣ
የዜማ ጊዜ መጣ።
በእሥር ላይ ያለህ ዮሴፍ ና ውጣ
የክብር ዘመን መጣ” (ያሬድ ማሩ #1-1996) ከሚቀጥለው ጋር አስተያዩት። በመካከላቸው የአራት ዓመታት ልዩነት አለ።

“የምድረ በዳው ዳዊት ከጫካው ውጣ
የመንገሥ ዘመን መጣ
ባለ ራዕዩ ዮሴፍ ከግዞት ውጣ የመክበር ዘመን መጣ” (ሰናይት እንግዳ #6 – 2000)።
ሌላም ልጨምርላችሁ፤

«ማደሪያህ በምስጋና ይሞላ
አምላክ የለምና ካንተ ሌላ» (እንዳልካቸው ሐዋዝ #1 – 1992)
ይሄም “Copy Paste” ይመስላል

«ማደሪያህ በምስጋና ይሞላ
አምላክ የለምና ከዓንተ ሌላ» (ኤልያስ ወልዴ # 1 – 2000)።

«ተራው የእኔ ነው የኔ
አምላኬ አለና ከጎኔ» (ደስዬ ወልዴ #2 – 1997) ። ይቺም በሌላኛው ላፍ ተደርጋለች

«ተራው የእኔ ነው የእኔ
አምላኬ አለና ከጎኔ» (ኤፍሬም ዓለሙ #1 – 1998።

በእርግጥ፡በጣም የወደድነው ጆሮአችንን የምንሰጠውና ልባችንን የነካ ነገር ውስጣችን ሊቀር፣ ከዚያም በራሳችን ሥራ ላይ ተጸዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ስለዚህ ከዚህ በፊት የነበረ ነገር ሳይታወቅ በእኛ ሥራ ላይ ሊንጸባርውቅ ይችላል። ግን ልክ አለው። ከዚህ በላይ የዘረዘርናቸውን በሚመለከት «እነዚህ ሁሉ በአጋጣሚ ነው የሆኑት» እንደማትሉ ተስፋ አደርጋለሁ። የዚህ ዐይነት «ምንተፋዎች» ብዙናቸው። ከተፋው ሳያንስ ምንተፋው! ለናሙናነት እነዚህ ይበቁናል። ካነሰ ሌላጊዜ እንጨምርበታለን።