ደቀ መዝሙር - ደቀ መዝሙር https://deqemezmur.com ደቀ መዝሙር መሆን ደቀ መዛሙርት ማድረግ Wed, 16 Nov 2022 16:39:48 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.5.3 https://deqemezmur.com/wp-content/uploads/2022/08/cropped-photo_2022-08-09_18-28-03-32x32.jpg ደቀ መዝሙር - ደቀ መዝሙር https://deqemezmur.com 32 32 ዝነኝነት ወይንስ ታማኝነት? https://deqemezmur.com/2022/10/16/celebrity-or-loyality/ Sun, 16 Oct 2022 23:44:48 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2148 ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ማቴ 25፥21 “አንተ ታማኝ ባሪያ” መባል ከምንም በላይ ሊያሳስበን የሚገባበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፤ በጌታ ፊት ዋጋ የሚሰጠው ታማኝ ባሪያ መሆን እንጂ ዝነኛ አገልጋል ሆኖ መገኘት አለመሆኑን ልናስተውል ይገባል፤ ታማኝ ሆኖ መገኝትን በተለያየ መልኩ የሚያሳንሱብን፣ ይሄንን ዋና የሆነውን ጥሪ እንዳናይ […]

The post ዝነኝነት ወይንስ ታማኝነት? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ማቴ 25፥21

“አንተ ታማኝ ባሪያ” መባል ከምንም በላይ ሊያሳስበን የሚገባበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፤ በጌታ ፊት ዋጋ የሚሰጠው ታማኝ ባሪያ መሆን እንጂ ዝነኛ አገልጋል ሆኖ መገኘት አለመሆኑን ልናስተውል ይገባል፤ ታማኝ ሆኖ መገኝትን በተለያየ መልኩ የሚያሳንሱብን፣ ይሄንን ዋና የሆነውን ጥሪ እንዳናይ የሚጋርዱን ብዙ አይነት ነገሮች በዙሪያችን ከበውናል፤ በተለይ ዘመን አመጣሹ የሶሻል ሚዲያውም ሆነ እንደ ዝነኛ (Celebrity) ወይንም ፌመስ ዘማሪ፣ ፌመስ ሰባኪ የመደነቅ ነገር ለብዙዎች እንቅፋት እየሆነ ያለንበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፤

ወደ ዝነኝነት የመጡ ሰዎች ብዙ አይነት የሕይወት መንገድ ተጉዘው ወደ ዝነኝነት ማማ ላይ መውጣት የቻሉ ናቸው፤ ይሄ ዋጋ ያስከፈላቸው ጉዞ እና አሁን ያሉበት ክብር (STATUS) በቀላሉ ሊለቁት የማይችሉት ማንነት ሆኖ ያገኙታል፤ ይሄን አይነቱ ዝነኝነት ወደ ቤተ እምነት የገባ አደገኛ የሆነ አካሄድን እየተፈጠረ እንዳለ ማየት ይቻላል፤ እነዚህ በጌታ ቤት በዝነኝነት መንፈስ ራሳቸውን ከፍ ያደረጉ፣ ከመደዴው ምእመን በላይ እንደሆኑ የሚያስቡ፤ ጌታ የሰጣቸው ጸጋ፣ ታማኝ ሊሆኑ የተጠሩለትን ጥሪ ያጎደሉ፣ ቅባታቸው ከተራው አማኝ ተርታ እንዳይመደቡ ከዛም ባለፈ መልኩ የሚቀመጡበት ወንበር የተለየ፣ የሚለብሱት ልብስ በዋጋ የተወደደ አንዳንዶቹም የሚነዱት መኪና ለኔ ቢጤው ደሃ ሲታይ የሚያስደነግጥ እየሆነ ከመጣ ሰንበትበትብሏል፤

በታዋቂነት ማንነት ማገልገል እና ለቃሉ እውነት ታማኝ ሆነን በማገልገል መካከል ያለው መስመር በጣም ስስ ነው፤ በጳውሎስ እና ባርናባስ (ሐሥ 14፥8-19) ያለውን ታሪክ ስንመለከት የሚያስተምረን ነገር አለ፤ ጳውሎስ እና ባርናባስ በበልስጥራን በእነሱ የተደረገው ተአምር ምክንያት “ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ፣ በሊቃኦንያ ቋንቋ፣ “አማልክት በሰው ተመስለው ወደ እኛ ወርደዋል!” ብለው ጮኹ፤” (ሐሥ 14:11) ይሄ የሚያሳየን ቀጣዩ ነገር እነ ጳውሎስን ለየት ያለ ስፍራ መስጠት ከዛ ባለፈ መልኩ ልዩ በሆነ መልኩ እነሱን ትንንሽ አማልክት ማድርገ ማምለክ ነበር የዚያ ከተማነዋሪዎች ፍላጎት። የጳውሎስ እና ባርናባስ ምላሽ ግን ““እናንት ሰዎች፤ ለምን ይህን ታደርጋላችሁ? እኛም እኮ እንደ እናንተው ሰዎች ነን” የሚል ነበር፤ ምክንያቱም ታማኝ ሊሆኑለት የሚገባ ጥሪ የነበራችው ሰዎች ስለነበሩ፤

ይሄን መስመር በምን ያክል እንዳለፍን አንዳንዴ በማይገባን መልኩ አልፈነው ልንገኝ እንችላለን፤ ቤተ ክርስቲያን በተለይ በሰዎች ዘንድ የተለየ ዝነኝነት ያተረፉ ሰዎች እንዲያገለግሉም ሆነ በመድረኮቻቸው እንዲገኙ ሲሽቀዳድሙ መመልከት ለዚህ አይነቱ ችግር የበለጠ መባባስ ምክንያት ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ ነው፤ “ከልካችን ያለፈ ጉርሻ መዋጥ ትንታ ያተርፋል። እግዚአብሔር በሰጠን ልክ ለክብሩ በመኖር ፈንታ የየራሳችን ትንንሽ ጣዖታት ለመሆን ባንጋጠጥን ጊዜ በድንገት መፈንገልን እናተርፋለን።” (የዱባ ጥጋብ ገጽ 118 በሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን)

ዝነኛ ሰዎች በተለየ መልኩ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ እንዲታወቅ የተለየ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብዬ አላምንም፤ ነገር ግን በእነዚሁ ሰዎች አማካኝነት ጌታ አይሠራም ማለቴም እንዳልሆነ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ፤ በጣም ጌታን የሚፈሩ በታማኝነት እርሱንና እርሱን ብቻ የሚያገለግሉ፣ በሚያገለግሉት ጌታም ሆነ የአገልግሎታቸውን በረከት ተካፋይ በሆነ አማኝ መካከል ስፍራ ያላቸው ወገኖችም እንዳሉ ማሰብ ተገቢ እንደ ሆነ አምናለሁ፤ “በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ።” (ቆላ 4፥17) ብሎ ጳውሎስ ለአክሪጳ እንዳስጠነቀቀው በዙሪያቸው የሚታየው ግርግር እና ጭብጨባ ሳይሆን ለተቀበለው አገልግሎት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያስጠነቅቀዋል፤

‘ከዚህም የተነሣ ዝናው በመላዋ ሶርያ ተሰማ፤ ‘ማቴዎስ 4:24

በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት እየሆነ ከነበረው ነገር የተነሳ ለየት ያለ እውቅናን አግኝቶ ነበር፣ ከመታወቅም አልፎ እንደውም ስላበላቸው ስላጠጣቸው፤ “’ኢየሱስም ሰዎቹ መጥተው በግድ ሊያነግሡት እንዳሰቡ ዐውቆ እንደ ገና ብቻውን ወደ ተራራ ገለል አለ።” (ዮሐንስ 6:15) በዚህ የዮሐንስ ወንጌል ታሪክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባደረገው ነገር ዝናን አትርፎ ነበር ነገር ግን ከዝነኝነት የተነሳ የሚመጣ ክብር ከሚያስገኝልን ምስጋና ይልቅ ይዞብን የሚመጣው ጣጣ ብዙ መሆኑን ሊያስተምረን ስለፈለገ ራሱን ገለል አደረገ እንጂ ለማሱ (ለብዙሃኑ) ግርግር ራሱን አልሰጠም፤

ራስን እንደ ማወቅ እና ራስን እንደ መሆን ትልቅ ነገር የለም፤ ይሄ በሕይወታችን መሆን ሲችል ያን ጊዜ ለታማኝነት የቀረበ ልቦናን እናገኛለን፤ ራሳችንን መሆን የሚያስችለን ብቸኛው ነገር ለእግዚአብሔር ቃል የተጠጋ ማንነት ሲኖረን ነው፤ የቃሉ መስታወት ማንነታችንን ለራሳችን በማጋለጥ ልካችንን እንድናይ ያደርገናል እግዚአብሔርን የትኛውንም ያክል ብናውቀው ልንላመደው አንችልም ለዚህ ነው ራስን ማወቅ ልክን ማወቅ ነው። ጌታ ጌታ  ነው እኛ እኛ ነን፤ ጴጥሮስ ከጌታ ኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ስለ ራሱ ያለው እይታ ለየት ያለ መሆን ችሎ ነበር፤ በፊት ፈጠን ፈጠን ይል የነበረው አሁን ግን “…..ጌታ ሆይ፤ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድድህም ታውቃለህ” አለው።” ወደሚለው ራስን ወደማወቅ መጣ፤ (ዮሐ 21፥17)

የተቀበልነው አደራ ተጠያቂነት ያለበት ስለሆነ ታማኝነት ግድ ይላል፤ ልባም ባሪያ ሆነን ስንገኝ የተሰጠንን አደራ ለተደራሹ እንደሚገባ ተጠንቅቀን እናደርሳለን፤ ለዚህ አይነቱ ባሪያ ትልቁ ትኩረት ተደራሹ አይደለም አደራ የሰጠው ነው ትልቅ ስፍራ ያለው!! “’ጌታም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እንግዲህ፣ ምግባቸውን በተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው፣ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ብልኅ መጋቢ ማነው? ‘ሉቃስ 12:42

የተቀበልነው አደራ ራሳችንን ልናሳይበት ሳይሆን ልንጠነቀቅለት፣ ራሳችንን እኛነታችንን ዝቅ ልናደርግለት፣ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በምድረበዳ የምንጮህ ድምጽ የምንሆንለት እንጂ የምንታይ ዝነኞች እንዳልሆንን ሊገባን በዚህ መልኩ ራሳችንን ልናውቅ ይገባል፤

‘እርሱ ሊልቅ፣ እኔ ግን ላንስ ይገባል። ‘ዮሐንስ 3:30

 

The post ዝነኝነት ወይንስ ታማኝነት? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ደቀ መዝሙር https://deqemezmur.com/2022/09/29/discipleship/ Thu, 29 Sep 2022 23:12:38 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2043 “ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።” ሉቃ 14፡27 ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የተናገረው ቃል ነው። ይህ ቃል ዛሬም ሊከተሉት ለሚወዱት ሁሉ ተገቢውን ጥያቄ ያነሳል፡ ራስን በመካድ ለእርሱና ለሱ ብቻ ለመኖር ውሳኔን አድርገን እንከተለው ዘንድ ይህ ጥሪ ለእያንዳንዳችን ደርሶናል ምላሻችን ግን ምንድን ነው? በተለይ ባለንበት ዘመን በየቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ በየኮንፈረንሱ የምንሰማቸው ስብከቶች […]

The post ደቀ መዝሙር first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>

“ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።” ሉቃ 14፡27

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የተናገረው ቃል ነው። ይህ ቃል ዛሬም ሊከተሉት ለሚወዱት ሁሉ ተገቢውን ጥያቄ ያነሳል፡ ራስን በመካድ ለእርሱና ለሱ ብቻ ለመኖር ውሳኔን አድርገን እንከተለው ዘንድ ይህ ጥሪ ለእያንዳንዳችን ደርሶናል ምላሻችን ግን ምንድን ነው? በተለይ ባለንበት ዘመን በየቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ በየኮንፈረንሱ የምንሰማቸው ስብከቶች (ትምህርቶች) ምን ላይ ያተኮሩ ናቸው ብላችሁ አስባችሁ ታውቁ ይሆን? ከርዕሶቻቸው እንኳ ብንነሳ “የጥርመሳ ዘመን” “የቅባት ዘመን” “የከፍታ ዘመን” ወዘተ… እያለ ይቀጥላል። ይሄ ማለት ግን ጥቂቶች የሚሆኑ የክርስትና አንኳር ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ የሉም ማለት አይደለም። ነገር ግን አብዛኛው ያደላው የኛ የአማኞች ሕይወት ለምድር የተፈጠረ ብቻ ያህል አድርገን እንድናስብ የሚያደርጉን መብዛታቸው እጅግ ያሳዝናል። ክርስትና ዋጋ ያስከፍላል !! የሚለው የኢየሱስ አስተምህሮ ከብዙዎች አንደበት የራቀ ይመስላል ወጣት የሆነውን ትውልዳችንን እንዲለማመድ እየተደረገ ያለው ነገር ከቀደሙ አባቶች ሕይወት ጋር ሲነጻጸር እጅጉን የራቀ ነው። ይሄ ጉዳይ ሊያሳስበን ይገባል ልል ነው ብቅ ያልኩት። እንደው የአቅም ለማበርከት መቼም ያለንበት ዘመን የሶሻል ሚዲያ መነጋገሪያ የሆነበት ዘመን ላይ ነው፡ ይሄንኑ ቴክኒዮሎጂ በመጠቀም ድምጼን ላሰማ ብዬ ነው። ጠንካራ ደቀ መዝሙርነት ያስፈልገናል አንድ ሰው እንዳለው ነው “ቤተ ክርስቲያንን ደቀ መዛሙርት ያልሆኑ ደቀ መዝሙሮች ሞልተዋታል” አለ።  

እንግዲህ ደቀ መዝሙርነት ዋናው እና ወሳኙ የክርስቲያን መለያው ነው። መስቀሉ ማንነታችን ነው። የሞቅታና የይሆንልሃል አስተምሕሮዎች የትም እያደረሱን አይደለም ያሉት። እውቁ ጀርመናዊው መጋቢ እና የነገረ መለኮት መምህር ዲትሪክ ቦንሆፈር “ብዙ ሰዎች በትክክለኛ ፍላጎት የምንናገረውን ለመስማት ወደ ማምለኪያ ስፍራችን ይመጣሉ ነገር ግን በብዛት ጥሩ ያልሆነ ስሜት እየተሰማቸው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ ምክንያቱም ወደ ኢየሱስ እንዳይመጡ በጣም ውስብስብ (አስቸጋሪ) ስለምናደርግባቸው ነው።” ብሎ ተናገረ የጌታ ኢየሱስ መልዕክት በጣም ግልጽ ነበር ሰዎች እንዲወስኑ ጥያቄ የሚፈጥር ሊከተሉት አለዛ ላይከተሉት ደቀ መዝሙራዊ ጥሪ ያቀርብላቸው ነበር። “ኢየሱስም፦ ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው።” ማቴ 8:20 ይሄ እንግዲህ የኢየሱስ ጥሪ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው በዚህ በማቴዎ 8 ላይ ባለው ታሪክ የምናየው ለዚህ የአይሁድ መምህር “ወደ ምትሄድበት እሄዳለሁ” ብሎ ማለቱ በጣም ቀላል ነበረ ነገር ግን ወደ ዋናው ውሳኔ እንዲመጣ ሲጋበዝ ያን ጊዜ ነው እውነተኛ ውሳኔ መወሰኑም አለመወሰኑም የሚታየው ኢየሱስ አይደለም ልከተልህ የሚሉትን ይቅርና አብረውት ያሉትን “ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ። እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ።” ዮሐ 6፡67  እንደው ዛሬ ጌታ እኛን ተመሳሳይ ጥያቄ ቢያቀርብልንስ? ለምን እንደተከተልነው ገብቶን ይሆን? እንደ ፈሪሳዊው አብሬህ እሄዳለሁ ማለቱ ላይከብድ ይችላል መወሰኑ ግን በጣም ወሳኝ ነው አብሬው ነኝ፡ ብለን ልናስብ ይሆን ይሆናል ነገር ግን እንደ ደቀ መዛሙርቱ  ሌሎች አማራጭ የሚመስሉ ነገሮች ጋር ስንደርስስ? እንደ ጴጥሮስ “ከአንተ ወዴት እንሄዳልን?”  ለማለት የሚያስችል የሕይወት ውሳኔን አድርገን ይሆን? ራሳችንን ክደን  መስቀሉን ተሸክመን መከተል አማራጭ የሌለው ጥሪ ነው። በይሆንልኛል የሂሳብ ስሌት ሰርተን ሳይሆን “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።” ማቴ 10፡25 የሚለውን ሂሳብ ሰርተን መከተል ነው። እንግዲህ ጎበዝ ወገባችንን ጠብቅ ትንፋሻችንን ሰብሰብ አድርገን የጀመርነውን ጉዞ በሚገባ ለመቀጠል እንበርታ ተስፋችን እኛ ከምናስበው ይበልጣል ጥሪያችን ክቡር ነው፡ መድረሻችን ከፍያለ ነው፡ ሰለዚህ እንበርታ።  ደቀ መዛሙርት በመሆን ሌሎችንም ደቀ መዛሙርት እናድርግ፤

The post ደቀ መዝሙር first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ማድረግ https://deqemezmur.com/2022/09/28/seeking-the-lord/ Wed, 28 Sep 2022 03:14:17 +0000 https://deqemezmur.com/?p=1939 በክርስቶስ በማመን ከመንፈሳዊ ሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ሰው ብዙ በረከቶችንና መብቶችን ያገኛል፤ ከነዚህ መካከል አንዱ ከእግዚአብሔር ጋር ሙሉ በሙሉ መታረቅና አዲስ ሕብረት መጀመር ነው፡፡ ይህ ሕብረት አእምሯችን ሊያስበው ከሚችለው ከየትኛውም ነገር የጠለቀ፣ የተሟላና የሰፋ ሕብረት ነው፡፡ በኛና በእግዚአብሔር መካከል ባለው ሕብረት ላይ ትልቅ ተፅዕኖን የሚያሳድረው በኛና በእግዚአብሔር መካከል የሰፋ ልዩነት መኖሩ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፦ እኛ […]

The post ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ማድረግ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
በክርስቶስ በማመን ከመንፈሳዊ ሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ሰው ብዙ በረከቶችንና መብቶችን ያገኛል፤ ከነዚህ መካከል አንዱ ከእግዚአብሔር ጋር ሙሉ በሙሉ መታረቅና አዲስ ሕብረት መጀመር ነው፡፡ ይህ ሕብረት አእምሯችን ሊያስበው ከሚችለው ከየትኛውም ነገር የጠለቀ፣ የተሟላና የሰፋ ሕብረት ነው፡፡ በኛና በእግዚአብሔር መካከል ባለው ሕብረት ላይ ትልቅ ተፅዕኖን የሚያሳድረው በኛና በእግዚአብሔር መካከል የሰፋ ልዩነት መኖሩ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፦

    • እኛ ውሱኖች ስንሆን እግዚአብሔር ግን ያልተወሰነ ነው፡፡
    • ስለምንኖርበት ዓለምና በእርከናችን ስላሉት ሰዎች ያለን መረዳት በጣም ውሱን ሲሆን እርሱ ግን ሁሉን አዋቂ ነው፡፡
    • እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው፤ እኛ ፍጡራን ነን፡፡
    • እርሱ የማይታይ ነው፤ እኛ ግን እንታያለን፡፡
    • እርሱ የማይለዋወጥ ነው፤ እኛ ግን እንለዋወጣለን፡፡
    • እግዚአብሔር ፍፁም ነው፤ እኛ ግን ፍፁማን አለመሆናችን ግልፅ ነው፡፡

ሆኖም ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት በሕይወታችን ውስጥ ከምናውቃቸው ሕብረቶች ጋር የሚመሳሰልባቸው መንገዶች አሉ፡፡ ይህም እንደማንኛውም ሕብረት ጊዜን፣ መነጋገርን፣ መፈላለግን፣ መቀራረብን፣ ወዘተ. የሚፈልግ መሆኑ ነው፡፡ ከሕብረቶች መካከል ምርጡ ረጅም ጊዜን በመውሰድ በጥልቀት ሐሳባችንን የምናካፍልበት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረትም ተመሳሳይ መንገድ ይከተላል፡፡ እንደ ማንኛውም ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ሁለትዮሽያዊ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሕብረትን ለመመሥረት የሚያደርጋቸው የተወሰኑ ነገሮች አሉ፤ ሕብረቱ እንዲጠብቅና እንዲያድግ ደግሞ ከኛም የሚጠበቁ ነገሮች አሉ፡፡ ይህንን የሁለትዮሽ መንገድና በሕብረት ላይ ያለውን ተፅዕኖ መረዳት በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሕብረት መንከባከብ የምንችለው ይህንን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዴት መንከባከብ እንደምንችል በመረዳት ነው፡፡

እግዚአብሔር ከኛ ጋር ላለው ሕብረት የመጀመርያውን እርምጃ ይወስዳል

በጥልቀት ያውቀናል (መዝ. 139፡1-4)፡-

እግዚአብሔር ስለ እኛ ሁሉንም ነገር ያውቃል፤ ተግባራታችንን፣ እንቅስቃሴዎቻችንን፣ ሐሳባችንን፣ ቃላችንን ያውቃል፡፡ እርሱ ሁሉን አዋቂ ስለሆነና ከጊዜና ከቦታ ውጪ ስለሚኖር እነዚህ ነገሮች ከመሆናቸው በፊት አስቀድሞ ያውቃቸዋል፡፡ እኛ ራሳችንን ከምናውቀው በላይ ያውቀናል፡፡

ዕውቀት በሰው ልጆች ግንኙነት ውስጥ አስፈሪ ነገር ነው፡፡ ለሌሎች የምንነግረው ችግር እንደማያስከትል ያመንንበትን ብቻ ነው፡፡ ሌሎች እንዳያውቁ የምንፈልጋቸውን መረጃዎች ደግሞ እንሰውራለን፡፡ እግዚአብሔር ስለ እኛ ሁሉንም ነገር ስለሚያውቅ ምንም ነገር ልንደብቀው አንችልም፡፡ የሚገርመው ነገር ግን ስለ እኛ የማይወደዱ ብዙ ነገሮችን ቢያውቅም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይወደናል!!!

ይጠብቀናል ይጋርደናል፡፡ እርሱ ጠባቂያችን ነው (መዝ. 139፡5-6)፡-

መዝሙረኛው “አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ፡፡” ይላል፡፡ እግዚአብሔር እጁን በኛ ላይ ማድረጉ ሁለንተናችንን የመጠበቁ ተምሳሌታዊ ንግግር ነው፡፡ በሌላ መዝሙር ላይ ዳዊት እግዚአብሔር ለእርሱ መጠንቀቁን በተለያዩ ምሳሌዎች ይገልፃል፡፡ ጋሻ፣ ምሽግ፣ መሸሸጊያ ቦታ እና መጠጊያ እያለ ይገልፃል፡፡

መዝሙር 91፡1-2 ላይ እንዲህ ይላል፡- “በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል፡፡ እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ፡፡”

ያለንበት ሁኔታ ምንም ቢሆን ሁል ጊዜ ትኩረቱ በኛ ላይ ነው (መዝ. 139፡7-12)፡-

መዝሙረኛው “ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?” በማለት በመደነቅ ይናገራል፡፡ በማስከተልም የትም ቢሄድ ከእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ሊወጣ እንደማይችል ይናገራል፡፡ ይህ ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነትና ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት መካከል የሚገኝ ትልቅ ልዩነት ነው፡፡ አንድ ሰው ምንም ያህል ቢመኝ ሁል ጊዜ የሥጋችንንና የስሜታችንን ፍላጎቶች ለመሙላት ሊገኝልን አይችልም፡፡ በሆነ ጊዜ ላይ ርቀትና ሌሎች ጉዳዮች ሊያግዱት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ከኛ ጋር ወደማይሆንበት ቦታ መሄድ አንችልም፡፡ እርሱ የሌለበት ቦታ የለምና፡፡

የሕልውናችን መሠረትና አስቀጣይ እርሱ ነው፡ ውጪያዊ (ሥጋችን) እና ዘላለማዊ (ስሜታዊ፣ መንፈሳዊ) (መዝ. 139፡13-16)፦

ስለሚቀርቡን ሰዎች በጣም ዋጋ ከምንሰጣቸው ነገሮች መካከል አንዱ አንዳችን ሌላችንን መረዳት መቻላችንን ነው፡፡ እነዚያ ምርጥ ወዳጆቻችን ምን እንደምንወድና እንደምንጠላ ያውቃሉ፡፡ እግዚአብሔር ፈጣሪያችን ስለሆነ ከማንም በላይ ውስጣችንን ያውቀዋል፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ሕብረት ውስጥ ኃላፊነት አለብን፦

  1. እርሱን ለመፈለግ (ኤር. 29፡10-14)

“እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ”  (ኤር 29፡10-14)፡፡ ልብ የአንድን ሰው የማንነቱን ማዕከል፣ ማለትም ስሜቱንና ፈቃዱን ያመለክታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከልብ ጋር የተያያዙ ብዙ ትዕዛዛት አሉት፤ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችን እንድንወደው (ዘዳ. 6፡5)፣ በፍጹም ልባችን እንድንታመነው (ምሳ. 3፡5)፣ በፍጹም ልባችን ንስሐ እንድንገባ ተነግሮናል (ኢዩ. 2፡12)፡፡ በግማሽ ልባችን ልንፈልገው አይገባንም፡፡

ወደ ተለያዩ ቦታዎች ለጉዞ የወጡ ሁለት ሰዎችን እስኪ አስቡ፡፡ የመጀመርያው ሰው በሳምንቱ አጋማሽ የጥፍር መቁረጫውን መጣሉን አስተዋለ፡፡ ብዙም ውድ ባይሆንም ጥሩ የጥፍር መቁረጫ ነው፡፡ ምናልባት ድንገት እንደ አጋጣሚ አገኘው ይሆናል በሚል ሲሄድ አልፎ አልፎ በዓይኖቹ ያማትራል፡፡

ሁለተኛው ሰው ከቤት በወጣበት ምሽት የመኪናው ቁልፉ ጠፋበት፡፡ በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ባለቤቱ ልጃቸው የመኪና አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል መግባቱን ደውላ ትነግረዋለች፡፡ በእጁና በጉልበቱ እየዳኸ ቁልፉን ፈለገው፡፡ የሸከፈውን እቃ ሁሉ በታትኖ ፈለገ፡፡ በመጣበት መንገድ ተመልሶ ቁልፉን ፈለገው፡፡ የመጀመርያው ሰው ሴንጢውን ይፈልግ የነበረው በግማሽ ልቡ ነበር፡፡ ሁለተኛው ሰው ቁልፉን ይፈልግ የነበረው በፍጹም ልቡ ነበር፡፡

  1. በፍጹም ልባችን፣ በፍጹም ነፍሳችንና በፍጹም ሐሳባችን ልንወደው ይገባል (ማቴ 22፡36-39)

“መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፡፡ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት፡፡” (ማቴ 22፡37)

እግዚአብሔር መኖሩን ወይም ፈጣሪ መሆኑን ዕውቅና መስጠት ብቻ ሳይሆን በፍጹም ልባችን፣ ነፍሳችንና ሐሳባችን ልንወደው ይገባል፡፡ በሌላ አባባል በሁለንተናችን ልንወደው ይገባል፡፡

  1. እርሱን መታዘዝ (ዮሐ 14፡21)

የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የመታዘዝ ኃላፊነትም አለብን፡፡ ይህ ፍቅር በተግባር የሚገለጥበት መንገድ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ እንደተናገረው መታዘዝ ለእግአብሔር ያለንን ፍቅር የምንገልጥበት መንገድ ነው (ዮሐ. 14፡21)፡፡ ይህንን ቃል የጻፈው ሐዋርያው ዮሐንስ ኋላ ላይ የኢየሱስን ንግግር በመድገም ጽፏል፡- “ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም” (1ዮሐ. 5፡3)። እግዚአብሔርን አውቀናል (ከእርሱ ጋር ሕብረትን መሥርተናል) የምንል ከሆነና ትዕዛዛቱን ባንጠብቅ ውሸተኞች መሆናችንን ዮሐንስ ተናግሯል (1ዮሐ. 2፡4)፡፡

  1. ወደ እርሱ መቅረብ (ኤር. 4፡8)

የጌታ ኢየሱስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ጻፈ፡- “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፡፡ እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ” (ያዕ 4፡8)። ይህ ጥቅስ ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ሕብረት ያለብንን ሌላ ኃላፊነት የሚገልፅ ነው፡፡ ስለ ውጫዊ ተግባራችን (እጆቻችሁን አንጹ) እና ስለ ውስጣዊው ሐሳባችንም ጭምር (ልባችሁን አጥሩ) ይናገራል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ ሁለቱም አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡

እኛ ኃጢአተኛ ፍጥረታት በመሆናችን ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ሕብረት ከእርሱ የሚያርቁንን ተግባራት እንፈፅማለን፡፡ ስለዚህ መራቃችንን ባወቅን ቁጥር ራሳችንን ዝቅ ማድረግ ያስፈልገናል፤ ኃጢአታችንንም በመናዘዝ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ያስፈልገናል፡፡ እኛ እርሱን በመፈለግ ወደ እርሱ እንቀርባለን፤ እርሱ ደግሞ በሙላት ወደ እኛ ይቀርባል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ኃላፊነቶች ከተስፋ ጋር እንደተያያዙ ልብ በሉ፡፡ ኃላፊነታችንን ስንወጣ አዎንታዊ ምላሽን እናገኛለን፡፡ ይህ ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን የሁለትዮሽ መንገድ ግንኙነት የሚገልጥ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ስንፈልግ ይገኝልናል፤ ለኛ ያለውን ግሩም የሆነውን ዕቅዱንም ይገልጥልናል፡፡ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ፍቅራችንን ስንገልጥ ፍቅሩን ይገልጥልናል፤ ራሱንም ይገልጥልናል፡፡ ወደ እርሱ ስንቀርብ እርሱም ወደ እኛ ይቀርባል፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ከእርሱ ጋር በመጣበቅ ይለመልማል 

እያንዳንዱ ግንኙነት የሚያድገው ልምዶችን በመለዋወጥና እርስ በርስ በሚገባ በመተዋወቅ ነው፡፡ ክርስትና በባሕርዩ በሕያው እግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል የሚደረግ ግንኙነት ነው፡፡ ራሱን ለኛ በመግለጥና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እኛን ከራሱ ጋር በማስታረቅ እግዚአብሔር እኛን በመፈለግ ይህንን ሕብረት ጀምሯል፡፡ በምላሹም እግዚአብሔርን በንቃት መፈለግና ከእርሱ ጋር ያለንን ሕብረት ልንንከባከብ ይገባናል፡፡ ይህንንም ከእርሱ ጋር ጊዜን በማሳለፍ ነው መፈፀም የምንችለው፡ ነገር ግን ሰዎች ብዙ ጊዜ “እግዚአብሔርን ሳታየው እንዴት ነው አብረኸው ጊዜን ልታሳለፍ የምትችለው?” በማለት ይጠይቃሉ፡፡ እንደ መታደል ሆኖ እግዚአብሔር መንገዱን አሳይቶናል፡፡ የእርሱ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ሰጥቶናል፡፡ በጸሎት ሥፍራችን ደግሞ ያገኘናል፡፡ ቃሉን ሳናቋርጥ ስናነብና ስንጸልይ ወደ እርሱ ይበልጥ እንቀርባለን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት ሰዎች ጋር እንዴት ሕብረት ያደርግ እንደነበር ስንመለከት የእርሱን ባሕርይ፣ እሴቶች እና ማንነቱን እናውቃለን፡፡ ከቃሉ ጋርና በጸሎት ጊዜን ባሳለፍን ቁጥር እግዚአብሔር እኛን በመቀበል ሕይወታችንን ይለውጣል፡፡

ከእግዚአብሔር ጋር በቃሉ አማካይነት እንገናኛለን

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና በተግባር መኖር ግሩም ልምምድ ነው፡፡ ከሌሎቹ መጻሕፍት በተለየ ሁኔታ የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና መንፈሳዊ ነው፣ በተግባር የሚቀየርና ጥልቅ ነው፡፡ የዕብራውያን መጽሐፍ የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ እንደሆነ ይናገራል (ዕብ. 4፡12)፡፡ በእርሱ አማካይነት እግዚአብሔር ሁለንተናችንን፣ ማለትም ነፍሳችንን፣ መንፈሳችንን፣ አካላችንን፣ አእምሯችንንና ልባችንን ይነካል፡፡ ቃሉን ባነበብንና በታዘዝን ቁጥር በሕይወታችን ውስጥ መሠረታዊ ለውጥ ይሆናል፡፡ መዝሙር 19፡7-14 የእግዚአብሔር ቃል ነፍሳችንን እንደሚያድስ፣ ጠቢባን እንደሚያደርገን፣ እንደሚያበረታንና እንደሚመራን ይናገራል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ከመልካም ምክር ያለፈና እግዚአብሔር ከኛ ጋር በቀጥታ የሚነጋገርበት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ጊዜን ማሳለፍ ከንጉሥ ጋር እንደ መነጋገር ነው፡፡ ይህም ማለት ቃሉን መቅረብ ያለብን ልክ እግዚአብሔርን እንደምንቀርበው ነው፤ በትህትናና በመታዘዝ፡፡ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፡- “ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ፡፡” (ዮሐ. 14፡21)

ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ጊዜን ማሳለፍ ከምሑራዊ ልምምድ ወይም ራስን ከማሻሻል ያለፈ ነው፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ያለንን አክብሮትና ፍቅር የምንገልጥበት መንገድ ነው፡፡ ለመማር ምቹ በሆነ አቀራረብና ለመለወጥ በመፈለግ በቃሉ በኩል ወደ እግዚአብሔር እንጠጋለን፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ባሕርዩን በሙላት ያንፀባርቃል እንዲሁም ዳርቻ የሌለውን ሉኣላዊ ኃይሉን የተሞላ ነው፡፡ በመዝሙር 37 ላይ ዳዊት እግዚአብሔር የገባውን ቃል እንደሚፈፅም ይነግረናል፡፡ ደግሞም ይመክረናል፡- “በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል” (ቁ. 4)። ስለዚህ እግዚአብሔር እውነቱን እንዲገልጥልንና ፈቃዱን በመካከላችን እንዲፈፅም በሚጠማ ልብ ልንጠባበቀው ይገባል፡፡

በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር እንነጋገራለን

እንደ ምድራዊው ጓደኝነታችን ሁሉ ከሰማዩ አባታችን ከእግዚአብሔር ጋርም ያለን ሕብረት መቋረጥ የለበትም፡፡ ሕይወታችን ከእግዚአብሔር ጋር የማያልቅ ንግግር የምናደርግበት ሊሆንልን ይችላል፡፡ ጸሎት ቃሉን በማንበብ ባሳለፍነው ጊዜ ላይ ተጨምሮ ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርገውን ንግግር እንድንቀጥል ያስችለናል፡፡ ነገር ግን ጸሎት ምንድነው? ጸሎት ሐዋርያው ዮሐንስ እንደጻፈው እግዚአብሔር እኛን ለመድረስ ለወሰደው እርምጃ የምንሰጠው ምላሽ ነው፡፡ ጌታችን እንዲህ አለ፡- “እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፡፡” (ራዕይ 3፡20)

ጸሎት የእግዚአብሔርን እርዳታ የምንጠይቅበትና የእርሱን አብሮነት የምንቀበልበት ነው፡፡ እንኳን በደህና መጣህ የማለት ወይንም ለእርዳታ የመጣራት ያህል ነው፡፡በጸሎት ለእግዚአብሔር ትኩረትን የምንሰጥበት ሕይወት በቀላሉ የሚመጣ አይደለም፡፡ የጸሎት ልምምድ ውስጥ መግባት ትግል አለው ነገር ግን ደስታን ያጎናፅፈናል፡፡እግዚአብሔር በጸጋው ጸሎትን ያለማምደናል፤ በቃሉም ውስጥ ብዙ ምሳሌዎችን ሰጥቶናል፡፡ ኤልያስ፣ ዳንኤል፣ አስቴር፣ ነህምያ፣ ራሱ ጌታ ኢየሱስና ሐዋርያቱ ይጠቀሳሉ፡፡

መጽሐፍ ቅደስ ስለ ጸሎት አጥብቆ ይናገራል፡፡ አንድ ክርስቲያን መፀለይ ካልቻለ ጤናማ መንፈሳዊ ሕይወት ሊኖረው አይችል፡፡

  • “እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።” 1ዜና 16፡11
  • “እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።” መዝ 145፡18
  • “እግዚአብሔር ከኅጥኣን ይርቃል የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።” ምሳ 15፡29
  • “ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።” ፊልጲስዩስ 4፡6
  • “ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ።” ቆላ 4፡2
  • “ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” 1ተሰ 5፡17
  • “እንዲህም አላቸው፦ ከእናንተ ማናቸውም ወዳጅ ያለው፥ በእኩል ሌሊትስ ወደ እርሱ ሄዶ። ወዳጄ ሆይ፥ ሦስት እንጀራ አበድረኝ፥ አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት የለኝምና ይላልን? ያም ከውስጥ መልሶ፦ አታድክመኝ፤ አሁን ደጁ ተቈልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ አሉ፤ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም ይላልን? እላችኋለሁ፥ ወዳጅ ስለ ሆነ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፥ ስለ ንዝነዛው ተነስቶ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል። እኔም እላችኋለሁ። ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል። አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ እርሱም ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ደግሞ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን? ወይስ እንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?” ሉቃ 5፡11-13
  • “በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።” ሉቃ 6፡12
  • “ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል፦ በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች። ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ። ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። ጌታም አለ። ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?” ሉቃ 18፡1-8
    • ጸሎት ነገሮችን ይለውጣል፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ እኛን ይለውጠናል፡፡
    • ጸሎት የእግዚአብሔርን ልብ ለልባችን ይገልጣል፡፡
    • ጸሎት የእግዚአብሔር ክብር በሕይወታችን እንዲገለጥ ያደርጋል፡፡
    • ጸሎት ከማይታዩ የክፋት ሰራዊቶች ጋር የሚደረግ ተጋድሎ ሲሆን ድል የማግኛ መንገድ ነው፡፡
    • ጸሎት ወደ እግዚአብሔር የመገኘቱ ሕልውና ያመጣናል፡፡
    • የሚጸልይ ሰው የእግዚአብሔርን ድምፅ ይለማመዳል፤ የእግዚአብሔርን አጠቃላይ ፈቃድ ከማወቅ አልፎ ለአስፈላጊ ጉዳዮች ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመመራት ልምምድ ውስጥ ይገባል፡፡
    • የሚጸልይ ሰው በእግዚአብሔር በረከት ውስጥ ይኖራል፤ ከፈተና የመውጫ መንገዶችንም ያገኛል፡፡
    • የሚጸልይ ሰው ለምድር ለውጥን ያመጣል፤ የእግዚአብሔርም ሞገስ ይሆንለታል፡፡

ማጠቃለያ

የግል የፅሞና ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ለመመሥረት በጣም ወሳኝ ነው፡፡

    • ትክክለኛ ጊዜ መምረጥ (ማለዳና አመሻሽ አካባቢ)
    • የሚያስፈልጉንን መሣርያዎች መያዝ (መጽሐፍ ቅዱስ፣ ማስታወሻ፣ የምናዳምጠው ለስላሳ መዝሙር)
    • ገለልተኛና ፀጥተኛ ቦታ ማግኘት፡፡
    • ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተወሰነ ክፍል ማንበብ፡፡
    • በምስጋና መጀመር፣ በንስሐ ራስን ማየት፡፡
    • በፀጥታ የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላሰል፤ ጌታን ማድመጥ፡፡
    • ይህንን የየዕለት ልማድ ማድረግ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንንም ይርዳን!

The post ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ማድረግ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
የክርስቲያን ጉዞ በዝግታ … ያለማቋረጥ https://deqemezmur.com/2022/09/28/spiritual-growth/ Wed, 28 Sep 2022 02:33:46 +0000 https://deqemezmur.com/?p=1934 ክርስቲያናዊ ሕይወት አጭር ሩጫ ሳይሆን ማራቶን ነው፡፡ ማራቶንን ለመሮጥ የሚያስፈልገውን ጥንካሬ ማዳበር ጊዜን ይፈልጋል፡፡ አንዳንድ አማኞች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፎችን ስለሚያነቡና በቀን ለብዙ ሰዓታት ስለሚጸልዩ ቅዱሳን ሰዎች ታሪክ በማንበብ ወይም በመስማት በነርሱ ተግባር በመነሳሳት ተመሳሳይ ልማድ ለማዳበር ይሞክራሉ፡፡ በቅፅበት ያንን የሚመስል መንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ መግባት የሚችሉ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ አብዛኞቻችን ያንን ማድረግ አንችልም፡፡ ያ […]

The post የክርስቲያን ጉዞ በዝግታ … ያለማቋረጥ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ክርስቲያናዊ ሕይወት አጭር ሩጫ ሳይሆን ማራቶን ነው፡፡ ማራቶንን ለመሮጥ የሚያስፈልገውን ጥንካሬ ማዳበር ጊዜን ይፈልጋል፡፡ አንዳንድ አማኞች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፎችን ስለሚያነቡና በቀን ለብዙ ሰዓታት ስለሚጸልዩ ቅዱሳን ሰዎች ታሪክ በማንበብ ወይም በመስማት በነርሱ ተግባር በመነሳሳት ተመሳሳይ ልማድ ለማዳበር ይሞክራሉ፡፡ በቅፅበት ያንን የሚመስል መንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ መግባት የሚችሉ ሰዎች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ አብዛኞቻችን ያንን ማድረግ አንችልም፡፡ ያ ደግሞ ምንም ማለት አይደለም፡፡ በቀጣይነት እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ቃሉን እንድናጠናና እንድንጸልይ ይጠብቅብናል፡፡ ነገር ግን ቀስ በቀስ በመጀመር ማሳደግ የተሻለ ነው፡፡

አማኝ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚከተልበት መጠን የዕድገት መጠኑን ይወስናል፡፡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መከተል ሁሌም ቀላል አይደለም ነገር ግን ውጤቱ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ አማኝ ተከታዮቹን ተግባራት በፈጸመ ቁጥር በመንፈሱ ያድጋል፡-

የእግዚአብሔርን ቃል መረዳትና መተግበር

የእግዚአብሔርን ባሕርያት፣ ዓላማውንና መንገዶቹን ባወቅን ቁጥር እናድጋለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ እግዚአብሔር ለኛ ራሱን ለመግለጥ የሚጠቀምበት ዋነኛ መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተሻለ ለማወቅ አማኝ የእግዚአብሔርን ቃል ትርጉም በመስማት፣ በማንበብ፣ በማጥናት፣ በመሸምደድና በማሰላሰል መረዳት ይኖርበታል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፈው ሁለተኛው መልዕክቱ የቃለ እግዚአብሔርን አስፈላጊነት እንዲህ ሲል ገልጿል፡- “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል፡፡” (2ጢሞ. 3፡16-17)

ቃሉን ማጥናት በራሱ የመጨረሻ ጉዳይ አይደለም፡፡ የማጥናት ዓላማ መማርና ማደግ እንጂ እውቀትን ማከማቸት አይደለም፡፡ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ዕውቀት ያላቸውና ሰፊ የሆኑ ንባቦችን የሸመደዱ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር የማያምኑ እንዲሁም እርሱን የመታዘዝ ሐሳብ የሌላቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ያዕቆብ አማኞች የቃሉ ሰሚዎች ብቻ በመሆን ራሳቸውን እንዳያታልሉ ያስጠነቅቃል (ያዕ. 1፡22)፡፡

መጸለይ

እግዚአብሔር ከአማኞች ጋር የሚገናኝበትን ክፍት መስመር አዘጋጅቷል፡፡ ጸሎት ማለት በቀላሉ እግዚአብሔር ሁሌም እንደሚሰማን በማወቅና ዓላማውን ከግብ ሊያደርስ እንዲሁም እኛን የበለጠ ሊጠቅም በሚችልበት ሁኔታ ምላሽ እንደሚሰጠን በማወቅ ከእግዚአብሔር ጋር ንግግር ማድረግ ማለት ነው፡፡ ሆኖም ጸሎት ማለት የገዛ አቅማችንን ካሟጠጥን በኋላ የምንጠቀመው ነገር አይደለም፡፡ ይልቁኑ ለገባንባቸው ሁኔታዎች ሁሉ የምንሰጠው ተፈጥሯዊ ምላሽ ሊሆን ይገባል፡፡ ምሪት ለመጠየቅ፣ ፍላጎቶቻችን እንዲሟሉልንም ሆነ ጥበቃ እንዲደረግልን መጀመርያ ወደ እግዚአብሔር ዘወር ማለት ያስፈልገናል፡፡  ኤፌሶን 6፡18 እንዲህ ይለናል፡- “በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፡፡”

ከአማኞች ጋር ሕብረት ማድረግ

ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ላይ ያለንን ግንኙነት ማደስ ወደጎን ከሰዎች ጋር ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር መንገድ ይጠርጋል፡፡ ሆኖም ይህ ግንኙነት በጋራ ጊዜን በማሳለፍና በክርስቶስ ሆነን የምንካፈለውን ሕይወት በጋራ በማጣጣም እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል፡፡

ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ጋር መሰባሰባችንን እንዳንተው የሚያስጠነቅቀን (ዕብ. 10፡24-25)፡፡ አንዳችን ለሌላችን እናስፈልጋለን፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወት በግል የምንኖረው ሕይወት ሆኖ አልተሠራም፡፡ ከሌሎች አማኞች ጋር በቋሚነት ሕብረት ማድረግ መፅናናትን፣ ተጠሪነትን፣ ትምህርትን፣ መበረታታትን፣ ድጋፍንና አቅጣጫን ይሰጠናል፡፡ አማኝ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሳትፎ ከሌለው የተዛባ አስተሳሰብ፣ የስሜት ድጋፍ ማጣት፣ የደህንነት ስሜት ማጣትና የተጠሪነት አለመኖር ችግሮች ይገጥሙታል፡፡

ሌሎችን ማገልገል

ከሌሎች አማኞች ጋር ጊዜን ከማሳለፍ ባለፈ አንዳችን ሌላችንን ልናገለግል ይገባል፡፡ አሁንም ምሳሌያችን ኢየሱስ ነው፡፡ ለመገልገል ሳይሆን ሌሎችን ለማገልገል እንደመጣ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል፡፡ ኋላ ላይም እርሱ ሲያገለግል እንደነበረው ሁሉ እነርሱም ሌሎችን እንዲያገለግሉ ነግሯቸዋል (ማቴ. 20፡28፣ ዮሐ. 13፡15)፡፡

ሌሎችን ማገልገል እግዚአብሔር ባሕርያችንን ለመቅረፅ የሚጠቀምበት መንገድ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁኑ አገልግሎት ሰጪውንም ሆነ ተቀባዩን የሚጠቅም ነው፡፡ ተቀባዩን የሚጠቅመው ፍላጎቱን በማሟላት ነው፡፡ ሰጪውን ደግሞ የሰዎች ፍላጎት ሲሟላ በመመልከት እንዲደሰት በማድረግና በሌሎች ላይ ተፅዕኖን እንዲያመጣ በመርዳት ነው፡፡ በዚህ ሒደት ውስጥ ሁላችንም በመስጠትና በመቀበል ጫፍ ላይ ስለምንሆን ደስታውን እኩል እንጋራለን፡፡

ለሌሎች የምንሰጠው አብዛኛው አገልግሎት የጀግንነት ተግባርን የሚጠይቅ አይደለም፡፡ በየዕለቱ ፍቅራችንን የምንገልፅባቸው መልካም የማበረታቻ ቃላትን መናገር፣ ሰዎችን ማዳመጥ፣ ምሳ መጋበዝ፣ በጥሩ ዓይን መመልከትና እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ እያደረገ ያለውን ማካፈልን የመሳሰሉ ቀለል ያሉ ተግባራት ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት የዘውትር መልካምነትን ያበረታታል፡- “እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ፡፡” (ገላ. 6፡10)

(“ደቀ መዛሙርትን ማነጽ” በሚል ርዕስ ከተዘጋጀ ጽሑፍ ከመጠነኛ ማሻሻያ ጋር የተወሰደ)

The post የክርስቲያን ጉዞ በዝግታ … ያለማቋረጥ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
የመንፈስ ቅዱስ ሙላት https://deqemezmur.com/2022/09/28/holy-spirit/ Wed, 28 Sep 2022 02:21:44 +0000 https://deqemezmur.com/?p=1928 “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ያላቸው ግንዛቤ በጣም የተዛባ ከመሆኑ የተነሳ ምንም ግንዛቤ የላቸውም ያሰኛል፡፡” መንፈስ ቅዱስ ከሥሉስ ቅዱስ አካላት መካከል አንዱ ነው፤ ልናመልከውና ልንታዘዘው ይገባል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እርሱ ቢሄድ መንፈስ ቅዱስን ስለሚልክላቸው መሄዱ መልካም እንደሆነ ነግሯቸዋል (ዮሐ. 16፡7)፡፡ ጌታ ኢየሱስ ከእነርሱ ተለይቶ እንደሚሄድ በመናገሩ ምክንያት አዝነውና ፈርተው […]

The post የመንፈስ ቅዱስ ሙላት first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
“በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ያላቸው ግንዛቤ በጣም የተዛባ ከመሆኑ የተነሳ ምንም ግንዛቤ የላቸውም ያሰኛል፡፡”

መንፈስ ቅዱስ ከሥሉስ ቅዱስ አካላት መካከል አንዱ ነው፤ ልናመልከውና ልንታዘዘው ይገባል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እርሱ ቢሄድ መንፈስ ቅዱስን ስለሚልክላቸው መሄዱ መልካም እንደሆነ ነግሯቸዋል (ዮሐ. 16፡7)፡፡ ጌታ ኢየሱስ ከእነርሱ ተለይቶ እንደሚሄድ በመናገሩ ምክንያት አዝነውና ፈርተው ለነበሩት ደቀ መዛሙርቱ ይህ ዜና በእጅጉ አስደሳች ነበር፡፡

ደህንነትን በመቀበያው ቅፅበት መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ሕይወት ውስጥ በማደር መዳኑን ያረጋግጥለታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የክርስቶስ መንፈስ በውስጣቸው የማይኖር ሰዎች ክርስቲያኖች አለመሆናቸውን ተናግሯል (ሮሜ 8፡9)፡፡ በአንፃሩ ግን እውነተኛ ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ማህተም እንደታተሙ ተናግሯል (ኤፌ. 1፡13)፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ ብሎ በጻፈ ጊዜ ተመሳሳይ ሐሳብን አስተጋብቷል፡- “ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እርሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን፡፡” (1ዮሐ. 4፡13)

የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ደህንነትን በመቀበያችን ቅፅበት ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አማኞች ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት እንዳለባቸው አጥብቆ ይናገራል፡፡ “በመንፈስ መመላለስ” የሚለው ሐሳብ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሚገኙት መልዕክታት ውስጥ በተደጋጋሚ ተጠቅሶ እንመለከታለን፡፡ “በእምነት መኖር” “ወደ እግዚአብሔር መቅረብ” እንዲሁም “ለእግዚአብሔር መገዛት” የሚሉት አማራጭ ሐረጎች በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ከሚለው ሐሳብ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “በመንፈስ ቅዱስ መሞላት” የሚለው አባባል አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መታጠቃቸውን፣ ጥበብንና ምሪትን ማግኘታቸውን ለመግለፅ የተነገረ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት መንፈስ ቅዱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ በመምጣት ምስክሮቹ ይሆኑ ዘንድ ኃይልን እንደሚሰጣቸው ነግሯቸዋል (ሐዋ. 1፡8)፡፡ ይህ የተስፋ ቃል በበዓለ ሃምሳ ዕለት ተፈፅሟል፡፡ ኤፌሶን 5፡18 ላይ የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር “መንፈስ ይሙላባችሁ …” ይላል፡፡

“መሞላት”

የመንፈስ ቅዱስን ሙላት ለመረዳት ኤፌሶን 5፡18 ላይ የሚገኘው ውስብስብ የሆነው የግሥ አወቃቀር ሊብራራ ይገባል፡፡ በዚህ ኃይለ ቃል ውስጥ የሚገኘው ግሥ አራት ውቅሮች አሉት፡፡ የአማርኛው ትርጉም የግሪኩን ፅንሰ ሐሳብ በቂ በሆነ ሁኔታ ስላላስቀመጠ በጥልቀት ማጥናት ይኖርብናል፡፡

ትዕዛዝ፡- መሞላት ትዕዛዝ ነው

ይህ ትዕዛዝ አማኝ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላ ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ያሳያል፡፡ መሞላት ምርጫ ሳይሆን የአማኝ ሕይወት አካል ነው፡፡ ለአማኝ መንፈስ ቅዱስን ሳይሞላ የክርስትናን ሕይወት መኖር መሞከር ጥልቅ ዋናተኛ የአየር መስጫውን ሳይከፍት ውኀ ስር እንደመጥለቅ ነው፡፡

ብዙ ቁጥር፡- ትዕዛዙ አማኞችን ሁሉ ይመለከታል

ኤፌሶን 5፡18 ላይ “ይሙላባችሁ” ብሎ ሲናገር የብዙ ቁጥርን አመላካች ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው ትዕዛዙ የተሰጠው ለአንድ ሰው ወይንም ለተወሰነ ቡድን ሳይሆን ለመላው ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ነው፡፡ ይህ ትዕዛዘት ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ወንድ፣ ሴት፣ ጠንካራ፣ ደካማ፣ በሳል፣ ለጋ ሳይል ሁሉንም አማኞች የሚያጠቃልል ነው፡፡

በመንፈስ ቅዱስ መሞላት በክርስትና ከመብሰል ጋር አንድ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፤ ነገር ግን የብስለት ሒደቱ ቁልፍ አካል ነው፡፡ አንድ ሰው በሳል ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ሊሞላ ይችላል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ያለማቋረጥ በሕይወቱ ውስጥ ሳይሠራ በክርስቶስ ወዳለው ብስለት ሊደርስ የሚችል ማንም የለም፡፡

ተግባር ተቀባይ፡- መሞላቱ በኛ ሊፈፀም አይችልም

“ይሙላባችሁ” የሚለው ተግባር ተቀባይ መሆንን በሚያሳይ ሁኔታ ሲተረጎም “መንፈሱ ራሱ እናንተን ይሙላችሁ” የሚል አንድምታ ነው ያለው፡፡ በሌላ አባባል እግዚአብሔር ራሱ ሊያደርግልን የሚሻው ነገር ነው፡፡ መጀመርያ እኛ እንድናሟላው የሚጠበቅብን አስቸጋሪ መስፈርት የለም፡፡ ምጡቅ የሆነ ደረጃ ላይ መድረስ አይጠበቅብንም፤ የሆነ ዓይነት ዕውቀት ማግኘት አይጠበቅብንም፤ የሆኑ ቴክኒኮችን መማር አያስፈልገንም፤ እግዚአብሔር በመንፈሱ ሊሞላን ብቻ ነው የሚገባው፡፡

የአሁን፡- ሙላቱ ቀጣይነት ያለው ሊሆን ይገባል

ግሡ የአሁን ጊዜን ገላጭ ነው፡፡ አባባሉ በግሪክ ቋንቋ ድርጊቱ አሁንም አሁንም ሳያቋርጥ መደጋገሙን የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በእግዚአብሔር ላይ በመደገፍ ሳይቋረጥ ሊከናወን ይገባል፡፡

“ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው” (ዮሐ. 3፡8)። በደህንነት ውስጥ ምስጢራዊ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ አሠራር እንዳለ ሁሉ በየዕለቱ በሚደረገው የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ረገድም ሙሉ በሙሉ ሊብራራ የማይችል ምስጢር አለ፡፡ ሆኖም ሁለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ መርሆችን በመረዳት አንድ ሰው በመንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደሚሞላ መረዳት እንችላለን፡፡ እነዚህም ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ለእግዚአብሔር መገዛት ናቸው፡፡

ወደ እግዚአብሔር መቅረብ

ክርስትና በባሕርዩ ከክርስቶስ ጋር ሕብረት ማድረግ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ እንደ አዲስ በመወለድ ከእርሱ ጋር ሕብረት እንጀምራለን፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወት ያንን ሕብረት ማጥበቅ፣ ማጥለቅና ማስፋት ነው፡፡ ሁሉም ክርስቲያናዊ ዕድገት መሠረቱ ይህ ሕብረት ነው፡፡ ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ከኢየሱስ ጋር ካለን ሕብረት ይመነጫል፡፡

ዮሐንስ 7፡37-39 በመንፈስ ቅዱስ ሙላትና ከክርስቶስ ጋር ባለን ሕብረት መካከል ስለሚገኘው ግንኙነት አፅንዖት ሰጥቶ ይናገራል፡፡

“ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፡፡ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ፡፡ ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና፡፡”

ኢየሱስ አማኞች ከእርሱ ጋር ሕብረት በማድረግ በመንፈስ ቅዱስ እንደሞሉ ጥሪ አቅርቦላቸዋል፡፡ ይህ ጥሪ በዮሐንስ 7፡37-39 ላይ በሚገኙት ሦስት ንግግሮች ተገልጧል፡፡ እነዚህንም እንደሚከተለው እናያለን፡-

“ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣ”

ጥማት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ አካላዊ ጥማት ሰውነታችን እርካታ እንደሚያስፈልገው እንደሚያመለክተው ሁሉ መንፈሳዊ ጥማትም የሚያስፈልገንን ነገር አመላካች ነው፡፡ መንፈሳዊ ጥማታችንን ማወቅ ወደ ክርስቶስ እንድንመጣ ያደርገናል፡፡

ይህንን ጥልቅ የነፍስ ጥማታችንን ለማርካት ወደ ኢየሱስ መምጣት ግድ ይለናል፡፡ ማንም ሰው ወይንም የትኛውም ነገር ይህንን ጥማታችንን ሊያረካልን አይችልም፡፡ “ይምጣ” የሚለው ቃል የማያቋርጥ ድርጊትን አመላካች ሲሆን ወደ ኢየሱስ ደጋግመን መምጣት እንዳለብን ያሳያል፡፡ ይህ መንፈሳዊ ጥማት እንደ ሥጋዊ ጥማት ሁሉ ደጋግሞ መርካት ያስፈልገዋል፡፡ ይህ እውነታ መንፈሳዊ ጥማት ከደህንነት በፊትም ሆነ በኋላ እንዳለ እንደሚቀጥል ያሳየናል፡፡ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያጣጥሙ ቢሆኑም ይህ ግንኙነት ግን በኛ ኃጢአትና በወደቀው ዓለም ውስጥ በመኖራችን ምክንያት ጥቃት ይደርስበታል፡፡

ጌታ ኢየሱስ ወደ እርሱ እንድንመጣ ከመጋበዝ ውጪ እንደማያስገድደን ልብ በሉ፡፡ በእርሱ መንገድ እንድንሄድ አያስገድደንም ነገር ግን ወደ እርሱ በመምጣት ከእርሱ ጋር እንድንኖርና የዘላለምን ሕይወት እንድንቋደስ ዕድልን ይሰጠናል፡፡ ይህ አቋም ከባሕርዩ ጋርና ግብረ ገባዊ ፍጥረታት አድርጎ እኛን ከመፍጠሩ ጋር የሚጣጣም ነው፡፡ ከልቡ ይፈልገናል ደግሞም ወደ እርሱ እንድንመጣ ይጓጓል፡፡ የእግዚአብሔር “የግብዣ” ባሕርይ በመጽሐፍ ቅዱስ የደህንነት አስተምህሮ ውስጥ ድርና ማግ ሆኖ እንመለከታለን፡፡

“ይጠጣ”

ወደ ክርስቶስ ከመጣን በኋላ ከእርሱ መጠጣት ያስፈልገናል፡፡ የምንጠጣውም በሚከተሉት መንገዶች ነው፡-

  • ከእርሱ ጋር መተባበር – ይህ ማለት በመገኘቱ ውስጥ መኖርና ጊዜን ከእርሱ ጋር ማሳለፍ ነው፡፡
  • እርሱን ማምለክ።
  • እርሱን መስማት – ቃሉን ማንበብ፣ በፊቱ በጥሞና መሆን፣ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት በመከተል፡፡
  • ሸክማችንን በእርሱ ላይ መጣል – ስለ ፍላጎታችን፣ ስለ ጉዳታችንና ስለልባችን መሻት በእግዚአብሔር ፊት ቅኖችና ግልፅ በመሆን ነፍሳችንን ለእርሱ መስጠት፤ ያስጨነቀንን ነገር ሁሉ ለእርሱ መንገር፡፡
  • እንዲያገለግለን ለእርሱ መፍቀድ – መንፈሱ ለመንፈሳችን እንዲያገለግል መፍቀድ፣ ፍርሃታችንን እንዲያረግብ፣ ቁስላችንን እንዲያክምና ልባችንን እንዲያበረታ መፍቀድ፡፡

በነዚህ መንገዶች ከክርስቶስ ጋር ጊዜን ስናሳልፍና ከእርሱ ጋር ባለን ግንኙነት ደስ ስንሰኝ መንፈሳዊ ጥማታችንን ሲያረካ እናየዋለን፡፡

“በእኔ የሚያምን”

ማመንን የሚያሳየው ቃል በተደጋጋሚ የሚፈፀምን ተግባር የሚያመለክት ነው፡፡ መጀመርያ ላይ ኢየሱስ ከኃጢአታችን እንዲያድነንና ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት እንዲያድስ ወደ እርሱ እንመጣለን፡፡ ይህ ደግሞ የሚያስፈልገን ትልቁ ነገር ነው፡፡ በየዕለቱ ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ስናጣጥም ኢየሱስ ለሚያስፈልገን ነገር ሁሉ እርሱን እንድንደገፍና እንድንታመን ይነግረናል፡፡

ወደ ኢየሱስ መምጣት፣ ከእርሱ መጠጣትና እርሱን መታመን አማኝ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲትረፈረፍ ያደርገዋል (ቁ. 38)፡፡

ለእግዚአብሔር መገዛት

ለእግዚአብሔር መገዛትና ፈቃዱን ማድረግ በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ሌላው ገፅታ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት የምንችልበት ብቸኛው መንገድ በፈቃዳችን ለእግዚአብሔር በመገዛትና እንዲያበረታንና እንዲመራን ወደ እርሱ በመቅረብ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ አለመታዘዛችንን ለመግለፅ ሁለት ቃላትን ይጠቀማል፡፡ ኤፌሶን 4፡30 ላይ መንፈስ ቅዱስን “እንዳናሳዝን” ተነግሮናል፡፡ በዚያ አውድ ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ አማኞች ሌሎች ሰዎችን በትክክል እንዲንከባከቡ ይመክራቸዋል፡፡ ስለዚህ የተሳሳቱ መንገዶችን መከተል፣ የድፍረት ኃጢአት ማድረግ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለንን ሕብረት ያበላሻሉ፡፡ 1ተሰሎንቄ 5፡19 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ “መንፈስን አታጥፉ” ይላል፡፡ መንፈስን የምናጠፋው እርሱን ከመከተል በማቋረጥና በራሳችን ኃይል የሆነ ነገር ለማድረግ በመሞከር ነው፡፡ እነዚህ ኃጢአቶች አንዳንዴ መንፈስ ቅዱስን የመግፋት ኃጢአቶች ተብለው ይታወቃሉ፡፡

እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ በራሳችን መንገድ ስንሄድ በመንፈስ ቅዱስ እንደገና በመሞላት ወደ መንገዱ መመለስ ግድ ይለናል፡፡ እግዚአብሔር ወደ መንገዱ መመለስን አስቸጋሪ ሥራ አላደረገብንም፡፡ መጀመርያ ያደረግነውን በመናዘዝ ንስሐ መግባት ያስፈልገናል፡፡ መናዘዝ ማለት ያደረግነው ነገር የተሳሳተ መሆኑን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መስማማት ነው (1ዮሐ. 1፡9)፡፡ ንስሐ ማለት ስለ ኃጢአታችን የልብ ለውጥ በማድረግ መንገዳችንን በመተው ወደ እግዚአብሔር መንገድ መመለስ ማለት ነው፡፡ ወደ እግዚአብሔር ስንመለስ በፈቃደኝነት ለእርሱ በመገዛት በመንፈሱ ደግሞ እንዲሞላን በእርሱ መታመን ይኖርብናል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ የእርሱ ፈቃድ በመሆኑ ደግሞ ይሞላናል፡፡

(“ደቀ መዛሙርትን ማነጽ” በሚል ርዕስ ከተዘጋጀ ጽሑፍ ከመጠነኛ ማሻሻያ ጋር የተወሰደ)

The post የመንፈስ ቅዱስ ሙላት first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
የመንፈስ ጠላቶቻችንን መረዳት https://deqemezmur.com/2022/09/28/spiritual-enemies/ Wed, 28 Sep 2022 02:08:36 +0000 https://deqemezmur.com/?p=1924 ልምድ ያላቸው ተዋጊዎች በውጊያ ውስጥ የመጀመርያው መርህ ጠላትን ማወቅ ነው ይላሉ፡፡ ክርስቲያኖች ጠላቶች አሏቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህ ጠላቶች ዓለም፣ ሥጋና ሰይጣን እንደሆኑ ይናገራል፡፡ እነዚህ ጠላቶች ሳያቋርጡ አማኙን ስለሚገዳደሩት መንፈሳዊ ዕድገትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም እነዚህ ጠላቶች የሚያመጡብንን ፈተናዎች ከተጋፈጥን እኛን በማጠንከርና እግዚአብሔርን የሚመስል ባሕርይን እንድናዳብር በመርዳት የዕድገት ምክንያት ሊሆኑን ይችላሉ (ያዕ. 1፡2-4)፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ […]

The post የመንፈስ ጠላቶቻችንን መረዳት first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ልምድ ያላቸው ተዋጊዎች በውጊያ ውስጥ የመጀመርያው መርህ ጠላትን ማወቅ ነው ይላሉ፡፡ ክርስቲያኖች ጠላቶች አሏቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህ ጠላቶች ዓለም፣ ሥጋና ሰይጣን እንደሆኑ ይናገራል፡፡ እነዚህ ጠላቶች ሳያቋርጡ አማኙን ስለሚገዳደሩት መንፈሳዊ ዕድገትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም እነዚህ ጠላቶች የሚያመጡብንን ፈተናዎች ከተጋፈጥን እኛን በማጠንከርና እግዚአብሔርን የሚመስል ባሕርይን እንድናዳብር በመርዳት የዕድገት ምክንያት ሊሆኑን ይችላሉ (ያዕ. 1፡2-4)፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ሦስቱ ጠላቶቻችን እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

ዓለም

አማኝ የሚጋፈጠው የመጀመርያው ጠላት ዓለም ነው፡፡ ዓለም ስንል በዙርያችን ያለውን ቁሳዊ ከባቢ ማለታችን አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዓለም” የሚለው ቃል ቁሳዊውን ከባቢ ብቻ ሳይሆን ክፉ ግዛትንም ጭምር ነው፡፡ እርሱም በሰይጣን የሚመራው ግዛት (ኤፌ. 2፡2) እንዲሁም ከእግዚአብሔር በተለየውና እግዚአብሔርን በሚጠላው ሕዝብ የተያዘው ሥርዓት ነው (ቆላ. 1፡21)፡፡ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥቱን በሙላት ለመመሥረት ወደ ምድር ሲመለስ ይህ ክፉ ግዛት ይጠፋል፡፡

አንድ ሰው ክርስቶስን እንደ አዳኙ ሲታመን ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማው መንግሥት ወደ ብርሃን ይሸጋገራል፡፡ አማኞች የዚህ ዓለም ግዛት አካል አይደሉም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች ናቸው (ቆላ. 1፡13-14፣ 21-22)፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ እንግዶችና መጻተኞች መሆናችንን ያሳስበናል (1ጴጥ. 2፡11)፡፡

አማኞች የእግዚአብሔር መንግሥት አባላት ቢሆኑም በዚህ ክፉ ዓለም ውስጥ ስለምንኖር ተፅዕኖ ያሳድርብናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ይህ ክፉ ዓለም በሥጋዊ እርካታ ምኞት፣ በዓይን አምሮትና ስለ ገንዘብ በመመካት የተያዘ ነው (1ዮሐ. 2፡15-17)፡፡ ወይንም ደግሞ ቻርለስ ዝዊንዶል የተሰኘ ደራሲ እንዳስቀመጠው “የዓለም ሥርዓት በአራት ቃላት ልንገልፃቸው በምችላቸው አራት ነገሮች የተያዘ ነው፤ እነርሱም ገንዘብ፣ ዝና፣ ሥልጣንና ደስታ ናቸው፡፡”

ሕይወታቸውን በእነዚህ አራቱ ነገሮች በሚመሩ አላማኞች ተከበናል፤ ነገር ግን እንደ ሰማይ ዜጎች ማዕበሉ ወደሚነጉድበት አቅጣጫ እንዳንወሰድ መጠንቀቅ ያስፈልገናል፡፡ በውጤቱም ከአቋማችን የተነሳ ልንሰደድና ጉዳት ሊደርስብን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሆነ ብለው ሊያሳድዱን ይችላሉ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሥርዓቱ ጋር ባለመስማማታችን ምክንያት ልንጎዳ እንችላለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይህ ተቃውሞ በማላገጥ ሊገለጥ ይችላል፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ግልጽ የሆነ ጥቃት ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከብቸኝነት ስሜት ጋር መታገል ያስፈልገናል፡፡ ጤናማ ባልሆኑ ግንኙነቶች፣ ጎጂ ጸባዮችና ሌሎች የኃጢአት ውጤቶች በሚታይበት ዓለም ውስጥ መኖሩ በራሱ ትልቅ የህመም ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡

1ዮሐንስ 2፡15-17 ላይ አማኞች ዓለምን ባለመውደድ ከእርሱ ራሳችንን እንድነጠብቅ ተነግሮናል፡፡ አንዳንድ አማኞች የምንኖርበትን ምድራዊ መንግሥት በተመለከተ አቋማችን ምን መሆን እንዳለበት ግራ ይገባቸዋል፡፡ ለእግዚአብሔር የተሻለው መንገድ ከዚህች ምድር መነጠል እንደሆነ ያስባሉ፡፡ አማኝ ካልሆኑት ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው እንደማይገባ የሚያምኑ ሲሆን ከዓለም ጋር እንደሚያመቻምቹ የሚያስቧቸውን አማኞች ይነቅፋሉ፡፡ የሚገርመው ነገር ኢየሱስም በዘመኑ ከነበሩት የሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ተመሳሳይ ትችት ደርሶበት ነበር፡፡ እንደ እግዚአብሔር ልጆችና የመንግሥቱ ዜጎች በማያምኑት ሕዝቦች መካከል ተፅዕኖን ልናሳርፍ ይገባናል፡፡ ዓለም ክፋትን እንድናደርግ ተፅዕኖ ሊያሳርፍብን አይገባም ነገር ግን የእግዚአብሔር አምባሳደሮች በመሆን በዚህ ዓለም ላይ ተፅዕኖን ልናመጣ ይገባናል፡፡

ሥጋ

ሁለተኛው የክርስቲያን ጠላት ሥጋ ነው፡፡ እኛ የሰው ልጆች የእግዚአብሔርን ፍጥረት ለመበከልና በቆሻሻ ለመሙላት ብዙ እንደሠራን ሁሉ በውስጣችን የሚገኘውን የእግዚአብሔርን አዲስ ፍጥረት ለመበከልና ለማበላሸት የሚሞክር ኃጢአተኛ ባሕርይ በውስጣችን አለ፡፡ ጠላታችን በውስጣችን ይኖራል፡፡

ሁሉም የሰው ልጆች ከኃጢአት ባሕርይ ጋር ነው የሚወለዱት፡፡ ይህ የኃጢአት ባሕርይ ከተሳሳተ አስተሳሰብና ከመጥፎ ልማድ ያለፈ ነው፡፡ እግዚአብሔርንና ጽድቁን እንድንቃወም የሚያደርገን ውስጣዊ ጥመትና ፍላጎት ነው፡፡ ታዋቂ ክርስቲያን ጸሐፊ የሆነው ጄ. ኦስዋልድ ሳንደርስ እንዲህ ሲል ጽፏል፡-  “ሥጋ በሰው ተፈጥሮ ውስጥ የሚገኝ ክፉ መሻት፣ ከአጥቂዎቻችን ጋር የሚተባበር ክፉ ከዳተኛ ነው፡፡ ሥጋ የዲያብሎስ ፈተና የሚቀመጥበትን ጎጆ ይሰጠዋል፡፡” የኢየሱስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ በራሳችን ምኞች ተስበን ኃጢአትን እንደምናደርግ በመናገር የሥጋችንን ተፅዕኖ ገልጿል (ያዕ. 1፡4)፡፡

የማያምን ሰው በዚህ የኃጢአት ባሕርይ ቁጥጥር ስር ነው፡፡ ክርስቲያን ኃጢአተኛ ባሕርይ አለው ስለዚህ ይህ ባሕርይ በሞት ጊዜ ግብዓተ መሬቱ እስኪፈፀም ድረስ ሊታገለው ይገባል፡፡ ክርስቲያን ከዚህ ኃጢአተኛ ባሕርይ ጋር መታገል ቢኖርበትም በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት በመሆን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሏል፡፡ በውስጡ በሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካይነት ኃጢአተኛ ባሕርይን በየትኛውም ጊዜ ልናሸንፍ እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስና ኃጢአተኛ ባሕርይ ተቃራኒ ስለሆኑ አንዱን እያስተናገድን በሌላው መኖር አንችልም፡፡ “በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ፡፡” (ገላ. 5፡16)

አማኞች ከዓለም ራሳቸውን የሚጠብቁባቸውን መንገዶች እንደተሰጡት ሁሉ ከኃጢአተኛ ባሕርይም የሚጠበቁባቸውን መንገዶች ተሰጥተዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው አማኝ በየትኛውም ሰዓት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካይነት ኃጢአተኛ ባሕርዩን ማሸነፍ ይችላል (ገላ. 5፡16፣ ሮሜ 8፡13)፡፡ ኃጢአተኛ ባሕርይ አማኝ በሥጋው እስኪሞት ድረስ በውስጡ የሚኖር በመሆኑ ከኃጢአተኛ ባሕርይ ጋር የሚደረግ ፍልሚያ እስከ ዕድሜ ልካችን ድረስ ይቀጥላል፡፡ ስለዚህ አማኝ (አዲስም ይሁን በሳል አማኝ) ንቁ መሆኑና በመንፈስ ቅዱስ መሞላቱ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

ዲያብሎስ

ሦስተኛው ጠላታችን ዲያብሎስ ነው፡፡ ቀንድ ያለው መንሽ የያዘ የካርቱን ምስል ከመሆን በተለየ ሁኔታ ዲያብሎስ ትክክለኛ ጠላት ነው፣ አደገኛ ጠላት ነው፣ እኛን ለመጉዳትም ይፈልጋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስ ከመስመር የወጡ ክርስቲያኖችን ይዞ ለማጥፋት እንደሚያደባ ይናገራል፡፡ ዲያብሎስና በማይታየው ዓለም ውስጥ የሚገኙ በእርሱ ትዕዛዝ ስር ያሉ እርኩሳን መናፍስት ክርስቲያኖችን አምርረው ይጠላሉ፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የእርሱ ጠላት ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር ስለወገንን ነው፡፡ ዲያብሎስ በአንድ ወቅት ትልቅ ሥልጣን ያለው መልአክ የነበረ ቢሆንም በእግዚአብሔር ላይ አመፀ፡፡ አሁን የክፋት ሁሉ ቋት በመሆን እግዚአብሔርንና ሥራውን ሁሉ የሚቃወም ሆኗል፡፡

ፍፁም የሆነውን ዓላማውን ከግብ ለማድረስ እግዚአብሔር ዲያብሎ ለተወሰነ ዘመን የተወሰነ ሥልጣን እንዲኖረው ፈቅዷል፡፡ ዲያብሎስና ተባባሪዎቹ አንድ ቀን አቅማቸውን ሁሉ በመገፈፍ ለዘላለም ወደሚሠቃዩበት የእሳት ባሕር ውስጥ ይጣላሉ፡፡ የታሪኩ የመጨረሻ ምዕራፍ አስቀድሞ ተጽፎ ስለተጠናቀቀ ክርስቲያኖች ማን ያሸንፋል ብለው መጨነቅ የለባቸውም፡፡

አሁን ግን አማኝ ይህንን ጠላት መጋፈጥ ይኖርበታል፡፡ ንቁ በመሆን ሰይጣን ጥቃት ሲፈፅም ማወቅ ይኖርበታል፡፡ አሁንም አማኝ አቅመ ቢስ ሳይሆን የዲያብሎስን ጥቃት የሚቋቋምበት ኃይል ተሰጥቶታል፡፡ ጴጥሮስ ጸንተን ዲያብሎስን ልንቃወመው እንደሚገባ ጽፏል (1ጴጥ. 5፡8-9)፡፡ ያዕቆብም ለመጀመርያዎቹ አማኞች “ዲያብሎስን ተቃወሙት ከእናንተም ይሸሻል” በማለት ጽፏል (ያዕ. 4፡7)፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን ለነበሩት ክርስቲያኖች በጻፈው መልዕክት ውስጥ ዲያብሎስን ለመቋቋም ስለተሰጡን መሣርያዎች በጥልቀት ይናገራል (ኤፌ. 6፡13-18)፡፡ የእውነት መታጠቂያ፣ የፅድቅ ጥሩር፣ የእምነት ጋሻ፣ የመንፈስ ሰይፍና የመሳሰሉት ትጥቆች የተሰጡን “የዲያብሎስን ሽንገላ መቃወም እንችል ዘንድ” እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የዲያብሎስ የተወደደ አንዱ ስልት በክርስቲያኖች አእምሮ ውስጥ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ማድረግ ነው፡፡ ሰይጣን የሐሰት አባት በመባል ነው የሚታወቀው (ዮሐ. 8፡44)፡፡ እውነትን በማጣመም ደግሞ የተካነ ነው፡፡ ይህ ከመጀመርያው ጀምሮ ሲጠቀምበት የነበረ አካሄድ ነው፡፡ ሔዋንን ያሳሳታት እውነትን በማጣመም የእግዚአብሔርን መልካምነት እንድትጠራጠር በማድረግ ነበር፡፡ ዛሬም ተመሳሳይ የሆነ ዘዴን በአማኞች ላይ ይጠቀማል፡፡ የዲያብሎስን ሐሰት በመስማት መጥፎ የሆኑ ሁኔታዎች ሐሳባችንን እንዲወስዱት ከፈቀድን የእግዚአብሔርን መልካምነት ወይም ኃይል ልንጠራጠር እንችላለን፡፡ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በመሰወርና ራሳችንን በእውነት በማስታጠቅ እንዲሁም በመጸለይ የእግዚአብሔርን እውነት ከጠላት ውሸት ልንለይ ይገባናል፡፡

በአሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን የተሓድሶ ሰው በማርቲን ሉተር የተጻፈው አምላካችን ፅኑ ምሽጋችን የሚለው ዝማሬ በሃያ አንደኛው ክፍለ የሚገኙትን አማኞች ማፅናናቱን ቀጥሏል፡፡ ከግጥሙ ላይ የጠወሰዱት የተወሰብኑ ስንኞች እንዲህ ይላሉ፡- “ያ ጥንታዊው ጠላታችን፣ ይፈልጋል ዛሬም ሊያጠፋን፣ ክፋቱና ኃይሉ ትልቅ፣ ጥላቻም የእርሱ ትጥቅ፣ በምድር የለም ከእርሱ የሚልቅ፡፡ ይህ ዓለም በዲያብሎስ ቢሞላም፣ ሊያስፈራራን ቢሞክርም፣ እግዚአብሔር እውነት ድል እንዲነሳ ስለወደደ እኛ አንፈራም፡፡ የጨለማው ንጉሥ ያጓራል፣ ልባችን መች እርሱን ይፈራል፣ ቁጣው አይችልም ሊያጠፋን፡፡ መጥፊያው እርግጥ ነው፣ ዓለም ሊደፋበት ነው፡፡” በዚህ ግጥም ውስጥ ስለ ጠላት ኃይል ማሳሰብያ ተሰጥቶናል፡፡ ከሁሉ በላይ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የምናገኘው ድል ተነግሮናል፡፡

ማጠቃለያ – ከአሸናፊዎች በላይ

ጠላቶቻችንን በዚህ ምድር ላይ እንዴት ድል እንደምንነሳ መማር ወሳኝ የሆነ የመንፈሳዊ ዕድገት አካል ነው፡፡ አማኝ ስለ ጠላቶቹ ማወቅና በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሱትን መሣርያዎች መጠቀም ይኖርበታል፡፡ ውጊያው ውስጥ ስንገባ በቃለ እግዚአብሔር የሰጠንን ተስፋ አጥብቀን ልንይዝ ይገባናል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቱ ስምንተኛው ምዕራፍ ላይ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፡- “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?” ሊያሸንፉን የሚችሉ ብዙ ነገሮችን ከዘረዘረ በኋላ ሐዋርያው ጳውሎስ “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” በማለት ይደመድማል (ሮሜ 8፡37)፡፡ ከዚያም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም ዓይነት ፍጥረት እንደሌለ በማረጋገጥ ይደመድማል (ሮሜ 8፡39)፡፡

(“ደቀ መዛሙርትን ማነጽ” በሚል ርዕስ ከተዘጋጀ ጽሑፍ ከመጠነኛ ማሻሻያ ጋር የተወሰደ)

The post የመንፈስ ጠላቶቻችንን መረዳት first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
በጸሎት ማደግ https://deqemezmur.com/2022/09/28/betselot-madeg/ Wed, 28 Sep 2022 01:53:03 +0000 https://deqemezmur.com/?p=1918 እግዚአብሔር ሁል ጊዜ የሚገኝና ከኛ ጋር ሕብረት ማድረግ የሚፈልግ አምላክ ነው፡፡ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ እጅግ ወሳኝ መንገድ ነው (ያዕ. 4፡8)፤ ለፈቃዱ ይበልጥ ጥማት እንዲኖረን ያደርጋል (ማቴ. 6፡10)፡፡ ጌታችን ኢየሱስ አስደናቂ የጸሎት ሕይወት ነበረው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሌሊቱን ሙሉ በጸሎት ሲያሳልፍ አይተውታል፡፡ ኢየሱስ የተካነ “የጸሎት ወታደር” ነበር፡፡ እንዴት መጸለይ እንዳለብንም አስተምሮናል፡፡ ስለዚህ እስኪ ከባለሙያው እንማር፡፡ የኢየሱስ […]

The post በጸሎት ማደግ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
እግዚአብሔር ሁል ጊዜ የሚገኝና ከኛ ጋር ሕብረት ማድረግ የሚፈልግ አምላክ ነው፡፡ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ እጅግ ወሳኝ መንገድ ነው (ያዕ. 4፡8)፤ ለፈቃዱ ይበልጥ ጥማት እንዲኖረን ያደርጋል (ማቴ. 6፡10)፡፡

ጌታችን ኢየሱስ አስደናቂ የጸሎት ሕይወት ነበረው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሌሊቱን ሙሉ በጸሎት ሲያሳልፍ አይተውታል፡፡ ኢየሱስ የተካነ “የጸሎት ወታደር” ነበር፡፡ እንዴት መጸለይ እንዳለብንም አስተምሮናል፡፡ ስለዚህ እስኪ ከባለሙያው እንማር፡፡

የኢየሱስ የጸሎት ሞዴል

ኢየሱስ የጸሎት መመርያ የሚሆነንን “የጌታ ጸሎት” ብለን የምንጠራውን ጸሎት አስተምሮናል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይህንን ጸሎት ስንጸልይ በጋራ ለማምለክ ብቻ አይደለም፡፡ ለግል የጸሎት ሕይወታችን እንደ ንድፍ ልንጠቀመው እንችላለን፡፡

ማቴዎስ 6፡9-13 ላይ የሚገኘውን የጌታን ጸሎት ስንመለከት ተቀዳሚው ተግባራችን እግዚአብሔርን ማመስገንና ማምለክ መሆኑን እናስተውላለን፡፡ ወደ ሰማዩ አባታችን እንጸልያለን፤ እናመልከዋለን፡፡

ፈቃዱን በምድር ላይ እንዲፈፅም እንጸልያለን፡፡

አባታችን በየዕለቱ የሚያስፈልገንን እንጀራ እንዲሰጠንና እንዲመግበንም እንጸልያለን፡፡ ኃጢአታችንን ይቅር እንዲለን እንጸልያለን፤ የበደሉንንም ይቅር እንድንል እንደሚጠብቅብንም እናስተውላለን፡፡ ከፈተና እንዲያድነንና ከክፉ እንዲጠብቀን እንጠይቀዋለን፡፡

እግዚአብሔር በቃሉና በጸሎት ከኛ ጋር ሕብረት ማድረግ ይፈልጋል፡፡ ቃሉን እንድንረዳና በጸሎት ከእርሱ ጋር እንድንገናኝ መንፈስ ቅዱስን ሰጥቶናል፡፡

The post በጸሎት ማደግ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
በቃሉ ማደግ https://deqemezmur.com/2022/09/28/bekalu-madeg/ Wed, 28 Sep 2022 01:45:16 +0000 https://deqemezmur.com/?p=1914 የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለአማኞች ከሚናገርባቸው መንገዶች መካከል ዋነኛውና መሠረታዊው ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከእግዚአብሔር ለመስማት በሌሎች መንገዶች ላይ ይደገፋሉ፡፡ አንዳንዶች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመለየት የውስጥ ሰላማቸውን ያዳምጣሉ ወይም ሁኔታዎችን ብቻ ይመለከታሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ዋነኛ የመናገርያ መንገዱ ቃሉ ነው፡፡ “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና […]

The post በቃሉ ማደግ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለአማኞች ከሚናገርባቸው መንገዶች መካከል ዋነኛውና መሠረታዊው ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከእግዚአብሔር ለመስማት በሌሎች መንገዶች ላይ ይደገፋሉ፡፡ አንዳንዶች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመለየት የውስጥ ሰላማቸውን ያዳምጣሉ ወይም ሁኔታዎችን ብቻ ይመለከታሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ዋነኛ የመናገርያ መንገዱ ቃሉ ነው፡፡ “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል፡፡” (1ጢሞ. 3፡16-17) የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚነግሩንን ሌሎች መንገዶች የምንመረምርበት ቋሚ መለኪያ ነው፡፡

ለክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ባሕርይ፣ አሠራሩንና የመንግሥቱን መርሆች በማሳወቅ ሕይወታችንንና ውሳኔዎቻችንን ይመራል፡፡ እርሱ ማን እንደሆነ፣ ፈቃዱ ምን እንደሆነና ከእርሱ ጋር እንዴት መገናኘት እንደምንችል የሚያሳውቀንን እጅግ የበለጸገ ዕውቀት ሰጥቶናል (መዝ. 19፡7-11)፡፡ ይህንን በረከት የምንካፈልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ፡-

  1. መስማት፡- የእግዚአብሔር ቃል ሲነበብና ሲብራራ እንሰማለን፡፡
  2. ማንበብ፡- አማኝ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ጊዜ ሲወስድ ከእግዚአብሔር የሚሰማበትን ተጨማሪ ዕድል ያገኛል፡፡
  3. ማጥናት፡- የእግዚአብሔርን ቃል ጠለቅ ባለ ሁኔታ ማጥናት ጊዜና ትዕግስትን ይጠይቃል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛዎችን ወይንም ሌሎች የድጋፍ መሣርያዎችን መጠቀም ጥናታችንን ከፍ ያደርጋል፡፡
  4. ማሰላሰል፡- የንባብ ፍጥነታችንን በመቀነስ ቃሉን ማሰላሰልም በጣም ወሳኝ ነው፡፡
  5. መሸምደድ፡- የእግዚአብሔርን ቃል “በልባችን ውስጥ እንድንሰውር” ተነግሮናል፦ “አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ” (መዝሙር 119:11)። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ” ሲል ይህንኑ ከማሳሰብ አንጻር ነው (ቆላስይስ 3:16)። የመጽሐፍ ቅዱስን ክፍሎች በትውስታ መያዝ ለክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል በሕይወቱ ውስጥ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችል ያሳውቀዋል፡፡ ቃሉን ከሌሎች ጋር እንዲካፈል፣ ከክፉው ፈተና፣ ከሰይጣን ውሸትና ጥቃት ራሱን እንዲከላከል ያግዘዋል፡፡
  6. ቃለ እግዚአብሔርን መተርጎም፡- የእግዚአብሔርን ቃል ስናነብ መንፈሱ እውነትን ማወቅ እንድንችል ልባችንን ይከፍታል፡፡ ነገር ግን ደግሞ ቃሉን የመተርጎም አቅማችን ማደግ ይኖርበታል፡፡ የተለያዩ ክርስቲያኖች አንዱን ቃል በተለያዩ መንገዶች ከመተርጎማቸው የተነሳ ቃሉን የመተርጎም አስፈላጊነትን የሚያጣጥሉ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ ቃሉን በትክክል መተርጎም በግል ስሜት ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ስሜታቸው የእግዚአብሔርን ቃል ለመተርጎም ሥልጣን ያለው ይመስል ስለ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የግል ስሜታቸውን ተንተርሰው ሲናገሩ እንሰማቸዋለን፡፡ እንደርሱ ግን አይደለም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ባለሥልጣን በመሆኑ እኛ እራሳችንን በእርሱ ላይ ባለሥልጣናት አድርገን መሾም አይገባንም፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝ ሁሉም ንባብ አንድ ትርጉም ብቻ ነው ያለው፡፡ እርሱም የመጀመርያው ጸሐፊ እንዲያስተላልፍ የፈለገው መልዕክት ነው፡፡ አንዳንድ ጠቃሚ ምንጮች የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕረ ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒድያ) እና ገላጭ የሆኑ ሐታቾች (ኮሜንተሪዎች) ናቸው፡፡ እነዚህ በክርስቲያናዊ መጻሕፍት መደብር ወይንም በኢንተርኔት ላይ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ለቃሉ ተገቢውን ክብር በመስጠት እንድናነበውና እንድንማረው ዘንድ እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን። አሜን።

(“ደቀ መዛሙርትን ማነጽ” በሚል ርዕስ ከተዘጋጀ ጽሑፍ ከተወሰነ ማሻሻያ ጋር የተወሰደ)

The post በቃሉ ማደግ first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>