አምልኮ/Worship - ደቀ መዝሙር https://deqemezmur.com ደቀ መዝሙር መሆን ደቀ መዛሙርት ማድረግ Tue, 04 Oct 2022 23:59:55 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.5.3 https://deqemezmur.com/wp-content/uploads/2022/08/cropped-photo_2022-08-09_18-28-03-32x32.jpg አምልኮ/Worship - ደቀ መዝሙር https://deqemezmur.com 32 32 በዝማሬ አምልኮ ዙሪያ https://deqemezmur.com/2022/10/04/on-worship-and-singing/ Tue, 04 Oct 2022 23:43:44 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2125 በወንድም ለዓለም ጥላሁን (ላሊ) የተጻፈ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል በአምልኮ ጊዜ: የምናመልከው (ምናልባት ባለማስተዋል) ራሳችን በምናባችን እንደመሰለን የሳልነውን “አምላክ” ሳይሆን ራሱን በቃሉና በመንፈሱ የገለጠውን ህያው እግዚአብሔርን መሆኑን እርግጠኞች እንሁን!! የዝማሬ አምልኮአችን ይዘትና ጥልቀት ጥራትና ፍሬያማነት እንዲለወጥ ከአምልኮ በፊት የምናደርገው ቅድመ ዝግጅት ወሳኝነት አለው- በቴክኒክ ብቻ ሳይሆን በመንፈስ!! የሚመለከው ማነው? የሚለውን ጥያቄ በአግባቡ […]

The post በዝማሬ አምልኮ ዙሪያ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
በወንድም ለዓለም ጥላሁን (ላሊ) የተጻፈ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል

በአምልኮ ጊዜ:
የምናመልከው (ምናልባት ባለማስተዋል) ራሳችን በምናባችን እንደመሰለን የሳልነውን “አምላክ” ሳይሆን ራሱን በቃሉና በመንፈሱ የገለጠውን ህያው እግዚአብሔርን መሆኑን እርግጠኞች እንሁን!! የዝማሬ አምልኮአችን ይዘትና ጥልቀት ጥራትና ፍሬያማነት እንዲለወጥ ከአምልኮ በፊት የምናደርገው ቅድመ ዝግጅት ወሳኝነት አለው- በቴክኒክ ብቻ ሳይሆን በመንፈስ!!
የሚመለከው ማነው? የሚለውን ጥያቄ በአግባቡ ስንመልስ የአምልኮአችን አቅጣጫ በትክክለኛው የልብ ቅኝት መገራቱ አይቀሬ ይሆናል!! መረሳት የሌለበት ቁምነገር ግን ዝግጅቱ የሚደረገው ቅዳሜ ማታ ወይም ዕሁድ ጠዋት ሳይሆን ከሰኞ እስከ ሰኞ ሊሆን የግድ መሆኑ ነው!! አምልኮ የሚያነጣጥረው በተመላኪው ላይ ብቻ ነው! ሁለት ተሞጋሾች ሁለት ተወዳሾች ሁለት ተደናቂዎች የሉም! ተመላኪው አንድና አንድ እርሱም “ያለና የሚኖር እኔ ነኝ” ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው!!
አምልኮ በተመላኪው ስምና ዝና ላይ ተንጠላጥለን ለራሳችን አድናቆት የምናተርፍበት ሳይሆን በተመላኪው ፊት ሁለንተናችንን ዝቅ አድርገን በትህትና “እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል” የምንልበት መንፈሳዊ አሰራር ነው!!
1. አምልኮ በየዕለቱ ከተመላኪው ጋር የሚደረግ የቅርበት ግንኙነት የወለዳቸው የትናንሽ ደመናዎች ጥርቅም እንጂ ድንገት የፕሮግራም ቀን ሳይታሰብ የሚከሰት የበረከት ዝናብ አይደለም! በልባችን መሰዊያ ላይ እንደበራ የሚቀጥል የየዕለት የህይወት ዘይቤ እንጂ የፕሮግራም ለት ክስተት አይደለም!
2. በአምልኮ ሰዓት
መዝሙሩና ሙዚቃው ከመቃኘቱ በፊት ልብ መቃኘት አለበት! ሙዚቃው የመዝሙሩን ዜማ ሳይጀምር በፊት የአምላኪው ልብ በራሱ ዜማና melody አምልኮ መጀመር መልመድ ይኖርበታል! ምክኒያቱም እግዚአብሔር አስቀድሞ የልባችንን ዕጣን ሳያሸት የዝማሬያችንን ዕጣን አያሸትምና!!
3. ሳያዩ ማምለክ ስለማይቻል ለማምለክ መገለጥ ይጠይቃል! እግዚአብሔር በዚህ ሳምንት ስለራሱ ምን ገለጠልን? ምን በራልን ነፍሳችን ምን ተረዳች? ምን አወቀች?
የሚገርመው ነገር አንድ ጠብታ መገለጥ አንድ አገር አምልኮ ይወልዳል! ከብዙ መዝሙር ይልቅ በመገለጥና በጥልቅ መረዳት የተዘመረ አንድ ወይም ጥቂት መዝሙር ረጅም መንገድ ያስኬደናል! በአንፃሩ ደግሞ በዛሬ ዓመቱ መገለጥ ብቻ ብዙ ርቀት መሄድ አስቸጋሪ ሆኖ እናገኘዋለን!
4. አምልኮ ስጦታ ይዞ መቅረቢያ ሳይሆን ራስን ስጦታ አድርጎ ማቅረቢያ ነው!
ለዚህ ነው: “ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ህያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ….እለምናችሁዋለሁ” ብሎ ሃዋርያው ጳውሎስ በአፅንዖት የሚያሳስበን (ሮሜ 12:1)
5. አምልኮ የሰውን ሁለንተና ይጠይቃል! ከላይ ያለው ጥቅስ “ሰውነታችሁን” ሲለን ስጋችሁን ማለቱ አይደለም! ሁለንተናችሁን አቅርቡ እያለን ነው – ስሜትን ፈቃድን ሃሳብን ነፍስን ስጋንና መንፈስን!!

The post በዝማሬ አምልኮ ዙሪያ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
አምልኮ ‹‹ምንነቱ፣ እንዴትነቱ እና ለምንነቱ›› https://deqemezmur.com/2022/10/03/worship-the-meaning-and-the-how/ Mon, 03 Oct 2022 19:49:33 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2076 ይህ ጽሁፍ በወንድም ረታ ጳውሎስ የተጻፈ ነው፤ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል፤ ክፍል 4 ባለፉት ክፍሎች እንዲሁ በግርድፉ የዘመናችንን ቤተ ክርሰቲያን የዝማሬ አምልኮ ሥርዓት ግድፈቶች እና መሰናክሎች በማንሳት ለመነጋገር ሞክረናል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ባሉ ክፍሎች የአምልኮ ትርጉም፣ መርህ እና አላማ በአጭር በአጭሩ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ “አምልኮ” የሚለው ቃል ውስጥ ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮችን እናስተውላለን፤ አምላክ፣ […]

The post አምልኮ ‹‹ምንነቱ፣ እንዴትነቱ እና ለምንነቱ›› first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ይህ ጽሁፍ በወንድም ረታ ጳውሎስ የተጻፈ ነው፤ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል፤

ክፍል 4
ባለፉት ክፍሎች እንዲሁ በግርድፉ የዘመናችንን ቤተ ክርሰቲያን የዝማሬ አምልኮ ሥርዓት ግድፈቶች እና መሰናክሎች በማንሳት ለመነጋገር ሞክረናል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ባሉ ክፍሎች የአምልኮ ትርጉም፣ መርህ እና አላማ በአጭር በአጭሩ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ “አምልኮ” የሚለው ቃል ውስጥ ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮችን እናስተውላለን፤ አምላክ፣ መስዋዕት እና አምላኪው፡፡ ሶስቱ ጉዳዮች በአግባቡ ተሳልጠው ልከኛ ቦታቸውን ካልያዙ አምልኮ የሚባለው ነገር ክሳቴ አይኖረውም፡፡ አምላክ (Object of Worship) ሲሆን አምልኮን ተቀባይ ወይም የድርጊቱ መንስኤ፣ ዋና ምክንያት ነው፡፡
                                                                                “አምላክ ስላለ ነው አምልኮ የኖረው!
በማንኛውም ሀይማኖት እና እምነት (ቃልቻ፣ ቦረንትቻ፣ ሌላም ቻ..) የአምልኮ ነገሮች ተመሳሳይ ናቸው፡፡ እኛ የምንነጋገረው ስለ ዓለማቱ ፈጣሪ ታላቁ አምላክ ዘለዘለማዊው እግዚአብሔር ነው፡፡ መስዋዕት ለአምላክ የሚሰጥ ስጦታ ወይም ምላሽ ሆኖ የሚቀርብ ጥልቅ ፍቅር፣ እምነት፣ ከፍተኛ አድናቆት (ውዳሴ)፣ ፍርሃት (እየወደድነው እንፈራዋለን)፣ መንቀጥቀጥ (የአክብሮት ጥግ)፣ መንዘፍዘፍ፣ ድንጋጤ (ሰቦማይ ይላል ግሪኩ)፣ ራስን እስከ መሳት ያለ ከፍተኛ አድናቆት (ራዕይ 1፡17)፣ መገዛት ሲሆን፥ ይህ ደግሞ በሶስት ምልዓተ ደርዝ ይገለጣል፡፡

  1. የሀሳብ አምልኮ (Worship in Thinking)
  2. የአንደበት አምልኮ (Worship in singing or speech)
  3. የሥራ አምልኮ (Worship in action)
  4. የሀሳብ አምልኮ ምንድነው?

ስለ አምላካችን እግዚአብሔር በልባችን ያለው ፍቅር፣ አክብሮት፣ ፍርሃት፣ አድናቆት እና እምነት ነው፡፡ ሀሳብ በጣም የሚገርም ፍጥረት፣ የማንነታችን ክፍል ሲሆን ለሰዎች ሊታይ ፈጽሞ የማይችል የአዕምሮ ቀመር ነው፡፡ በዓለም ያሉ ጠቢባን ሳይነቲስቶች የሰውን የተለያዩ የአካል ክፍሎች በዝርዝር የሚያሳዩ፣ የመጠቁ መሳሪያዎችን ሰርተዋል፡፡ የጭንቅላት ዕጢ፣ የደም መፍሰስ፣ የነርቭ ችግሮችን፣ የተሰበረ አጥንት… ወዘተ ለማየት ችለዋል፡፡ CT SCAN, MRI, X-RAY, ULTRASOUND… ብዙ ነገሮችን ማሳየት የቻሉ የሰው ልጅ ረቂቅ የጥበብ ውጤቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን የቱንም ያህል ቢራቀቁ የሰውን ሀሳብ ለማየትና ለመገንዘብ አልቻሉም፡፡ ሃሳባችን በማንም አይታይም ለዚህም ነው እንደ ፈለግን የምናስበው፡፡ ከሰዎች ጋር አብረን ስንኖር እርስ በርስ ሀሳባችንን መተያየት የምንችል ቢሆን ኖሮ ምን ይሆን ነበር? ስለ ባልንጀራችን የምናስበውን ሁሉ የሚያውቅ መሳሪያ ቢኖር በእውነት በምድር እንኖር ነበር ወይ?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሀሳብ ምን እንደሚል ጥቂት ብቻ እንመልከት፡፡
ኢያሱ 18 የዚህ ህግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይበቀንም በሌሊትም አስብ፤ ያን ጊዜ መንገድህ ይቀናልሃል፡፡
መዝ. 12-3…በእግዚአብሔር ህግ ደስ ይለዋል፣ ህጉንም በቀን እና በሌሊት ያስባል እርሱ በውሃ ፈሳሾች ዳር እንደተተከለች ፍሬዋን እንደምትሰጥ፣ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፣ የሚሰራውም ሁሉ ከናወንለታል።
ፊል. 48 በቀረውስ ወንድሞች ሆይአስቡ
ቆላ 31 በላይ ያለውን አስቡ እያለ ምን ያህል ሀሳባችን ከፍ ያለ ንጹህ እና ቅን ሊሆን እንደሚገባው ቃሉ በአጽንኦት ይናገራል፡፡

አምልኮ ስለ እግዚአብሔር በልባችን ከምናስበው በጎ ነገር ካልጀመረ ይፈርሳል!! ‹‹በሀሳብህ ያላከበርከው ጌታ መድረክህ ላይ አይከብርልህም››!! በልብህ ያላነገስከው ጌታ ድንገት በደመቀ ተቀጣጣይ ዝማሬ አይነግስልህም! የጊታርህ ክር፣ ድምጽህም ቢቃኝ ሀሳብህ ካልተቃኘ ፈርሷል! ዛሬ ሀሳባችንን የሞላው ነገር ምን ይሆን? ሀሳባችን እና መዝሙራችን ይተዋወቃሉ?፣ ይቀራረባሉ? ወይስ በየፊናቸው እየተመሙ ነው? በቀን እና በሌሊት የምናስበው ጉዳይ በመድረክ እና በጉባኤ ከምንዘምራቸው ዝማሬዎች ጋር በእውነት ዝምድና አለው ወይ? ካልሆነ ድርሰተ ተውኔት እየተወንን ብቻ እንጂ እያመለክን አይደለም፣ አፍርሰናል፡፡ በዋልድባ የዘፈነ ዲያቆን አፍርሷል እንደሚባለው እንዲሁ ልንዘፍን አይገባም፡፡ የሀሳብ ጥራት በሌለበት የአንደበታችን ስል ንግግር ሆነ ዜማ እግዚአብሔርን ሊያስደስተው አይችልም፡፡

ምስጋናችን ጥልቅ እንጂ ግልብ ሊሆን አይገባም፡፡ “ግልብ” ምስጋና ቆሌ የሌለው እንዲሁ የሙዚቃ ምት እየተከተሉ የሚሉትንም ሳያውቁ መደሳሰት መፈንጠዝ አይነት ሲሆን:- “ጥልቅ” ምስጋና ግን ከጥልቅ ልባችን የሚፈልቅ፣ በቂ ምክንያት ያለው፣ የጌታ ምህረት ብዛቱ በባለውለተኝነት ስሜት እያናወጠን፣ እንባ እንባ እያለን ወይም የሚፈነቅል ደስታ ሲያስጮኸን ነው፡፡ ደስታም እኮ ጥልቅ እና ግልብ ልዩነቱ ያስታውቃል፡፡ ማንም በማያየው የሀሳባችን ስፍራ እኔ ልንገስ እያለ ነው ጌታ፡!!

አንደበታችን ለሰው ነው፣ ተግባራችንም ለሰው የሚታይ ነው፣ ፍርድ ቤት ዳኛ በንግግርህ አልያም በስራህ እንጂ በሃሳብህ ሊፈርድብህ አይችልም፡፡ እንደዚህ እያሰብክ ነው ስለዚህ ጥፋተኛ ነህ ቢል ዳኛ እንዴት እንግዳ ነገር ይሆን? ለእግዚአብሔር ብቻ በተለየችው የሀሳባችን መሰዊያ አምልኮን ብንጀምር አትጠራጠሩ ሁሉ ይሰምራል፡፡ ልባችን ልክ አይደለም!! ከዚህም የተነሳ በእውነተኛ አምልኮ ልንባረክበት ከሚገባን በረከት በብዙ ጎድለናል፡፡ ፊል 4፡8 ቃሉ “በቀረውስ ወንድሞች ሆይ እውነተኛ የሆነውን…ንጹህ የሆነውን፣ ፍቅር ያለበትን፣ መልካም ወሬ ያለበትን…ወዘተ አስቡ” ሲለን እኛ ሁሉን በተቃራኒው እያሰብን ቢሆንስ? ማር 12፡28 በፍጹም ልብህ፣ ሃሳብህ፣ ነፍስህ እና ሐይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ ሲል እኛ በፍጹም ሪትም፣ ፒች፣ ቅኝት፣ ጩኸት፣ ላይት፣ ጪስ፣ መድረክ፣ ልብስ ብቻ ልንወደው ሞክረን ይሆን? ልብም፣ ነፍስም፣ ሀሳብም፣ ሀይልም የውስጥ ናቸው በመሰረታዊ ደረጃ፡፡ ስለዚህ ጊታራችን ኪቦርዳችን ላይን አሬያችን ምርጥ እንደሆነ ሁሉ ሀሳባችን ምርጥ ይሁን!! ስለ ጌታ፣ ስለ ባልንጀራ፣ ስለ ሀገር፣ ስለ ህዝብ ያለን ሀሳብ በጎ ይሁን፡፡ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ!! መዝ 19፡14 የአፌ ቃል እና የልቤ ሀሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን፡፡ ሀሳብ ሲያምር አንደበት ያምራል፣ ተግባርም ያምራል፡፡

 

 

The post አምልኮ ‹‹ምንነቱ፣ እንዴትነቱ እና ለምንነቱ›› first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ግን ምንድን ነው፣ ኀልዎቱ የመለኮቱ? https://deqemezmur.com/2022/10/01/what-dose-the-presence-of-god-meaning/ Sat, 01 Oct 2022 22:06:04 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2029 ከሰሎሞን ጥላሁን ፌስ ቡክ ገጽ የተገኘ ጽሁፍ እግዚአብሔር ሳይከፋፈል ሳያንስና ሳይበዛ በፍጥረተ ዓለሙ ሁሉ በሙላቱ ይገኛል፣ ይህ ጠባዩ omnipresence/ “ክሳቴ ኩሉ” ይባላል። ድብልቅልቅ ባለው የመርካቶ ግፊያ መሃል ያለ አንድ ገበያተኛ በጠፈር ምርምር ማርስ ላይ የወጣ ጓደኛው ስልክ ደውሎ እግዚአብሔር በዚህ አለ ቢለው መርካቶ መሐል ካለው ማንነቱ የተሻለና ንጹህ ማንነት አለው ማለት አይደለም። እነዚህ የእኛ ርቀቶች […]

The post ግን ምንድን ነው፣ ኀልዎቱ የመለኮቱ? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ከሰሎሞን ጥላሁን ፌስ ቡክ ገጽ የተገኘ ጽሁፍ

እግዚአብሔር ሳይከፋፈል ሳያንስና ሳይበዛ በፍጥረተ ዓለሙ ሁሉ በሙላቱ ይገኛል፣ ይህ ጠባዩ omnipresence/ “ክሳቴ ኩሉ” ይባላል። ድብልቅልቅ ባለው የመርካቶ ግፊያ መሃል ያለ አንድ ገበያተኛ በጠፈር ምርምር ማርስ ላይ የወጣ ጓደኛው ስልክ ደውሎ እግዚአብሔር በዚህ አለ ቢለው መርካቶ መሐል ካለው ማንነቱ የተሻለና ንጹህ ማንነት አለው ማለት አይደለም። እነዚህ የእኛ ርቀቶች ለእግዚአብሔር በኢንች አይራራቁበትም፣ ሥፍራዎች ሳይፈጠሩ በፊት የነበረው በስፍራዎች ሁሉ ሳይቀናነስ አለ- መገኛዎቹ ግን እርሱነቱ አይደሉም … በብሉይ ለምሳሌ ታቦቱን አስመልክቶ ሲስቱ፣ “ታቦቱን ይዘን ጦርነት ብንወጣ ድል እናደርጋለን” አሉ እነርሱም አለቁ ታቦቱም ተማረከ። የመገኛው ምሳሌና እርሱ ራሱን ሲያምታቱ ሳጥን ውስጥ እንደማይገባላቸው አሳያቸው! …ለምሳሌ በአዲስ ኪዳን አማኞች  ሲስቱ “የመለኮት ማደሪያ መለኮት ነን አሉ”፣ (አፌ ቁርጥ ይበል) ግማሾቹም ሞቱ ያሉትም አሉ በሙተት ላይ። ስለዚህ ከእኛ ጋር ነው እንጂ እኛን አይደለም!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

ይህ ሳይርቅ መቅረቡ “አባታችን ሆይ” እንድንል ሲያደርገን፣ ረቂቅና ምጡቅነቱ (ትራንሴንደንስ) “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” እንድንል ያደርገናል። ክርስትናን ልዩ የሚያደርገው ይህ ነው።  ስለዚህ እየቀረብነው እንፈራዋለን እየፈራነው እንወደዋለን!

የህልውናው ስሜት የመገኘቱ መገለጥ ነው እንጂ የሆነ ቦታ የሄደው ሲመጣ አይደለም፣ “እግዜር ” ለአፍታ በመሄዱ የተነሳ የሌለበት ቦታ ሊኖር አይችልም፣ እነዚህ ሁሉ መለዋወጦች ያሉት እኛ ዘንድ ነው። እኛ ከዚያ ስንመጣ ያለነው እዚህ ነው፣ ከዚህ ስንሄድ ያለነው እዚያ ነው! ለእግዜር ግን ህልውናው በመጠን አይቀናነስም። የእግዚአብሔር መገኘት እኛ ሲሰማን ከሆነ ቦታ መጣሁ ብሏቸው አደለም እኛ ዘንድ ያለው – ኢያኢሮስ ይሔ ስለገባው ነው ጌታን “ባትሔድም እዚያ ነህ ብቻ ቃል ተናገር” ያለው። እዚህ የእድሜ ልክ ደም ፍሳሽ ሲያቆም በዚያው ሰከንድ እዚያ ማዶ ከመቅሰፍት ሞት ይመልሳል! ሉቃስ 8:41-56 ስለዚህ እቅርብ ላለው ጉዳያችን ደሜን አቁምልኝ ስንለው ሩቅ ያለውን ጉዳያችንን ከሞት አስነሳልኝ የማለት የእምነት ድፍረት ይፈቀድልናል!

የእግዚአብሔር የህልውናው ተሰምቴዎቻችን መለዋወጥ እኛ ዘንድ ካሉ ልምምዶች ጋር የተያያዙ ናቸው። ምንም እንኳ የህልውናው ስሜት ለሁላችንም “እነሆ” የተባለ ቢሆንም፣ ሁላችንም አንድ ዓይነት ስላልሆንን በተመሳሳይ አንለማመደውም! እድሜ፣ ያለንበት መንፈሳዊ ደረጃ፣ የመንፈሳዊ የህይወት ተሞክሮ፣ የምንሰጠው ጊዜ “ሊትል ኢንቲሜሴ ሊትል ካፓሲቲ” አለ [ቶኒ ኤቫንስ] ልምምዶቻችን ይለያያሉ፣ ሁላችንም ግን መንፈሳችን ክፍት ነው … ለህልውናው መነካኪያ ቅባሪ የሰው ልጅ ሁሉ አለው። ስለዚህ በምንም ዓይነት መንፈሳዊ ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም የኅልውናውን ስሜት አለመፈለግ ከተፈጠርንበት አላማ በታች ለመኖር መወሰን ነው! እግዚኦ በሉ አንድ ጊዜ ፟_ ስንት ቀን ነው ያለዚህ ስሜት መኖር የምትችሉት? እነሆ ምርጫው የእናንተው ነው፣ አማኝ ሆኖ እንደ አላማኝ መኖር ….

እግዚአብሔር የህልውናውን ስሜት ከሌሎች የተሻለ ነጥሎ ለእገሌ አብዝቶ የሰጠው የለም “ኤልያስ እንደኛው ሰው ነበረ ..” ማለት ይኽው ነው…. እንዲያውም ብዙ ጊዜ ስፍራ የሚያናውጠው በማህበር ሲያገኘን ነው፤ የሐዋ 2፡… እነርሱም ስፍራውም ተናወጠ ዘጸ 40 … ተራራው ጤሰ – ስለዚህ ስንሰበሰብ ኅልውናው ይሰማናል ወይ? ስንሰባሰብ የማን ኅልውና ይሰማናል? ወንድሞች በኅብረት …
እግዚአብሔር እዚህ/እዛ ነው እንጂ እዚህ ብቻ እና እዛ ብቻ አይደለም። በክርስትና አስተምህሮ ሁለት የእግዚአብሔር ሀልዎት መገለጫ ቃሎች አሉ መለኮታዊ ምጡቅነቱና መለኮራዊ ቅርበቱ (138 ፡7)…  እግዚአብሔር ሳያንስና ሳይበዛ ያለ መስፈሪያ አለ።

ሀ. ወደ ላይና ወደ ታች 7- 8 የምታወቀው በምድር ላይ ስላለሁ ነው ብዩ ወደ ሰማይ ብመጥቅ ቀድመኸኝ አገኝሃለሁ ወደ ታችኛው ጥልቁ ብሔድ የዚህም ሥፍራ ዳኛ አንተ ሆነህ አገኝሃለሁ (አሞጽ 9:2)
ለ. ምስራቅና ምእራብ 9-10 ላይና ታች ባይደብቁኝ ንጋት በሚነጋበት በምስራቁ በኩል በማለዳ ተነስቼ ጸሐይ ሳትጠልቅ እንደ ንስር ሁለት ሜትር ክንፍ ባወጣና ወደ ምእራብ ብሸሽ ያ ይረዳኝ ይሆን? ለዚህ እንኳ ቀድመኸኝ መንገዱን ያበጀኸው አንተ ነህ –  በሁሉ ሥፍራ በአንድ ጊዜ ለሚገኘው ጌታ ምስራቅና ምእራብ የለውም ሁሉም ነገር ለእርሱ እዚህ ጋ ነው!!!!!  ስለዚህ ካንተ ሽሽት ከእግዜር ወጥቶ ወደ እግዜር መግባት ነው ካለ በኋላ – ከጅረት ወደ ወንዝ፣ ከወንዝ ወደ ሐይቅ፣ ከሐይቅ ወደ ባህር ከውሃ ወደ ውሃ

እግዚአብሔር በስፍራዎች ሁሉ ይገኛል ማለት ስፍራዎች ሁሉ እግዜር ናቸው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር የመገኛዎቹም ድምር ውጤት አይደለም – ይኽ ፓንቴይዝም ነው እግዚአብሔር እዚህ እዛ ነው እንጂ እዚህ ውስጥ አይደለም። ለእግዜር የቀረበ ነጥብ ላይ ያለ ማንም የለም፣ ለዚህ ነው አማላጅ የሚባለው ነገር የማይሰራው” እንደታዋቂ ሰዎች አንተ ትቀርበዋለህ አናግርልኝ አይባልም። የስላሴ አካል እግዜር ሰው የሆነው ክርስቶስ ብቻ ነው ይህን ሚና የሚጫወት-  እግዚአብሔር ቁስ አይደለም በቅርበትና በርቀት ከ ጀምሮ እስከ አይባልም. “አለ” የሚለው ቃል የማይሰራበት የፍጥረቱ ክልል የለም። መዝ 139 ፡7-13

ስለዚህ፦ መንፈሳዊ ቦታ ነው ብለን ያልንበት ቦታ ስንገኝ የምናሳየው ጥንቃቄና ሌላው የህይወታችን ቦታ የምናሳየው አንድ ዐይነት ሊሆን ይገባል:: ይኼ እኮ ቤተ ክርስቲያን ነው እንዲህና እንዲህ አይባልም አይደረግም እንላለን እዚህ ያለው እዚያ የለም ወይ?

The post ግን ምንድን ነው፣ ኀልዎቱ የመለኮቱ? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
የሚደረገውን ማድረግ ወይስ የሚያደርገንን መሆን? https://deqemezmur.com/2022/09/26/doing-what-he-wants-us-to-do-or/ https://deqemezmur.com/2022/09/26/doing-what-he-wants-us-to-do-or/#respond Mon, 26 Sep 2022 21:11:31 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2095 ይህ ጽሁፍ በወንድም ረታ ጳውሎስ የተጻፈ ነው፤ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል፤ ክፍል 3 የእውነተኛ አምልኮ ሀ ሁ በክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ፈቃድ የተደረግነውን ምንነታችንን (ማንነትን) ከማወቅ እና በምድርም (በጊዜ እና በቦታ) በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ተገልጦ ከልባችን እስከ መላው ሰውነታችን የምር ለአምላካችን “የሚያደርገንን መሆን እንጂ የተለመደ የተሸመደደ ተግባርን መድገም” አይደለም። በክፍል 2 ያነሳሁትን […]

The post የሚደረገውን ማድረግ ወይስ የሚያደርገንን መሆን? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ይህ ጽሁፍ በወንድም ረታ ጳውሎስ የተጻፈ ነው፤ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል፤

ክፍል 3
የእውነተኛ አምልኮ ሀ ሁ በክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ፈቃድ የተደረግነውን ምንነታችንን (ማንነትን) ከማወቅ እና በምድርም (በጊዜ እና በቦታ) በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ተገልጦ ከልባችን እስከ መላው ሰውነታችን የምር ለአምላካችን “የሚያደርገንን መሆን እንጂ የተለመደ የተሸመደደ ተግባርን መድገም” አይደለም። በክፍል 2 ያነሳሁትን የጉባኤ ዝማሬ ሁኔታ በደንብ ስናጤን ሊተርጂካል አዘማመር በወቅቱ ስሜታዊ መስተጋብርን በጣም የሚቃወም ነበረ። በሉተራን አዘማመር ስርአት እልልታ፣ ሽብሸባ፣ ጩኸት እና ሌሎች በነፍስ መነካት የሚንጸባረቁ ነገሮች እጅግ በጣም ክልክል ነበሩ። እኔ ራሴ በማስታውስበት ዘመን በቃለ ህይወት እና በመካነ ኢየሱስ እልልታ ጭብጨባ ሀሌሉያ ጩኸት ፉጨት (አሁንም) የተወገዙ ነበሩ በቃለ ህይወት የማስታውሰው በዓመት ሁለት ጊዜ እልልታ ይፈቀድ ነበረ፣ በጌታችን ልደት እና በትንሳኤው ቀናት ብቻ። እሱም ኮሚቴ ተዋቅሮ በጥንቃቄ ነው። ስንት ጊዜ እልል እንደሚባልም ተወስኖ ለጉባኤ ተነግሮ ነው። ከተባለው ቁጥር ያሳለፈ ቀጥታ ተይዞ ወደ ጸሎት ክፍል ተወስዶ አጋንንት ነው ተብሎ ይገሰጻል።

መዘምራን ቆመው ሲዘምሩ እንቅስቃሴ ፈጽሞ ክልክል ነበረ። የተንቀሳቀሰ ከ 4-6 ወር አገልግሎት ይቀጣ ነበር። አንድ ወንድም በአኮርዲዮን ኳየሩን እያጀበ አጨዋወቱን ቀየር አድርጎ እንደ እልልታ ሲያደርገው አንዱ የቤ/ክ መሪ አወቀበት፣ አኮርዲዮኑን እልል አስብለሀል ተብሎ ተጠርቶ ተገሰጸ ተቀጣ። ይገርማል! ይህንን የመሣሰሉ ብዙ ነገሮች ነበሩ። የሚተኮረው እውነት ላይ እንጂ ስሜታዊ ነገሮች ላይ አልነበረም። የዚያን ጊዜ ክርስቲያን ብርቱ ፣ መንፈሳዊ የሚባለው መከራን ተቋቁሞ ወንጌል ሲሰብክ፣ በመከራ ሲጸና፣ በጸሎት ሲተጋ እንጂ በጣም እየዘለለ ሲዘምር ወይም አሜን ሀሌሉያ ሲል አይደለም።

ሆኖም በስሜታችን ጌታን ማክበር ምንም ጥርጥር የለውም ተገቢ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። መንፈስ እና ስሜት ግን ይለያያል፣ ለየቅል ነው! መንፈስ ቅዱስ ስሜታችንን ሊነካ ይችላል? አዎ በደንብ!! ወይ ሊያስለቅሰን፣ አልያም ሊያስቀን ሊያስደስተን ይችላል። ሙዚቃ እና ዝማሬስ ስሜታችንን ሊነካ ይችላል? በሚገባ! እንኳን መዝሙር ዓለማዊ ዘፈንም ስሜትን ይነካል። ስሜታችን በማንኛውም አርት (ኪነ ጥበብ) ለመነካት ቅርብ የሆነ የተፈጥሯችን ክፍል ነው። ታላላቅ ፈላስፎችም  ” The purpose of Art is Emotional infection” ብለዋል። ሙዚቃ የሰውን ብቻ ሳይሆን የእንስሳትንም ስሜት ይነካል።
ለምሳሌ: – በአውሮፓ በተደረገ ጥናት የወተት ላሞች ክላሲካል ሙዚቃ ሲከፈትላቸው ወተታቸውን በጣም ይለቁታል። በጃዝ ሙዚቃም ዶሮዎች እንቁላል የመጣል ፍጥነታቸው ጨምሯል። ተክሎችም ለሙዚቃ ምላሽ በመስጠት አበቦቻቸው ሙዚቃ ወደአለበት አቅጣጫ ዞረው ተገኝተዋል። ለዚህ ነው የተቀላቀለብን፣ ጥንቃቄም የሚያስፈልገን። “መንፈስ” የምንለው ነገር መንፈስ ቅዱስን ይሁን የመዝሙሩን ከባቢ (Atmosphere) አንዳንዴ ግልጽ አይደለም።

መንፈስ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ አይደለም!
ለምሳሌ: ዛሬ የፓርላማው ስብሰባ መንፈስ ጥሩ ነበረ ስንል መንፈስ ቅዱስ ወይም መንፈስ እርኩስ ለማለት አይደለም። ከባቢው፣ አንድምታው፣ ሁናቴው ለማለት ነው መንፈሱ የምንለው በተለምዶ። በጉባኤ ዝማሬ ወቅትም መንፈሱ ጠፋ ወረደ ወይም የሚገርም መንፈስ ነበረ ስንል ብዙ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን እያመለከትን አለመሆኑን ልብ በሉ።

ይሁንና መንፈስ ቅዱስ ግን ከሥላሴ አንዱ የሆነው ራሱ እግዚአብሔር ነው፣ የሚገኘውም እውነት ውስጥ እንጂ ስሜት ውስጥ አይደለም። ስሜት እውነትን የምንገልጥበት መንገድ እንጂ በራሱ እውነት አይደለም። ከራሱ ፣ ስሜት ካለው ከእግዚአብሔር የተሠጠን ድንቅ ስጦታ ነው ስሜት። እውነተኛ አምልኮ ለሙዚቃ ግለት የሚሰጥ ምላሽ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ቸርነት፣ ማዳን፣ ድንቅ ስራ እና ለማንነቱ ውበት በእውነት እና በመንፈስ የሚሰጥ ምላሽ ነው። ምላሽ ካለ አነሳሽ አለ ማለት ነው፣ አነሳሹ ራሱ ተመላኪው ጌታ ነው። አንድ ጊዜ ጋሽ ንጉሤ ቡልቻ እንዳለው እግዜር ያልጠቀሰው ሊያመልከው አይችልም። ጥቅሻ በሰዎች ማህበራዊ ኑሮ ውስጥ ራሱን የቻለ የተግባቦት መንገድ መሆኑ እሙን ነው።

ስናጠቃልለው ዝማሬ ስንዘምር ስሜት አልባ እንሁን እያልኩ ሳይሆን ስሜታችን እውነትን ሸፍኖ ከአምልኮ መግለጫነት ወደ ተመላኪነት ከፍ ሲል ይህ ከፍተኛ ውድቀት መሆኑ ይታወቅ ነው እያልኩ ያለሁት። የስሜት አምላኪዎች (Worshippers of their emotions) እየበዙ ነው!! ዝማሬ ከልብ ከሆነ ፣ ከምር ከመንፈስ ፣ በቃሉ ቅኝት ከሆነ ስሜታችን አምልኮን ለመግለጥ ወሳኝ ቅመም ነው! እንኳን እግዚአብሔርን ሰውንም ስንወድና ስናመሠግን ስሜትን ካልጨመርን ውበት የለውም።

The post የሚደረገውን ማድረግ ወይስ የሚያደርገንን መሆን? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
https://deqemezmur.com/2022/09/26/doing-what-he-wants-us-to-do-or/feed/ 0
እንዴት እዚህ ደረስን? ቀጥሎስ ወዴት? https://deqemezmur.com/2022/09/25/how-we-get-here/ Sun, 25 Sep 2022 22:10:32 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2108 ይህ ጽሁፍ በወንድም ረታ ጳውሎስ የተጻፈ ነው፤ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል፤ ክፍል 2 የወንጌል አማኝነት ክርስትና (Evangelical Christianity) በሀገራችን በሙላት ከገባ በትንሹ 95 አመታትን አስቆጥሯል። ሆኖም በ1889 አካባቢ በባህረ ነጋሽ (ኤርትራ) ተጀምሮ የነበረውን የሚሽነሪዎች አገልግሎት ከጨመርን 120 ዓመት ያልፋል። የስዊድን፣ የፊንላንድ እና የኖርዌይ..ወዘተ ሚሽነሪዎች ይህንን የወንጌል ተልዕኮ ይዘው ወደ ሀገራችን ሲመጡ ለህዝቡ ያስተማሩት ቃሉን […]

The post እንዴት እዚህ ደረስን? ቀጥሎስ ወዴት? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ይህ ጽሁፍ በወንድም ረታ ጳውሎስ የተጻፈ ነው፤ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል፤

ክፍል 2
የወንጌል አማኝነት ክርስትና (Evangelical Christianity) በሀገራችን በሙላት ከገባ በትንሹ 95 አመታትን አስቆጥሯል። ሆኖም በ1889 አካባቢ በባህረ ነጋሽ (ኤርትራ) ተጀምሮ የነበረውን የሚሽነሪዎች አገልግሎት ከጨመርን 120 ዓመት ያልፋል። የስዊድን፣ የፊንላንድ እና የኖርዌይ..ወዘተ ሚሽነሪዎች ይህንን የወንጌል ተልዕኮ ይዘው ወደ ሀገራችን ሲመጡ ለህዝቡ ያስተማሩት ቃሉን ብቻ ሳይሆን መዝሙሮቻቸውንም ጭምር ነበር። የመዝሙሮቹ የዜማ ዘውግም የሚሽነሪዎቹ ሀገር ሲሆን አዘማመሩም በህብረት እና በሐርመኒ (በአራቱ መሠረታዊ ድምጾች) ነበረ።መዝሙሮቹ በመጽሐፍ ተጽፈው (በታይፕ ወይም በእጅ) ጉባኤ ሲሰበሰብ በየወንበሩ ይሰራጫሉ፣ የሚዘመረው ዝማሬ ገጹ ተገልጦ በፒያኖ ወይም በኦርጋን በመታጀብ በፕሮግራም መሪ (ኮንዳክተር) እየተመራ ይዘመራል። የመጀመሪያው የመዝሙር መጽሐፍ በ1890ዎቹ በባህረ ነጋሽ የተጻፈው 40 መዝሙሮችን የያዘው መጽሐፍ እንደሆነ ይነገራል። በገጠሩ አካባቢ ደግሞ እዚያው በጉባኤ የሚፈጠር የቅብብሎሽ ዝማሬ (Antiphonal Chanting) ይታወቅ ነበረ።

በተለይም በጌድኦ፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በወላይታ እና በሀዲያ ህዝብ የተለመደ እና የደመቀ ጉባኤያዊ (Liturgical) አዘማመር ነበረ። ሊተርጂካል አዘማመር ማለት ጉባኤው ዋና ተዋናይ ወይም ሚና ተጫዋች የሆነበት የአዘማመር ዘዬ ማለት ነው። ከኢየሱስ ክርስቶስ እና ከሐዋሪያት ጀምሮ በሮማ ካቶሊክ ቀጥሎም በሉተራን የነበረ ሰፊውን የቤተክርስቲያን ታሪክ ሞልቶ የያዘው አዘማመር ይህ ሊተርጂካል አዘማመር ነበረ ቢባል አይጋነንም። ዋናው ዘማሪ ህዝቡ ነበረ!!ከመጽሐፉ እና ከቅብብሎሽ ባህላዊ አዘማመር ቀጥሎ ጊዜው በውል ባይታወቅም በግምት ከ1950ዎቹ መጨረሻ የሶሎ ዝማሬ፣ የኳየር ዝማሬ እንዲሁም የሀገርኛ ቅኝት ዘመናዊ አዘማመሮች የተጀመሩበትና በሚገርም ፍጥነት እየተስፋፉ የመጡበት ጊዜ ነበር። በሶሎ ዝማሬ እነ አዲሱ ወርቁ፣  ለገሰ ወትሮ፣ ደረጀ ከበደ፣ ሸዋዬ ዳምጤ፣ ታምራት ወልባ፣ ተስፋዬ ጋቢሶ፣ ታምራት ኃይሌ፣ ሙሉ ሀይሉ፣ አስቴር ተፈራ…ወዘተ

1960ዎቹን እና 70ዎቹን በተለየ ውበት እና ጣዕም ወንጌልን ያበሰሩበት፣ ቅዱሳንንም በዚያ ሁሉ ስደት ያጽናኑበት ወርቃማው ዘመን ነበር። እዚህ ውስጥ በሙዚቀኝነት እና የኳየር አሰልጣኝነት ጋሽ ደበበ ለማ ( አሁን ፓ/ር) ሌሎች ስማቸው ያልተጠቀሰ ብዙ አገልገዮች በየስፍራው ነበሩ። በአጭሩ ነው!ቀጣዩ የጉባኤ አዘማመር የነበረው የአዝማች ምርጫ ነው። ፕሮግራም መሪው ቆሞ ጉባኤውን መዝሙር ያስመርጣል፣ በጊታር ወይም በአኮርዲዮን ካልሆነም በእህቶች እገዛ የመግቢያ ፒች ይሰጣል ጉባኤው ይዘምራል።  ፕሮግራም መሪው ቢዘምርም ባይዘምርም ፣ መዝሙሩን ቢችልም ባይችልም ችግር የለም- ህዝቡ የሚወዘወዘውን እጅ እያየ ቅልጥ ድምቅ አድርጎ ይዘምራል።

በመጨረሻም እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ የቀጠለው ይህ ህዝባዊ አዘማመር በ1990 ዓ/ም ባልሳሳት በእህታችን ሊሊ እንዲሁም ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን መመስረት ጋር ተያይዞ በአሜሪካ ጴንጤቆስጤ እንቅስቃሴ የተለመደው አምልኮ መሪ (Worship leader) እና የአምልኮ ቡድን (Worship team) የተባለው የጉባኤ አዘማመር ዘውግ ተከሰተ።

የሽብሸባ ኳየር ፣ ዘማሪ እንዳልካቸው ሐዋዝ፣ ቤተልሔም ወልዴ …ወዘተ በወቅቱ አስደናቂ በሆነ የመንፈስ ቅዱስ ህልውና እና መነቃቃት ጉባኤውን በዝማሬ መምራት ጀመሩ። አዲስ ነገር ነው!! በጣም ይማርካል!! ብዙዎችን አጽናንቷል አነቃቅቷል አረስርሷል። እኔም በወቅቱ ከተባረኩት አንዱ ነኝ ክብር ለጌታ ይሁን!

ይህ የአምልኮ መሪ የሚለው አደረጃጀት ከተለያዩ አብያተክርስቲያናት ከባድ ተቃውሞ እየገጠመው ምናልባት እስከ 1993 ዓ/ም ብቻ ቆየ እንጂ ከመካነ ኢየሱስ፣ ከቃለ ህይወት ጀምሮ ሁሉንም አጥቢያ ሞላው። የካሴት መዝሙሮችን እያጠኑ በአንድ ፒች እና ሪትም የሚሄዱ ብዙ መዝሙሮችን እየቀጣጠሉ መዘመር ታሪኩ በአጭሩ ይህን ይመስላል። አሁን ይህ ጉዳይ ምን ላይ ነው ያለው? ያ ሁሉ ከጅምሩ የነበረው ውበት እና በረከት ለምን ወደ ብስጭት፣ ግልብ ዝላይ፣ የተለመደ ጩኸት…አታታታታ….ራቻቻቻቻ…እእሪሪሪ…የት አለ ጩኸት አይሰማኝም…ውውውይይይ…እንዴት ተቀየረ??

በዋልዝ:- አቤት ምህረት የበዛለት ብሎ ጀምሮ በመሀል 6/8 ወሎ፣ 12/8 ችክችካ (ዋጋው በገዠፈ ቴምፖ) ምን ልሁና ምን ልሁና፣በመጨረሻም በፈጣን ዲስኮ በመንፈሱ ስሆን..ዳራ ራራራ…የሚሄደው የተሸመደደ (Predictable) ከልብ ያልሆነ ግልብ አዘማመር የዋን ማኑን አይን አይን እያዩ፣ ስሜቱን እየተከታተሉ አልሰለቻችሁም ወይ??

መዝሙር የአርፋጅ ፕሮፌቶች መጠበቂያ፣ *የትንቢትና ስም ጥሪ* ማዳመቂያ፣ የህዝብን ስሜት ብቻ በማጦዝ ለሁሉ “አሜን” እንዲል ማደንዘዣ፣ እንደው እንደ ዲጄ ሙዚቃ መዛፈኛ መፈንጠዣ፣ ጭር እንዳይል በሰርግ ቤት ተበርቻቻ ሆኖ የሚቀጥል አይምሰላችሁ። ሊዘመርለት የተገባው የቤቱ ባለቤት ጅራፉን ያነሳል!!!

እንግዲህ እቀጥላለሁ በክፍል 3

መጽሐፍ ቅዱሳዊው ጉባኤያዊ አዘማመር እና የህብረት አምልኮ መርህ፣ አላማ፣ ስርዓት፣ አመራር … እንዴት ነው??

The post እንዴት እዚህ ደረስን? ቀጥሎስ ወዴት? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
“መዝሙር ወይስ መዝናኛ?” https://deqemezmur.com/2022/09/20/singing-for-the-lord-or-entertainment/ Tue, 20 Sep 2022 22:33:40 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2032 የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊ ረታ ጳውሎስ ነው፤ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል፤ ክፍል አንድ የዜማ ስርአተ አምልኮ ውድቀት ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት ሁሉ መዘመር የተለመደ ነገር ነው። ደቀ መዛሙርቱም ከኢየሱስ ጋር ሆነው ዘምረዋል። ማቴ 26:30 ሐዋርያው ጳውሎስ ዘምሩ ተቀኙ ብሏል። ኤፌ 5:19 በአዲስ ኪዳን ዘመን ሁሉ በብዙም በጥቂት፣ በዝግታም በጩኸት ሲዘመር ነበረ እየተዘመረም ነው። አሁን ግን […]

The post “መዝሙር ወይስ መዝናኛ?” first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊ ረታ ጳውሎስ ነው፤ በጸሃፊው ፈቃድ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወጥቷል፤

ክፍል አንድ

የዜማ ስርአተ አምልኮ ውድቀት
ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት ሁሉ መዘመር የተለመደ ነገር ነው። ደቀ መዛሙርቱም ከኢየሱስ ጋር ሆነው ዘምረዋል። ማቴ 26:30
ሐዋርያው ጳውሎስ ዘምሩ ተቀኙ ብሏል። ኤፌ 5:19 በአዲስ ኪዳን ዘመን ሁሉ በብዙም በጥቂት፣ በዝግታም በጩኸት ሲዘመር ነበረ እየተዘመረም ነው።
አሁን ግን ያለው እድገት የሚመስል ዝቅጠት ቃሉን ከመዘመር፣ በማስተዋል ከመዘመር፣ የምር ከመዘመር፣ ለአምላክ ከመዘመር ያፈነገጠ ተዝናኖታዊ ፈንጠዚያ (ዘፈናምነት አለ ዘላለም መንግስቱ) እንደ ወረርሽኝ እየተራባ ነው።
ዋን ማኖቹ ጋ ደግሞ ብሷል። ዋናውን ካላስደሰትክ ማይክ ሁሉ ትነጠቃለህ!! ጉባኤውን አስተኛህብኝ፣ ዘጭ አረክብኝ ተብለህ ከመድረክ እያለህ በምልክት መዝሙር ቀይር አልያም ለሌላ ሰው ስጥ ትባላለህ። አድምቀው፣ ቀውጠው፣ ከፍ አርገን፣ ሿሿ ሸምበለላ፣ እሳት፣ እሪሪሪ…እንጂ የንሰሀ መዝሙር??? በጌታ ስም ይወጋል። የጥልቅ አምልኮ፣ የጤናማ ሙዚቃ እና ድምጽ ለዛ ፈጽሞ የሚገባቸው አይመስልም። ባንዱ በሲንኮፕ ምት ፋታ የሌለው ሙዚቃ መጫወት አለበት። ዝግ ያለ ነገር ዝቅ ያደርጋቸዋል አይወዱም። ጭር ሲል ይጨንቃቸዋል፣ ሕዝቡ ጥሎ የሚሄድባቸው ይመስላቸዋል። ጌታ በጣም ከበረ ተመለከ የሚባለው ከፍተኛ ጩኸት (120 db) ፣ ከፍተኛ ዝላይ እና ላብ ያለበት ዝማሬ ሲሆን ነው።

“ዋናውን ካላስደሰትክ ማይክ ሁሉ ትነጠቃለህ!! ጉባኤውን አስተኛህብኝ፣ ዘጭ አረክብኝ ተብለህ ከመድረክ እያለህ በምልክት መዝሙር ቀይር አልያም ለሌላ ሰው ስጥ ትባላለህ።”

እንዴት አይነት ምስኪንነት ነው? ድንግዝግዝ ጨለማ ውስጥ ያላችሁ የአሻገዳዎ አፍቃሪያን ጌታ ልቦናችሁን ያብራ። ችግሩ አትሰሙም፣ እናንተን ማን ያስተምራል? አስተማሪህን ልታስተምር አትችልም ብሏል እኮ አንዱ ዋና ማን ኦፍ ጎድ። እኔ የአርኪቴክቸር አስተማሪዬን በአንድ ወቅት ጊታር አስተምሬዋለሁ። ስጦታ ልዩ ልዩ ነው። አርኪቴክቸር ላይ እኔ የእሱ ተማሪ ነኝ፣ ጊታር ላይ እሱ የእኔ ተማሪ ነው አለቀ!! ሁሉን እኛ እናውቃለን የምትሉ ጓዶች እስቲ አደብ ግዙ። ስለ ድምጽ፣ ዜማ፣ አምልኮ…ወዘተ ተማሩ። ሁል ጊዜ እናንተ ደረጃ መዳቢ፣ አስመስካሪ፣ አስተማሪ፣ አናዛዥ ሆናችሁ እናንተን ማን ያገልግል? በሌሎች አገልግሎት አትነኩም አትባረኩም እናንተ ሁሌም ነኪ፣ ባራኪ፣ ሰጪ ናችሁ። ጥሩ ነው ጎሽ ከማለት ውጪ ከበታቻችሁ ያሉ አገልጋዮች ሲያገለግሉ ተባርኬአለሁ ነጽናንቻለሁ ጌታ ተናግሮኛል ማለት በእናንተ ዘንድ ነውር አይደለም ወይ? ተአምር ቢሆንላችሁ እንኳ ትመሠክራላችሁ ወይ?

ዛሬ ትንሽ ጠንከር ብያለሁ ይቅርታ!! ከፍቅር ከመንፈስ ነው እየተናገርኩ ያለሁት!

ወደ መዝሙሩ እንመለስና እባካችሁ ማስተዋላችንን አትንፈጉን! ዘማሪዎችም “ዘምሮ አደር” ከመሆን ይልቅ ለእውነት ሙቱ!! እንጀራም ውሀም ይቅር የጠራችሁ ጌታ፣ መዝሙር የሰጣችሁ ጌታ አዕምሮም ሰጥቷችኋል እየሰራችሁ ማገልገል ትችላላችሁ። የማታምኑበትን የአስረሽ ምቺው ዳንኪራ አገልግሎት ለማይረባ መብል ብላችሁ አትስጡ!!!! በቃ በሉ!!! መዝሙር በመንፈስ ከመሞላት፣ በቃሉ ከመሞላት፣ ከልብ ፈልቆ ለእውነተኛ አምላክ በመሠዊያው የሚቀርብ መስዋዕት እንጂ የመድረክ ትወና አይደለም። ቆላ 3:15
ይህንን ሁሉ ስጽፍ በከፍተኛ ሁኔታ ለእውነተኛ የዜማ አምልኮ የሚተጉ ጉምቱ አገልጋዮችን ባለመዘንጋት ነው።

 

The post “መዝሙር ወይስ መዝናኛ?” first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ማምለክ ወይንስ ማድመቅ? https://deqemezmur.com/2022/05/13/%e1%88%9b%e1%88%9d%e1%88%88%e1%8a%ad-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%8a%95%e1%88%b5-%e1%88%9b%e1%8b%b5%e1%88%98%e1%89%85/ Fri, 13 May 2022 23:49:08 +0000 http://deqemezmur.com/?p=1044     መቼም መዘመር መልካም ነው ለጌታ የሚገባውን ማቅረብ ይገባናል መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው። ግን ግን አንዳንዴ ጥያቄ እንድጠይቅ የሚያደርጉኝ፡ ነገሮች አሉ እንደው እንዳላየ ሆኜ ለማለፍ ካልፈለኩ በቀር፡ አምልኮ ጭፈራችን ነው ወይንስ ሕይወታችን? አካሄዳችን ወዴት ነው? ምን እያደረግን ነው? በእኛና በዚያኛው (በዓለማዊው) ሰፈር ያለው ልዩነት ምን መሆን አለበት? የመገናኛ ብዙኃን (Social network) በሰፊው ግልጋሎት ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮ […]

The post ማምለክ ወይንስ ማድመቅ? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>

 

 

መቼም መዘመር መልካም ነው ለጌታ የሚገባውን ማቅረብ ይገባናል መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው። ግን ግን አንዳንዴ ጥያቄ እንድጠይቅ የሚያደርጉኝ፡ ነገሮች አሉ እንደው እንዳላየ ሆኜ ለማለፍ ካልፈለኩ በቀር፡ አምልኮ ጭፈራችን ነው ወይንስ ሕይወታችን? አካሄዳችን ወዴት ነው? ምን እያደረግን ነው? በእኛና በዚያኛው (በዓለማዊው) ሰፈር ያለው ልዩነት ምን መሆን አለበት?

የመገናኛ ብዙኃን (Social network) በሰፊው ግልጋሎት ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮ እየጨመረ እያደጉ ያሉ ብዙ ጠቃሚ አስተማሪና ግንዛቤ ሰጪ ነገሮች ማግኘት ችለናል። ይሄ እውነት ሆኖ እያለ ግን በዛው መጠን የሚጎዱ ነገሮችም የሞሉበት ሁኔታ አለ። በዚህ ሃሳብ እያለን የምንገለገልበት የዩቱብም ሆነ የፌስ ቡክ ገጾች የሚያስተላልፉት መልእክት ለአድማጫቸው የሚደርሱት የታሰበውንም ሆነ ይልተጠበቀ ውጤት የሚያመጡ ናቸው። 

   እንደ ክርስቲያንነቴ (ወንጌላዊ አማኝ) እንደመሆኔ በወንጌላዊ አማኞች መካከል “አምልኮ” እየተባለ የሚሆነው ነገር እጅጉን እያሳሰበኝ፡ ከመጣ ሰንብቷል። አምልኮ የሚለው ሃሳብ ከስሜት ያልተለየ የሆነ ይመስላል  (ምንም እንኳ አምልኮ ያለ ስሜት ባይሆንም)። ጭፈራ እና ማምለክ ልዩነቱ ብዙ በማይታይበት አንዳንዴ እግዚአብሔርን ለማክበር የተሰበሰበ ጉባኤ ሳይሆን ጥሩ የሆነ ዳንኪራ የሚረገጥበት ቤት እስኪመስል ዘማሪው (አስመላኪው) አምላኪው የሚሆኑትንም የሚያደርጉትንም ለማን? እና ለምን? እንደሚያደርጉት በማይለዩበት መልኩ ሲዘሉ እናያለን። ይሄንን የታዘቡ ብዙዎች አሉ ብዬ እላለሁ ከአንዳንድ አስተያየቶችም እንደሚነበበው ወንጌላውያን አማኞችም ሆኑ ወንጌላውያን አማኝ ያልሆንኑት የሚሉት በርካታ ነገሮች አሉ። የአንዳንዶች ሁኔታ በሚታዩ የተለያዩ “የአምልኮ” ተብለው የተሰየሙ የቪድዮ ክሊፕ ግር ያሰኛል፡ መዘምር አይሉት መዝፈን ውዝዋዜ አይሉት አክብሮት ያሰቅቃል፡ ያሳፍራል፡ በተለይ አንባቢዎቼ እንዲረዱልኝ፡የምፈልገው የሃይማኖተኝነት ወግ ይዞኝ፡አይደለም ነገሩ አሳስቦኝ፡ነው። ወዴት እየሄድን ነው?  

 “የማታመልክ ቤተ ክርስቲያን በመዝናኛ መያዝ አለባት። ቤተ ክርስቲያንን ወደ አምልኮ የማይመሩ መሪዎች መዝናኛን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።” ኤ ደብሊው ቶዘር A. W. Tozer

ተመልካች አለን ተመልካቾቻችን አይምሮ ያላቸው ማገናዘብ የሚችሉ ናቸው። ክርስትናችን በውስጥ (አማኞች)፡ በውጭ ደግሞ የማያምኑት የሚያዩት ነገር ያለበት ሕይወት ነው። ለዚህም ነው ኢየሱስ “እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።” (ማቴ 5:16)   “ብዙ ፍሬ በማፍራት ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብትገልጡ በዚህ አባቴ ይከብራል።” ዮሐ 15:8 ብሎ የተናገረው።

       በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ የምናደርገውንም ሆነ የምንኖረውን ኑሮ “ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” (1 ቆሮ 10:31) እንደሚል ምንም እንኩዋን ነጻነት ያለን ሰዎች ብንሆንም ነጻነታችን ግን ልቅነት እንዳልሆነ ልናስተውል ይገባል “ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር አይጠቅምም…” (1 ቆሮ 6:12) በጸጋው የምንኖር ሰዎች መሆናችን ባይዘነጋም ጸጋው ግን ልቅም አይደለም ሕግም አይደለም የራሱ መጠን አለው በአንዱ ጫፍ የምናጠብቀ ወይም በሌላኛው ጫፍ የምናላላው እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል ባይነኝ። 

             በዘመናችን ያሉ እውቅና ያገኙ የአሕዛብ ልማድ፡ ባሕሎች ቤተ ክርስቲያንን ዘልቀው እየገቡ ይገኛሉ (Pop-culture) እንለያቸው (Distinguish) እንለያያቸው (Separate) የእግዚአብሔርን እውነት ዓለማዊ ቀሚስ አልብሰን በማቅረብ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ መሞከር ካህን የነበረው አሮን ሕዝቡ ባቀረበለት ጥያቄ መሰረት እንዲመለክ የሰራውን ጥጃ እንደማቅረብ ይታያል ብዬ እፈራለሁ፡ (ዘፀ 32:5-6) ከግብጽ የወጣው የእስራኤል ሕዝብ በለመደው መልኩ (በምርኮ ምድር እንደተለማመደው) በልቡ የነበረውን አምላክ ብሎ ለሚለው ሲሰዋ የምናይበት ታሪክ ነው የዚህ ታሪክ ፍጻሜ እጅግ አሳዛኝ፡ እንደነበረ ከታሪኩ ማስተዋል እንችላለን።

 ስሜታዊነት (ሁሉንም ባይሆን) ነገር ግን ጎልቶ በሚታይ መልኩ ወጣቶቻችንን የተጠናወተ ይመስላል (እድሜዬ በወጣቱ ክልል እንዳለ ይታወቅልኝ) በእግዚአብሔር ማንነት ያልተ ገራ ያልተያዘ አይምሮ እና ማንነት ለአጓጉል ስሜታዊነት ያጋልጠናል አጓጉል ስሜታዊነት ወደ አጓጉል ስህተተኛነት ይወስደናል፡ በእኛና በዚያኛው ሰፈር (ዓለማዊነት) መካከል መስመር አለ ይሄ መስመር ደምቆ መሰመር አለበት ባይ ነኝ፡ ዳዊት እርቃኑን በእግዚአብሔር ፊት ዘምሮአልና እኛን ማን ይከለክለናል? ባይ እንደማይጠፋ እርግጠኛ ነኝ። ዳዊት እርቃኑን መዘመሩ ሳይሆን ልቡም የሚያመልክ የነበረ ሰው መሆኑ ከውድቀቱም እንኳ የምንማራቸው ነገሮች አሉ (መዝ 51) ሕይወት አምልኮ ነው! እንጂ ዝማሬ ወይም ኅይማኖታዊ ተግባራቶቻችን በራሳቸው ሙሉ አምልኮ መሆን አይችሉም።  

ይህንን ሁሉ ማለትህ ጥሩ ነው ታዲያ ምን ይሁን ሒስ ብቻ ነው? ወይንስ መፍትሄ አለህ ወይ? ለሚሉ ይሄንን ለመሰንዘር እሞክራለሁ።

አምልኮ እና መዝናኛን (Entertainment) መለየት

“የማታመልክ ቤተ ክርስቲያን በመዝናኛ መያዝ አለባት። ቤተ ክርስቲያንን ወደ አምልኮ የማይመሩ መሪዎች መዝናኛን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።” ኤ ደብሊው ቶዘር A. W. Tozer

      አምልኮ የሆነ ተግባር አይደለም ነገር ግን ማንነት እንጂ።

       ባለንበት ዘመን አምልኮአችንን ይዘቱን ልንፈትሽ ከዛም ባለፈ መልኩ ትኩረትልንሰጠው ይገባል እላለሁ ምክንያቱም ትኩረት ካልሰጠነው በቆይታ መጽሐፍቅዱሳዊ መልኩን ይለቅብናልና ነው። አሁንም ቢሆን ያለው ልምምድ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አምልኮ ያማከለ ለመሆኑ ምን ያህሎቻችን እርግጠኞች ነን? በመድረኮቻችን የሚንጸባረቁት የተዋናይና የታዳሚ አይነት ይዘት ያላቸው ልምዶች መታየት ከጀመሩ ሰንበት ያሉ ይመስለኛል። የመድረክ አገልጋዮች ሃላፊነትን ከተቀበሉት አደራ አንጻር ምን እያደረጉ እንደሆነ ተረድተው የሚተገብሩት ጥቂቶች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ጉባኤውን ሞቅ አድርገን መያዝ ነው ለአብዛኞቻችን የሚታየን በጉባኤው ላይ ሙሉ አክብሮትና ሙሉ መገዛት የሚገባውን ጌታ ወደ ጎን አድርገን በሱ ስም እኛው መሟሟቁላይ ነው ትኩረታችን፡፡ ከማልረሳቸው ትዝታዎች መካከል በቤተ ክርስትያን እኔና ሌሎች ወገኖች በምናገለገልበት ፕሮግራም የመምራት ተራው የነበረ አንድ ወንድም ለአገልግሎት ልምምድ ላይ በነበርንበት ሰአት የያዛቸው የአዝማቾች መብዛት ከዛም አልፎ አዝማቾቹ አንድ አይነት የሙዚቃ ቁልፍ እና ሪትም አላቸው እንጂ ያላቸው የመልእክት ይዘት የተለያየ ነበርና አንዲት እህት ምነው? ብትለው የሰጣት መልስ “አየሽ ጉባኤውን ለማግኘት እንዲህ ነው ማድረግ ያለብን። በዚህ ዝማሬ አዝማች እህት እከሊትን በዚህ ዝማሬ አዝማች ደግሞ ወንድም እከሌን በዚህኛው ደግሞ እማማ እክሌን በዚያኛው ደግሞ አባባ እከሌንና ጋሽ እከሌን አገኛቸዋለሁ።” ብሎ እርፍ።

     እንግዲህ እዚህ ላይ ነው የአምልኮአችን ይዘት መዝናኛ ነው? ወይንስ እግዚአብሔርን ማክበሪያ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያለብን።

           በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ በሆነ መልኩ በአንዳንድ የሕይወት ክልላችን ላይ  በዚህ መልኩ ቢሆን ወይንም በዚያ መልኩ የሚል ቀጥተኛ ትእዛዝ ባይሰጠንም: እንደሚባለው አንዳንድ ግራጫማ የሆኑ ክልሎች አሉ፡ እንዴት እናስተናግዳቸው? ምንድን ነው መመዘኛቸው? 

         ነገር ግን በጉባኤም ሆነ በግል አምልኮአችን ልንከተለው የሚገባ መርህ ይሰጠናል፡ ጳውሎስ ይሄንን በፊሊጵስዩስ መልእክቱ “በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ እውነት የሆነውን ሁሉ ክቡር የሆነውን ሁሉ ትክክል የሆነውን ሁሉ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ መልካም የሆነውን ሁሉ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደነዚህ ስላሉ ነገሮች አስቡ።” (ፊሊ 4:8) ይለናል።

  • የነገር መመዘኛችን “እውነት የሆነው ነው “እውነት ለሁሉም አይመችም ብዙዎች አይስማሙበትም ከብዙሃኑጋ ሳይሆን ከማይለወጠው እውነት እሱም ከቃሉ ጋር። ኢየሱስ በዮሐንስ ወንጌል (7:18) እውነተኛነት የሚለካው ስለ እኛ ወይም ስለምን ቀበልው ክብርና ማንነት ሳይሆን የተላክንበትን በመፈጸም የላኪውን ሥራ ስንሠራ እንደሆነ ይናገራል፡ እውነት በእኛና በምናመልከው አምላክ (ዮሐ 8:34)፣ በምንኖርበት ዓለም (ኤፌ 5:9) ፣ ጠላትን በምንዋጋበት ጊዜ (ኤፌ 6:14) በዚህ ሁሉ ወሳኝ፡ነው ስለዚህ የነገር መለኪያው እውነት እንደ ቃሉ እንጂ እነደ ሁኔታዎች እንደ ብዙኃኑ መሆን የለበትም። “ቃልህ እውነት ነው በእውነትህ ቀድሳቸው፡” (ዮሐ 17:17) ይሄ እውነት የሚያደርገን ለእግዚአብሔር እንድንለይ የእርሱ እንድን ሆን ያደርገናል፤ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህር በዚህ ክፍል የተናገርው ነገር አለ እሱም ሰዎች ባለንበት ዘመን “እውነት ይሆን?” ብለው አይጠይቁም ነገር ግን “ይሰራልኛል ወይ?” እና “ምን ስሜት ይፈጥርልኛል?” የሚለው ነው። ነገር ግን ስሜታችን የሚመቸውን ሳይሆን በእውነተኛ ቃሉ አማካኝነት ልናስተናግደው የሚገባ መሆን አለበት ወይም ልምምዳችን በቃሉ መፈተሽ አለበት እንጂ በሌላ አባባል ልምምዳችን ቃሉን አያረጋግጥልንም ቃሉ ግን ልምምዳችንን ያረጋግጥልናል።
  •  የነገሮች መመዘኛ ክቡር የሆነውን” በሌላ አባባል ሊከበር የሚገባው ልከነቱ ርካሽ ያልሆነ ክቡር ባልሆነ ነገር ላይ አይምሮአችንን አናስይዝም ምድራዊ የሚያልፍ በእግዚአብሔር ፊት ስፍራ የሌለው ማንኛውም ነገር “ዜግነታችን ሰማያዊ ስለሆነ” (ፊሊ 3:20) ሃሳባችንም በሰማያዊው መመዘኛ የተለካ መሆን አለበት፡ ዘላቂነት የሌለው ቢሆን እንኳ ራሳችንን መጠየቅ ያለብን “ለጥቂት ይጠቅማልና፡” (1 ጢሞ 4:8) ጳውሎስ እንዳለውና በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለው ወይ? ለዘላለማዊው መንደርደሪያ ይሆናል ወይ?  ዘላለማዊውን ታሳቢ ያደረገ ዋጋ አለው ወይ? ምንም አይደለም ተብሎ የሚታለፍ ጥቂት የሚል ነገር በክርስትና ስለሌለ የተከበረ ነገር ማለት የተከበረ ነው። ምን አደረግን? ሳይሆን ለምንድን ነው የምናደርገው? ለስሜታችን ሳይሆን ለመንፈሳችን ለተቀበልነው ላመንነው እውነት የተከበረ መሆኑ የምናሳይበት ነው መሆን ያለበት። ክቡር የምንለው “ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ” (ፊሊ 2:4) ራሳችንን ያማከለ መሆን የለበትም።
  • የነገሮች መመዘኛ “ትክክል የሆነውን ሁሉ”  የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ”ትክክል” የሚለው ቃል “ጽድቅ” ከሚለውጋ እንደሚዛመድ ያስረዳሉ። ትክክልን ማየት ያለብን በእግዚአብሔር የቅድስና መስፈርት የሚመጥን ሲሆን ትክክል እንለዋለን። “ትክክለኛውንና ቀና የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰዎቹን እንዲያዝ መርጨዋለሁ፡” (ዘፍ 18:19) በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ  የሆነ ፍትህ ያልተጓደለበት (መዝ 82:2) በእግዚአብሔር ፊት ሚዛኑ ያልተጭበርበረ መለኪያው ትክክል የሆነ (ምሳ 11:1 ፣ 16:11) ይህ ትክክለኛነት በእግዚአብሔር በእርሱ የሚመራ ነው፡ (ኢሳ 26:7) ፈሪሳውያን ራሳቸውን ትክክል እንደ ነበሩ ይቆጥሩ ነበር ነገር ግን በመለኪያው ሲታይ አልነበሩም (ሉቃ 18:9-14) ልንኖረው ልንከተለው የሚገባን የትክክል መስፈርቱ እኛ አይደለንም በአጠቃላይ መብታችንን የምናስከብርበትን ሳይሆን ለትክክለኛው ነገር መብታችንን የምንተውበትነ ነው የሚናገረው (ሮሜ 14:13-17)።
  • የነገሮች መለኪያ “ንጹሕ የሆነውን ሁሉ” ሞራላዊ ንጽሕና ምንም አይነት ክፋት (ነውር) የሌለበት ሰውነታችንን የማያረክስ በውስጥ ማንነታችንም በውጭውም እንደ ጢሞቴዎስ ለሚያዩን “በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።” (1 ጢሞ 4:142) ደግሞም ያዕቆብ “በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕና ነውር የሌለበት” (1:27) እንደሚናገር በኤፌሶን 5:3 “በመካከላችሁ ከቶ አይነሳ” ብሎ እንደሚላቸው ይሄ ንጽሕና በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው በተለይ (በፊሊ 1:17) ክርስቶስን ሲሰብኩ በንጽሕና እንዳልነበር እንደሚናገር የራስን ጥቅም ወይም ስውር ሃሳብ ያላነገበ ሆኖ የሚገኝ የእኔነት እርሾ የሌለበት (ማቴ 6:1-2 ፣ 1ቆሮ 5:6 ፣ገላ 5:9)
  • የነገሮች መለኪያ “ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ” እንደ አማኝነታችን ተቀባይነት ያለውን ከውስጥ፡ መነሻ ሃሳቡም ሆነ ለሌሎች ስናደርገው አስደሳች ሆኖ ሲገኝ፡ (በ 1ቆሮ 13፡ 4-7) ባለው መርህ ላይ የተመሰረተ ከላይ ካነሳነው እውነት ጋር የሚሄድ። ይህ ተወዳጅ የምንለው ርህራሄ ያለው ለሌሎች አሳቢ የሆነ፡ ይሄ ተወዳጅ የሆነው ጽድቅ የሞላበትን ሰላም ያመጣል ወይ?
  • የነገሮች መለኪያ “መልካም የሆነውን ሁሉ” ይሄን አይነቱ መልካምነተ በሌሎች ዘንድ እግዚአብሔርን ባስቀደመ መልኩ በእኛ ሲገለጥ፡የሚከበር ስፍራ የሚሰጠው፡ ነው። ሲደመጥም የሚወደድ በጨው እንደ ተቀመመ እንደሚል፡

“በጎነት ቢሆን ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉ ነገሮች አስቡ”። እንግዲህ በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር ክብር ሊሆን የሚገባው “እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን  ሁሉ አስቡ።” ብሎ ስለሚል ለየትኛውም ነገር መነሻ መስፈርት ይሆነናል በመንፈሳዊው ይሁን ምድራዊው፤ ምንም እንኳ “በእናንተም ሆነ በሰዎች የፍርድ ሸንጎ ቢፈረድብኝ፡ እኔ በበኩሌ ግድ የለኝም…በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ነው።” (1ቆ 4:3, 4) ብሎ ጳውሎስ ቢናገርም በሌላ ቦታ ግን በተቀበለው ሃላፊነት አንጻር “በዚህ በምናከናውነው የቸርነት ሥራ አንዳች ነቀፋ እንዳይገኝብን እንጠነቀቃለን። ምክንያቱም ዓላማችን በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን በሰውም ፊት መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ነው።” (2ቆሮ 8:20-21)  

ፍርድ አይደለም ተጠያቂነትና ኅላፊነት ነው!

እንደ ክርስቲያን ነገሮች እየተጠቀምንባቸው ነው? ወይንስ ነገሮች እኛን እየተጠቀሙብን ነው? ለየትኛውም እርምጃችን ምላሽ እንሰጥበታለንመልካምም ሆነ ክፉ፡ የትኛውም እርምጃችን በልባችን ካለ እውነተኛ ንጽህና የመነጨመሆን አለበት ራስወዳድነት የሌለበት (እኔን ይመቸኝ፡እንጂ ስጋ መብላቴ ማንም አያገባውም) በሚልመንፈስ ሳይሆን ለወንድማችን መልካምነት እና ለእግዚአብሔር ክብር መዋል አለበት።

“ታዲያ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? ለምንስ ወንድምህን ትንቃለህ? ሁላችንም በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት እንቀርባለንና… ስለዚ እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ፊትመልስ እንሰጣለን።” (ሮሜ 14:10ና 12)    

The post ማምለክ ወይንስ ማድመቅ? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ሰው ሰራሽ ደመና https://deqemezmur.com/2020/06/28/prepare-yourself-for-studio-recording-sessions/ Sun, 28 Jun 2020 17:27:37 +0000 https://demo.mekshq.com/voice/?p=171 የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊ አሳየኸኝ ለገሰ ነው፤ ጽሁፉ የተገኘው ከፌስቡክ ገጹ ነው፤  አንዳንድ የዘመናችን “ቤተ ክርስቲያናት” በአምልኮ ሰዓት (በልዩ ልዩ ክዋኔዎች) ለታዳሚው “አስደሳች ድባብ” ለመፍጠር የሚኼዱበት ርቀት አስደንጋጭ እየሆነ መጥቷል፡፡ የመድረክ አገልግሎቶች የገበያ ፍልስፍና (marketing philosophy) የሚከተሉ ይመስላሉ፡፡ የደንበኞችን ፍላጎት በማጥናት ተፈላጊውን ምርት እንደሚያቀርብ አምራች፣ ጆሮን የሚያሳክክ ትምህርትና ስሜትን የሚኮረኩር ሸቀጥ ሁሉ መድረኩ ላይ መሰጣት ከጀመረ […]

The post ሰው ሰራሽ ደመና first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊ አሳየኸኝ ለገሰ ነው፤ ጽሁፉ የተገኘው ከፌስቡክ ገጹ ነው፤ 

አንዳንድ የዘመናችን “ቤተ ክርስቲያናት” በአምልኮ ሰዓት (በልዩ ልዩ ክዋኔዎች) ለታዳሚው “አስደሳች ድባብ” ለመፍጠር የሚኼዱበት ርቀት አስደንጋጭ እየሆነ መጥቷል፡፡ የመድረክ አገልግሎቶች የገበያ ፍልስፍና (marketing philosophy) የሚከተሉ ይመስላሉ፡፡ የደንበኞችን ፍላጎት በማጥናት ተፈላጊውን ምርት እንደሚያቀርብ አምራች፣ ጆሮን የሚያሳክክ ትምህርትና ስሜትን የሚኮረኩር ሸቀጥ ሁሉ መድረኩ ላይ መሰጣት ከጀመረ ቆየ፡፡

ስብከቱ በአዎንታዊ ሐሳቦች የተሞላ፣ ለአድማጩ ጊዜያዊ ስሜት የሚጨነቅ፣ ቀላልና ዘና የሚያደርግ ሲሆን፤ የሚያስተምር፣ የሚወቅስ፣ የሚገስጽና የሚያቀና ጠንካራ ትምህርት ከብዙ ምስባኮች ተሰድዷል፡፡ ስለ ኀጢአት፣ ስለ ፍርድ፣ ስለ ሕይወት ንጽሕና፣ ስለ ንስሐ፣ ስለ ወንድማማች መዋደድ፣ ስለ ጌታ ምጽአት አይነሳም፡፡ ትምህርቶች፣ ለአድማጭ እንዳይጎረብጡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይዘታቸው ሳስቶ ሥነ ልቡናዊና አነቃቂ ይደረጋሉ፡፡

አምልኮ እየተባለ የሚከወነውም ድርጊት እንዲሁ ነው፡፡ መዝሙሮች ከመልዕክት አዘልነት ይልቅ ምዕመናንን ለማውረግረግ የሚጨነቁ፣ በተራ ቀረርቶና በባዶ ተስፋ ታዳሚን ማስፈንጠዝን ግባቸው ያደረጉ ሆነዋል፡፡ የጥሩ ‹‹አስመላኪ›› መለኪያው ‘ሕዝቡን ምን ያህል አንቀሳቀሰ? ድምጹና ደንሶ የማስደነስ ችሎታው ምን ይመስላል?’ የሚል የሆነ ይመስላል፡፡ መልዕክት አልባውን ጩኸት የሚያጅበው ሙዚቃ፣ የሚብረቀረቁ የመድረክ መብራቶችና ከጀርባ የሚለቀቀው ባዕድ ጭስ፣ ተመልካችን በስሜት የሚያጦዝ ድባብ ይፈጥራሉ፡፡ ከሁሉ የከፋው ነገር፣ ይህ ሰው ሰራሽ ድባብ “የእግዚአብሔር ሕልውና” እየተባለ መጠራቱ ነው፡፡ (ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደ ሐገረ አሜሪካ ተጉዞ የተመለሰ አገልጋይ፣ በዚያ ስላያቸው አንዳንድ ቤተ ክርስቲያናት ሲናገር፣ “የመንፈስ ቅዱስ ደመና ጠፍቶባቸው፣ አርቴፊሻል ደመና ፈጥረው ከመድረክ ያቦንናሉ” ብሎ የተናገረው ትዝ ይለኛል፡፡)

በኮምፒዩተር ቴክኖሉጂ “user friendly” የሚባል የተለመደ ቃል አለ፡፡ ለተጠቃሚ የሚቀርቡ ሶፍተዌሮችና ፕሮግራሞች ለተጠቃሚው የማይከብዱና ያልተወሳሰቡ እንዲሆኑ አደርጎ ማቅረብ ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎትም እንዲሁ user friendly እየሆነ መጥቷል፡፡ አይደን ቆዘር የተባሉ መጋቢ (ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት) በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያናት ላይ የተመለከቱትን ለውጥ አስመልክቶ፣ “ተዝናኖት (ወይም Entertainment) የወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያናትን እያጠቃ ያለ እጅግ የከፋ ኑፋቄ ነው! ተዝናኖት ራሱ እውነተኛውን አምልኮ የተካ ‘ሌላ አምልኮ’ ሆኗል” ብለው ነበር፡፡ የዘመናችንን ቤተ ክርስቲያን በትኩረት የታዘቡት ፌሚ አደለይ የተባሉ ጸሐፊም እንዲሁ፣ “ፈንጠዚያ ከመውደዳችን የተነሳ የእኛ ዘመን ቤተክርስቲያን ከ”ታላቁ ተልዕኮ ወደ ታላቁ ተዝናኖት” (from Great Commission to Great Entertainment) እየተሸጋገረች ይመስለኛል” ብለዋል፡፡

የገበያ ሕጉ፣ `ሰዎች ምን ያስፈልጋቸዋል` ከሚለው ይልቅ `ሰዎች ምን ይፈልጋሉ` የሚለው ላይ አተኩሩዋል፡፡ የታዳሚ ስሜት ላይ የቆመ “ተጠቃሚ ተኮር (consumer-oriented)” አገልግሎትም ተፈጥሯል፡፡ እግዚአብሔር ራሱም፣ “ዓላማችን የደንበኞች እርካታ ነው” የሚል ጥቅስ ለጥፎ፣ ‹‹ተደሰቱልኝ፣ ተዝናኑልኝ›› እያለ እንደሚያስተናግድ አስተናጋጅ የፍላጎታችን አገልጋይ ተደርጎ ተስሏል፡፡ በዚህም ሳቢያ፣ ብዙ ምስባኮች የወደቀውን ሰው የልዕልና መሻት እና ‹ኤጎ› እያከኩ አዳምን በሚቀልቡ ተናጋሪዎች ተሞልተዋል፡፡ ኮምጨጭ ያለው የቃል እውነት የሚነገርባቸው አዳራሾች ባዶ እየሆኑ፣ ጊዜው በጠየቀው የገበያ ስልት የሚመሩት ደግሞ ጠጠር መጣያ እያጡ ነው፡፡

አንዳንዶች ይህን አስነዋሪ ድርጊታቸውን፣ “ወጣቱንና አማኝ ያልሆነውን ማኅበረሰብ በአውዱ ለማግኘት የሚደረግ ነው” በማለት ለማመናፈስ ይጥራሉ፤ “በሁሉ እነርሱን መሰልኩ” የሚለውን የጳውሎስን ቃል ዋቢ አድርገውም ይጠቅሳሉ፡፡ ይህ ጳውሎስንም ሆነ ቃሉን ጠንቅቆ አለማወቅ ነው፡፡ ጳውሎስ ሰውን ለማስደሰት መልዕክቱን የሚያቀጥን የመድረክ አጫዋች አልነበረም፡፡ ዓለምን ለማዳን እንደ ዓለም መሆንን አልሰበከም፡፡ የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን፣ ዓለም የራሷ የሆኑትን ለመሳብ የምትጠቀማቸውን ዘዴዎች ኮርጃ መጠቀሟ የክፍለ ዘመናችን ታላቅ መንፈሳዊ ቅሌት ይመስለኛል፡፡

ትውልዱ የሚያስፈልገው ይህ አልነበረም፤ ስጋዊ አፒታይቱን የሚያረካ ኀይማኖታዊ ተዝናኖት ወደ ክርስቶስ አያቀርበውም! በዳንኪራ የዳነ፣ የኮሜዲ ምሽት በመሰሉ ስብከቶች የተለወጠና በአነቃቂ ዲስኩሮች ያደገ ክርስቲያን አላየንም፡፡ የሚያስፈልገን ወደ እግዚአብሔርና ወደ ቃሉ የሚመልሰን ጥልቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርትና ክርስቶስንና ወንጌሉን የሚያልቅ አምልኮና አገልግሎት ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አጥሯ ፈርሶ የዓለም ኮተት ሁሉ ማራገፊያ እንዳትሆን መከላከል ይገባናል፡፡ ከተያያዝነው አደገኛ ቁልቁለት የሚመልሱንን እውነተኛ እረኞች እግዚአብሔር ይስጠን፡፡ መልካም ቀን!

 

The post ሰው ሰራሽ ደመና first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ደስ ያለው ይዘምር ወይስ ካሴት ያውጣ? https://deqemezmur.com/2014/10/01/%e1%8b%b0%e1%88%b5-%e1%8b%ab%e1%88%88%e1%8b%8d-%e1%8b%ad%e1%8b%98%e1%88%9d%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%88%b5-%e1%8a%ab%e1%88%b4%e1%89%b5-%e1%8b%ab%e1%8b%8d%e1%8c%a3-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d/ Wed, 01 Oct 2014 23:35:55 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2038 ይሄ ጽሁፍ በጳውሎስ በፈቃዱ የተጻፈ ነው። በጸሃፊው ፈቃድ በደ ቀመዝሙር ብሎግ ላይ ቀርቧል። ከጳውሎስ ፈቃዱ ከሁለት ዘማሪዎች ጋር ወደ አዋሳ እየሄድኩ ነው (በእናታችሁ ሥማቸውን አትጠይቁኝ)። እዚያ ስንደርስ ሌላ ሦስተኛ ዘማሪ አገኘን። ይህ ዘማሪ ከእኔ ጋር ካሉ ዘማሪዎች ለአንዱ የሚሆን መዝሙር አዘጋጅቷል። ግጥሙን ካስጻፋቸው በኋላ ዜማውን ለማስለመድ ሲጀምረው ቁጭ ዘፈን ይመስላል። አብረውኝ የነበሩ ዘማሪዎችም ይህንን አውቀዋል። […]

The post ደስ ያለው ይዘምር ወይስ ካሴት ያውጣ? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ይሄ ጽሁፍ በጳውሎስ በፈቃዱ የተጻፈ ነው። በጸሃፊው ፈቃድ በደ ቀመዝሙር ብሎግ ላይ ቀርቧል።
ከጳውሎስ ፈቃዱ

guitar3-642x336ከሁለት ዘማሪዎች ጋር ወደ አዋሳ እየሄድኩ ነው (በእናታችሁ ሥማቸውን አትጠይቁኝ)። እዚያ ስንደርስ ሌላ ሦስተኛ ዘማሪ አገኘን። ይህ ዘማሪ ከእኔ ጋር ካሉ ዘማሪዎች ለአንዱ የሚሆን መዝሙር አዘጋጅቷል። ግጥሙን ካስጻፋቸው በኋላ ዜማውን ለማስለመድ ሲጀምረው ቁጭ ዘፈን ይመስላል። አብረውኝ የነበሩ ዘማሪዎችም ይህንን አውቀዋል። “ይህማ የእገሌን ዘፈን ይመስላል” አለ አንደኛው የዘፋኙን ስም ጠቅሶ። ያኛውም ለማስተባበል አልሞከረም። “አዎ ከዚህኛው ዘፈኑ ላይ ነው የወሰድኩት” በማለት ዘፈኑን ማንጎራጎር ጀመረ። ከእኔ ጋር ከሄዱት ዘማሪዎች አንዱ ቀጠል አድርጎ “እኔም እኮ ከዚያኛው ዘፈኑ ላይ ወስጃለሁ” በማለት የሆነ መዝሙር በፉጨት አሰማን። እኔ በድንጋጤ እንደ ጅብራ ከተገተርኩበት ስፍራ በዕፍረት ጉንዳን አክያለሁ ሆኖም ከምንም አልቆጠሩኝም። ዘማሪዎቻችን ግጥም እነ ኤፍሬም ታምሩ ደግሞ ዜማ በመስጠት እንደሚያገለግሉን ግን ከዚያን ቀን ጀምሮ ማወቅ ችያለሁ።

አሁን አሁንማ በአንድ የመዝሙር ካሴት ላይ ሰባትና ስምንት የዘፈን ዜማዎችን ወደ መስማት «አድገናል»።

ይህ ከሆነ ስድስት ዓመት አልፎታል። እኔም ብዙዎቹን ዘማሪዎች ለማናገርና ለመምከር ሞክሬያለሁ። ግና ጥቂት የማይባሉ ዘማሪዎች ከዚህ ዓመላቸው ፍቀቅ ማለት አልሆነላቸውም። አሁን አሁንማ በአንድ የመዝሙር ካሴት ላይ ሰባትና ስምንት የዘፈን ዜማዎችን ወደ መስማት «አድገናል»። ለመገሠጽ ሲሞከርም “በመዝሙሮቹ ተባርከንባቸዋል ለምን ትነኳቸዋላችሁ?” በማለት የሚቆጡ ከየአካባቢው ብቅ ይላሉ። የእነሱን የ«ተባርኬያለሁ» ስሜት የትክክለኛ መለኪይ ያደረገው ማን ነው? የአንድ ሰው ስም ከተጠቀሰም «ያጠፋው እሱ ብቻ አይደለም ስለዚህ እርሱ ተለይቶ ለምን ይወቀሳል?» የሚል አመክንዮታዊነት የጎደለው ተቃውሞ ይደመጣል። ኧረ ለመሆኑ ይህ ሁሉ ጥፋት ሲፈጸም የት ነበሩ? ምናልባት በእንቁላሉ ሥርቆት ጊዜ ማጨብጨባቸውን አቁመው ቢገሥጿቸው ኖሮ ከብዙ ዕፍረት ባተረፉን ነበር!

ይህንን ሁሉ የማቀርበው ግን ጠላቶቼን የማብዛትና እንጀራዬን የማጥፋት ሞኝነት ይዞኝ ወይም ብሽሽቅ አምሮኝ አይደለም። ትውልዱን የማቅናት የባለአደራነት ድርሻዬን ለመወጣት በማሰብ ብቻ ነው።

ሆን ብለው ከዘፈን ዜማ የሚወስዱ ዘማሪወችን አውቃለሁ። ጥቂቶችንም አነጋግሬአለሁ። “ዜማ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው ለሰይጣን ማን ሰጠው? ስለዚህ እንደ ፈለግን መውሰድ እንችላለን” ይላሉ። በዚሁ ከቀጠሉ በዜማ ስርቆት ተከሠው አንድ ቀን ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ እሰጋለሁ። «የዘፈን ዜማ ስንጠቀም የማያውቀውን መልእክት በሚያውቀው ዜማ ለሰይጣን እያቀረብንለት ነው» የሚሉም አሉ («ወደው አይሥቁ!» ይላል ያገሬ ሰው)። በእነርሱ ቤት ሰይጣን እንደ ሕንድ ፊልም «የሌቦች አለቃ» መሆኑ ነው። እንዲህ ከተቻለማ መዝሙር እንዲሆኑልን የምንፈልጋቸው ብዙ «ምርጥ ምርጥ» ዘፈኖች ስላሉ ከሆነ አይቀር አንደኛውኑ ጥቆማ ብንጀምር ይሻለናል። እኔ በበኩሌ «የነገን ማወቅ ፈለግሁ» የሚለውን ዘፈን መርጫለሁ።

«የዘፈን ዜማ ስንጠቀም የማያውቀውን መልእክት በሚያውቀው ዜማ ለሰይጣን እያቀረብንለት ነው» የሚሉም አሉ («ወደው አይሥቁ!» ይላል ያገሬ ሰው)። በእነርሱ ቤት ሰይጣን እንደ ሕንድ ፊልም «የሌቦች አለቃ» መሆኑ ነው።

ዜማ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው እንዴ? ክርክሩ ውሃ አያነሣም። ከቴአትር ቤትና ከዘፈኑ ዓለም አካባቢ የመጡ ሰዎችም ይህን አይነግሩንም። አንዳንዶቹ የዘፈን ዜማዎች ጫት በመቃም ሌሎቹ ደግሞ ሰይጣንን በመለማመን የሚደረሱ ናቸው። በርካቶቹ ዘፋኞች ውሎአቸው ጠንቋይ ቤት እንደ ሆነ በቅርቡ በኢትዮጵያ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲገለጽ ከነበረው የአንድ ጠንቋይ ገድል ተረድተናል።ከዘፈን ደራሲዎች መካከል አንደኛው ሲጸለይበት በውስጡ የነበረው ርኩስ መንፈስ «ዜማና ግጥም የምንሰጠው እኛ ነን» ይል ነበር። «ሳብ በለው የሃሙስ ፈረስ» የሚል ዘፈን አለ አይደል? «የሀሙስ ፈረስ» ማን ይመስላችኋል? «የበረሀው ዐውሎ ነፋስ» የሚል ዘፈንም አለ። ይሄስ ማነው? ነውር የሚተላለፍባቸው አሳፋሪ ዘፈኖች ከመብዛታቸው የተነሣ «በስምንተኛው ሺህ ዘፋኝ ይበዛል’ የሚል ንግርት አለ» እያሉ የሚያሾፉ የትምህርት ቤት ጓደኞች አሉኝ። እውን ዜማ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነውን?

ለመሆኑ የዘፈን ዜማ መዋስ የደረሱት አዲስ ዜማ መፍጠር አቅቷቸው ነው ወይ? መጽሐፍ ቅዱስም ቢሆን “ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ ዘምሩ” (መዝ 96:1 ፣ 40:3 -አ.ም.ት) በማለት በግልጽ ይናገራል። መንፈስ ቅዱስን የት አድርገነው ነው? ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነው እግዚአብሔር ብንጠይቀው በልግስና የማይሰጠን ይመስል ቅልውጥና ምን ወሰደን?
በፊት የመዝሙር ዜማ የሚወስዱ ዘፋኞች ነበር የሚበዙት ምክንያቱም መዝሙሮቻችን በዘፋኞች ዘንድ ተሰሚነት ነበራቸው። አሁን ደግሞ በዚያው መጠን የእነርሱ ዘፈን የእኛን ዘማሪዎች ቀልብ ሰርቋል። ይህም የእኛ ዘማሪዎች የዘፈንን ዜማ በመስረቅ መታማት እንዲጀምሩ አደረገ።

በፊት የመዝሙር ዜማ የሚወስዱ ዘፋኞች ነበር የሚበዙት ምክንያቱም መዝሙሮቻችን በዘፋኞች ዘንድ ተሰሚነት ነበራቸው። አሁን ደግሞ በዚያው መጠን የእነርሱ ዘፈን የእኛን ዘማሪዎች ቀልብ ሰርቋል። ይህም የእኛ ዘማሪዎች የዘፈንን ዜማ በመስረቅ መታማት እንዲጀምሩ አደረገ።

ዘፈን በመዝሙር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከልክ እያለፈ ነው። ቴዲ አፍሮ የተነሣውን ዓይነት ፎቶ ተነስቶ ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ፖስተር የሚያዘጋጅ ዘማሪ በቅርቡ ዓይተናል። በነገር ሁሉ እሱን መምሰል የሚያምራቸው የእርሱ ደቀ መዛሙርት ከመካከላችን ብቅ ማለት ጀምረዋል። አኮራረጃቸው፣ ስም ሳይቀር እንደሚገለብጥ ቀሽም ኮራጅ ተማሪ ነው። አንዳንድ ዘፋኖች መሃል ዘፋኞች የማቃሰት ድምፅ መቀላቀል ይወዳሉ። መልእክቱ ሰዎችን ለአልጋላይ ጨዋታ ለማነሣሣት ወይም እዚያ ላይ ያሉ ለማስመሰል እንደሚደረግ እገምታለሁ። አስገራሚው ግን አንዳንድ መዝሙሮችም መሃል የሚያቃስቱ ዘማሪዎችን እየሰማን መሆኑ ነው። ምን ማለት እንደሆነ አስተውለውት ይሆን? እንደ ዘፈን “የታለ እጃችሁ? እስቲ ሞቅ አድርጉት ባካችሁ?” የሚሉ ዘማሪዎችም አሉ።

ሆኖም ሁሉም ዘማሪዎች ይህን የሚያደርጉት ሆን ብለው ነው የሚል ጭፍን ግንዛቤ የለኝም። ሳያውቁ የሚሳሳቱ ይኖራሉ። የክልሎችን ሳይጨምር በአዲስ አበባ ብቻ ወደ አራት አካባቢ ኤፍ ኤም ሬዲዮዎች ያሉ ይመስላኛል። ሁሉም ሲሞዝቁ ነው የሚውሉት። ስለዚህ ሰዎች ሻይ ሲጠጡና ታክሲ ሲጠቀሙ ወደዱም ጠሉ ዘፈን ሊሰሙ ይችላሉ። በዘፈን ስሜት ውስጥ፡ሆነው ምዝሙር እንጻፍ ካሉ ደግሞ ይህ የተጠቀጠቁት ዜማ ደግሞ የመዝሙራቸው ዜማ ሆኖ ብቅ ይላል። መዝሙሩ ከዘፈን የተመሳሰለበትን አንድ ዘማሪ ይህንን ጽሁፍ ሳዘጋጅ አናግሬው ነበር። “በጓዳዬ ሆኜ ከእግዚአብሔር የተቀበልኳቸው የመሰሉኝ፡መዝሙሮች ዜማቸው የዘፈን ዜማ ሆኖ እየተገኘ የተውኳቸው ብዙ ናቸው” ብሎኛል። መቼም የችግሩ ስፋት መጣጥፍ ሳይሆን መጽሐፍ ይወጣዋል።

አሁን አሁን ወደ ክልሎች እየወጡ ከአዲስ አበባ ርቀው ጠፍተው ይሆናል እንጂ “ቆርቆሮ ያለው (ያለሽ)” እያሉ የሚዞሩ ትጉ ሠራተኞች በየሰፈራችን አይጠፉም ነበር። የወዳደቁ ብረታ ብረቶች፣ አሮጌ ብልቃጥ፣ አፈር ውስጥ፡የተቀበረ የጫማ ሶል ሁሉ ሲያገኙ ይገዛሉ። እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም። ከየትም የተሰበሰበ ኮልኮሌና ቅራቅንቦ ዜማ ለእርሱ አይቀርብለትም።  የመልእክታቸው ተወራራሽነትማ አስደንጋጭ ነው። አንዱ ዘማሪ የሌላኛውን መዝሙር በሌላ ዜማ ለውሶ ያቀርብልናል። ስለዚህ አዲስ ነገር ከመፍጠር ይልቅ ፍራሽ አዳሽይ መስል አሮጌውን መዝሙር ገረፍ ገረፍ አድርገው ለገበያ ያቀርቡታል። ከተለያዩ መዝሙሮች ተለጣጥፈው የተበጁ ድሪቶ መዝሙሮች በዝተዋልና አዲስ ፈጠራ እያማረን ከቀረ ቆየ።

እግዚአብሔር ግን እንዲህ አይደለም። ከየትም የተሰበሰበ ኮልኮሌና ቅራቅንቦ ዜማ ለእርሱ አይቀርብለትም።  የመልእክታቸው ተወራራሽነትማ አስደንጋጭ ነው። አንዱ ዘማሪ የሌላኛውን መዝሙር በሌላ ዜማ ለውሶ ያቀርብልናል።

“የሞት መልአክ አያስፈራኝም
ተሸሽጌያለሁ አያገኘኝም”።
ይህን መዝሙር ታውቁታላችሁ? ዶ/ር ደረጀ ለልደታ መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የሰጠው ዝማሬ ነው። ካልተሳሳትኩ  20 ዓመት አልፎታል። ይህንን መዝሙር በቁጥር 4 ካሴቷ ላይ ምሕረት ኢተፋ የራሷ አስመስላ ቃል በቃል አቅርባዋለች፤

“የሞት መልአክ አያስፈራኝም
ተሸፍኛለሁ አያገኘኝም” በማለት።

ልዩነቱ “ተሸሽጌያለሁ” የሚለው በ”ተሸፍኛለሁ” መቀየሩ ብቻ ነው።
ሌላ ልጨምርላችሁ። የጌጃ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን “ሀ” መዘምራን በቁጥር 1 ካሴታቸው ላይ
“ጌታ ቀድሞ ተገኝቶበት
ስፍራውን ይዞ ዐርፎበት
እንዴት ይሰጥማል መርከቡ
ምንስ ቢያይል ወጀቡ?” ብለው ዘምረዋል።
እርሷ ደግሞ ከዓመታት በኋላ፣
“ጌታ ኢየሱስ ተኝቶበት
ስፍራውን ሁሉ ተቆጣጥሮት
እንዴት ይሰጥማል መርከቡ
ምንስ ቢያይል ወጀቡ?”

በማለት የካሴት ዘመቻዋን አሐዱ ብላ ጀምራበታለች።
አጋጣሚ ይሆንን? ካልሆነ የሰው መዝሙር ደብተር ውስጥ፡ ምን ልትሰራ ገባች?! አንድ ልጨምርበት

“ጅማሬዬ ላይ ቆሞ ፍጻሜዬን ያየ
ይኼ ነው አምላኬ ከሁሉ የተለየ (ሲሳይ አበበ #2 – 1998)
“ጅማሬዬ ላይ ሆኖ ፍጻሜዬን ያየ
ይሄ ነው የኔ አባት ከሰው ይተለየ” (ምሕረት ኢተፋ ልዩ ዕትም – 1998) አንድ የመጨረሻ ብቻ ታገሡኝ ፤

“የአለ አዋቂዎች ልቦና በሰዎች ተሥፋ ያደርጋል
ግን እግዚአብሔር ብቻ ደኅንነትን ያዘጋጃል።” መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ #4 1984
“ያለ አዋቂዎች ልቦና የሚታየውን ብቻ ያያል
ግን እግዚአብሔር ብቻ መድኅኒትን ያዘጋጃል።” (ምሕረት ኢተፋ ልዩ ዕትም 1998)

“ምህረት ብቻ አይደለችም ይህንን ያደረገችው፤ የእርሷ ስም ብቻ ለምን ይጠቀሳል?” የሚለው የተለመደው ጥያቄ እንዳይነሣ አንድ ሁለት ጣል ላድርግበት።

“የምድረ በዳው ዳዊት ና ውጣ
የዜማ ጊዜ መጣ።
በእሥር ላይ ያለህ ዮሴፍ ና ውጣ
የክብር ዘመን መጣ” (ያሬድ ማሩ #1-1996) ከሚቀጥለው ጋር አስተያዩት። በመካከላቸው የአራት ዓመታት ልዩነት አለ።

“የምድረ በዳው ዳዊት ከጫካው ውጣ
የመንገሥ ዘመን መጣ
ባለ ራዕዩ ዮሴፍ ከግዞት ውጣ የመክበር ዘመን መጣ” (ሰናይት እንግዳ #6 – 2000)።
ሌላም ልጨምርላችሁ፤

«ማደሪያህ በምስጋና ይሞላ
አምላክ የለምና ካንተ ሌላ» (እንዳልካቸው ሐዋዝ #1 – 1992)
ይሄም “Copy Paste” ይመስላል

«ማደሪያህ በምስጋና ይሞላ
አምላክ የለምና ከዓንተ ሌላ» (ኤልያስ ወልዴ # 1 – 2000)።

«ተራው የእኔ ነው የኔ
አምላኬ አለና ከጎኔ» (ደስዬ ወልዴ #2 – 1997) ። ይቺም በሌላኛው ላፍ ተደርጋለች

«ተራው የእኔ ነው የእኔ
አምላኬ አለና ከጎኔ» (ኤፍሬም ዓለሙ #1 – 1998።

በእርግጥ፡በጣም የወደድነው ጆሮአችንን የምንሰጠውና ልባችንን የነካ ነገር ውስጣችን ሊቀር፣ ከዚያም በራሳችን ሥራ ላይ ተጸዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ስለዚህ ከዚህ በፊት የነበረ ነገር ሳይታወቅ በእኛ ሥራ ላይ ሊንጸባርውቅ ይችላል። ግን ልክ አለው። ከዚህ በላይ የዘረዘርናቸውን በሚመለከት «እነዚህ ሁሉ በአጋጣሚ ነው የሆኑት» እንደማትሉ ተስፋ አደርጋለሁ። የዚህ ዐይነት «ምንተፋዎች» ብዙናቸው። ከተፋው ሳያንስ ምንተፋው! ለናሙናነት እነዚህ ይበቁናል። ካነሰ ሌላጊዜ እንጨምርበታለን።

The post ደስ ያለው ይዘምር ወይስ ካሴት ያውጣ? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>