Tebebe Mekonnen - ደቀ መዝሙር https://deqemezmur.com ደቀ መዝሙር መሆን ደቀ መዛሙርት ማድረግ Sun, 16 Oct 2022 23:52:11 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=6.5.5 https://deqemezmur.com/wp-content/uploads/2022/08/cropped-photo_2022-08-09_18-28-03-32x32.jpg Tebebe Mekonnen - ደቀ መዝሙር https://deqemezmur.com 32 32 ዝነኝነት ወይንስ ታማኝነት? https://deqemezmur.com/2022/10/16/celebrity-or-loyality/ Sun, 16 Oct 2022 23:44:48 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2148 ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ማቴ 25፥21 “አንተ ታማኝ ባሪያ” መባል ከምንም በላይ ሊያሳስበን የሚገባበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፤ በጌታ ፊት ዋጋ የሚሰጠው ታማኝ ባሪያ መሆን እንጂ ዝነኛ አገልጋል ሆኖ መገኘት አለመሆኑን ልናስተውል ይገባል፤ ታማኝ ሆኖ መገኝትን በተለያየ መልኩ የሚያሳንሱብን፣ ይሄንን ዋና የሆነውን ጥሪ እንዳናይ […]

The post ዝነኝነት ወይንስ ታማኝነት? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ማቴ 25፥21

“አንተ ታማኝ ባሪያ” መባል ከምንም በላይ ሊያሳስበን የሚገባበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፤ በጌታ ፊት ዋጋ የሚሰጠው ታማኝ ባሪያ መሆን እንጂ ዝነኛ አገልጋል ሆኖ መገኘት አለመሆኑን ልናስተውል ይገባል፤ ታማኝ ሆኖ መገኝትን በተለያየ መልኩ የሚያሳንሱብን፣ ይሄንን ዋና የሆነውን ጥሪ እንዳናይ የሚጋርዱን ብዙ አይነት ነገሮች በዙሪያችን ከበውናል፤ በተለይ ዘመን አመጣሹ የሶሻል ሚዲያውም ሆነ እንደ ዝነኛ (Celebrity) ወይንም ፌመስ ዘማሪ፣ ፌመስ ሰባኪ የመደነቅ ነገር ለብዙዎች እንቅፋት እየሆነ ያለንበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፤

ወደ ዝነኝነት የመጡ ሰዎች ብዙ አይነት የሕይወት መንገድ ተጉዘው ወደ ዝነኝነት ማማ ላይ መውጣት የቻሉ ናቸው፤ ይሄ ዋጋ ያስከፈላቸው ጉዞ እና አሁን ያሉበት ክብር (STATUS) በቀላሉ ሊለቁት የማይችሉት ማንነት ሆኖ ያገኙታል፤ ይሄን አይነቱ ዝነኝነት ወደ ቤተ እምነት የገባ አደገኛ የሆነ አካሄድን እየተፈጠረ እንዳለ ማየት ይቻላል፤ እነዚህ በጌታ ቤት በዝነኝነት መንፈስ ራሳቸውን ከፍ ያደረጉ፣ ከመደዴው ምእመን በላይ እንደሆኑ የሚያስቡ፤ ጌታ የሰጣቸው ጸጋ፣ ታማኝ ሊሆኑ የተጠሩለትን ጥሪ ያጎደሉ፣ ቅባታቸው ከተራው አማኝ ተርታ እንዳይመደቡ ከዛም ባለፈ መልኩ የሚቀመጡበት ወንበር የተለየ፣ የሚለብሱት ልብስ በዋጋ የተወደደ አንዳንዶቹም የሚነዱት መኪና ለኔ ቢጤው ደሃ ሲታይ የሚያስደነግጥ እየሆነ ከመጣ ሰንበትበትብሏል፤

በታዋቂነት ማንነት ማገልገል እና ለቃሉ እውነት ታማኝ ሆነን በማገልገል መካከል ያለው መስመር በጣም ስስ ነው፤ በጳውሎስ እና ባርናባስ (ሐሥ 14፥8-19) ያለውን ታሪክ ስንመለከት የሚያስተምረን ነገር አለ፤ ጳውሎስ እና ባርናባስ በበልስጥራን በእነሱ የተደረገው ተአምር ምክንያት “ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ፣ በሊቃኦንያ ቋንቋ፣ “አማልክት በሰው ተመስለው ወደ እኛ ወርደዋል!” ብለው ጮኹ፤” (ሐሥ 14:11) ይሄ የሚያሳየን ቀጣዩ ነገር እነ ጳውሎስን ለየት ያለ ስፍራ መስጠት ከዛ ባለፈ መልኩ ልዩ በሆነ መልኩ እነሱን ትንንሽ አማልክት ማድርገ ማምለክ ነበር የዚያ ከተማነዋሪዎች ፍላጎት። የጳውሎስ እና ባርናባስ ምላሽ ግን ““እናንት ሰዎች፤ ለምን ይህን ታደርጋላችሁ? እኛም እኮ እንደ እናንተው ሰዎች ነን” የሚል ነበር፤ ምክንያቱም ታማኝ ሊሆኑለት የሚገባ ጥሪ የነበራችው ሰዎች ስለነበሩ፤

ይሄን መስመር በምን ያክል እንዳለፍን አንዳንዴ በማይገባን መልኩ አልፈነው ልንገኝ እንችላለን፤ ቤተ ክርስቲያን በተለይ በሰዎች ዘንድ የተለየ ዝነኝነት ያተረፉ ሰዎች እንዲያገለግሉም ሆነ በመድረኮቻቸው እንዲገኙ ሲሽቀዳድሙ መመልከት ለዚህ አይነቱ ችግር የበለጠ መባባስ ምክንያት ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ ነው፤ “ከልካችን ያለፈ ጉርሻ መዋጥ ትንታ ያተርፋል። እግዚአብሔር በሰጠን ልክ ለክብሩ በመኖር ፈንታ የየራሳችን ትንንሽ ጣዖታት ለመሆን ባንጋጠጥን ጊዜ በድንገት መፈንገልን እናተርፋለን።” (የዱባ ጥጋብ ገጽ 118 በሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን)

ዝነኛ ሰዎች በተለየ መልኩ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ እንዲታወቅ የተለየ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብዬ አላምንም፤ ነገር ግን በእነዚሁ ሰዎች አማካኝነት ጌታ አይሠራም ማለቴም እንዳልሆነ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ፤ በጣም ጌታን የሚፈሩ በታማኝነት እርሱንና እርሱን ብቻ የሚያገለግሉ፣ በሚያገለግሉት ጌታም ሆነ የአገልግሎታቸውን በረከት ተካፋይ በሆነ አማኝ መካከል ስፍራ ያላቸው ወገኖችም እንዳሉ ማሰብ ተገቢ እንደ ሆነ አምናለሁ፤ “በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ።” (ቆላ 4፥17) ብሎ ጳውሎስ ለአክሪጳ እንዳስጠነቀቀው በዙሪያቸው የሚታየው ግርግር እና ጭብጨባ ሳይሆን ለተቀበለው አገልግሎት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያስጠነቅቀዋል፤

‘ከዚህም የተነሣ ዝናው በመላዋ ሶርያ ተሰማ፤ ‘ማቴዎስ 4:24

በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት እየሆነ ከነበረው ነገር የተነሳ ለየት ያለ እውቅናን አግኝቶ ነበር፣ ከመታወቅም አልፎ እንደውም ስላበላቸው ስላጠጣቸው፤ “’ኢየሱስም ሰዎቹ መጥተው በግድ ሊያነግሡት እንዳሰቡ ዐውቆ እንደ ገና ብቻውን ወደ ተራራ ገለል አለ።” (ዮሐንስ 6:15) በዚህ የዮሐንስ ወንጌል ታሪክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባደረገው ነገር ዝናን አትርፎ ነበር ነገር ግን ከዝነኝነት የተነሳ የሚመጣ ክብር ከሚያስገኝልን ምስጋና ይልቅ ይዞብን የሚመጣው ጣጣ ብዙ መሆኑን ሊያስተምረን ስለፈለገ ራሱን ገለል አደረገ እንጂ ለማሱ (ለብዙሃኑ) ግርግር ራሱን አልሰጠም፤

ራስን እንደ ማወቅ እና ራስን እንደ መሆን ትልቅ ነገር የለም፤ ይሄ በሕይወታችን መሆን ሲችል ያን ጊዜ ለታማኝነት የቀረበ ልቦናን እናገኛለን፤ ራሳችንን መሆን የሚያስችለን ብቸኛው ነገር ለእግዚአብሔር ቃል የተጠጋ ማንነት ሲኖረን ነው፤ የቃሉ መስታወት ማንነታችንን ለራሳችን በማጋለጥ ልካችንን እንድናይ ያደርገናል እግዚአብሔርን የትኛውንም ያክል ብናውቀው ልንላመደው አንችልም ለዚህ ነው ራስን ማወቅ ልክን ማወቅ ነው። ጌታ ጌታ  ነው እኛ እኛ ነን፤ ጴጥሮስ ከጌታ ኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ስለ ራሱ ያለው እይታ ለየት ያለ መሆን ችሎ ነበር፤ በፊት ፈጠን ፈጠን ይል የነበረው አሁን ግን “…..ጌታ ሆይ፤ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድድህም ታውቃለህ” አለው።” ወደሚለው ራስን ወደማወቅ መጣ፤ (ዮሐ 21፥17)

የተቀበልነው አደራ ተጠያቂነት ያለበት ስለሆነ ታማኝነት ግድ ይላል፤ ልባም ባሪያ ሆነን ስንገኝ የተሰጠንን አደራ ለተደራሹ እንደሚገባ ተጠንቅቀን እናደርሳለን፤ ለዚህ አይነቱ ባሪያ ትልቁ ትኩረት ተደራሹ አይደለም አደራ የሰጠው ነው ትልቅ ስፍራ ያለው!! “’ጌታም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እንግዲህ፣ ምግባቸውን በተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው፣ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ብልኅ መጋቢ ማነው? ‘ሉቃስ 12:42

የተቀበልነው አደራ ራሳችንን ልናሳይበት ሳይሆን ልንጠነቀቅለት፣ ራሳችንን እኛነታችንን ዝቅ ልናደርግለት፣ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በምድረበዳ የምንጮህ ድምጽ የምንሆንለት እንጂ የምንታይ ዝነኞች እንዳልሆንን ሊገባን በዚህ መልኩ ራሳችንን ልናውቅ ይገባል፤

‘እርሱ ሊልቅ፣ እኔ ግን ላንስ ይገባል። ‘ዮሐንስ 3:30

 

The post ዝነኝነት ወይንስ ታማኝነት? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ሰልፊ (እኔው፣ ከኔው፣ ለኔው፣ በኔው) https://deqemezmur.com/2022/10/01/selfie/ Sat, 01 Oct 2022 19:13:02 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2017 ሰልፊ የኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት የ2013 የዓመቱ ቃል ለመባል የበቃ ዘመነኛ ቃል ነው፤ ትርጉሙ አንድ ሰው ራሱን በተለይ በስማርት ፎን ወይም በዌብ ካም ራሱን በራሱ ፎቶ ካነሳ በኋላ በመገናኛ ብዙሃን (ሶሻል ሚድያ) ገጾች ላይ በመጫን ራሱን ሲያስተዋውቅ እንደማለት ነው። ሰዎች ሰልፊ በማድረግ በፌስቡክም ሆነ በየትኛውም የመገናኛ ብዙሃን (ሶሻል ሚዲያ) በማውጣታቸው ምንም ችግር የለውም (በግሌ ክፋቱን አላይም)። በጨዋደንብና ስርዓት […]

The post ሰልፊ (እኔው፣ ከኔው፣ ለኔው፣ በኔው) first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ሰልፊ የኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት የ2013 የዓመቱ ቃል ለመባል የበቃ ዘመነኛ ቃል ነው፤ ትርጉሙ አንድ ሰው ራሱን በተለይ በስማርት ፎን ወይም በዌብ ካም ራሱን በራሱ ፎቶ ካነሳ በኋላ በመገናኛ ብዙሃን (ሶሻል ሚድያ) ገጾች ላይ በመጫን ራሱን ሲያስተዋውቅ እንደማለት ነው።

ሰዎች ሰልፊ በማድረግ በፌስቡክም ሆነ በየትኛውም የመገናኛ ብዙሃን (ሶሻል ሚዲያ) በማውጣታቸው ምንም ችግር የለውም (በግሌ ክፋቱን አላይም)። በጨዋደንብና ስርዓት የጠበቀ እስከሆነ ድረስ ማለቴ ነው።
ወደ ዋናው ሃሳቤ ልመለስና በአማርኛችን ብንተረጉመው ምን እንደሚባል እንጃ ግን “ራስ በራስ” እንበለው? ለአማርኛ ቋንቋ ተርጓሚዎች ብተወው እመርጣለሁ። ይሄ ቃል ጎላ ባለመለኩ የሰማሁት በ2013 የደቡብ አፍሪቃው መሪ ማንዴላ የቀብር ስነስርዓት ላይ ታድመው ከነበሩ የሃገር መሪዎች መካከል የአሜሪካኑ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ እንዲሁም የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሮን እና የዴንማርኳ ጠቅላይ ሚንስትር ሄሌ ቶርኒንግ የዓለማችንን ሚድያ ትኩረት ስበው በነበረበት ወቅት ነው። እነዚህ የሦስት አገራት መሪዎች ሰልፊ ፎቶ ሲነሱ በመታየታቸው ምክንያት ማለት ነው።

ሰልፊ አሁን በመዝገበ ቃላት ወጣ እንጂ አዳሜ እና ሔዋኔ ቀድሞውኑ ሰልፊ (ራስ በራስ) ናቸው። በተለይ የአሁኑ ባሕል ይሄን የሰው ልጅ ማንነት እያጎላው መጥቷል ራስን ከፍ ማድረግ ማስቀደም በአገራችንስ ብዙ ብሂሎች አሉ አይደል “ከራስ በላይ ንፋስ” ፡“ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል”። አሁን አሁን የማሕበረ ሰብ መገናኛዎች (social network) መበራከታቸው ማንነታችንን እየገለጡት ነው ብዬ ብል ማጋነን አይሆንብኝም “በፊት ገጽ” (Facebook) ገጾቻችን ላይ የምንመለከታቸው የምንታዘባቸው ነገሮች አሉ።

ሰልፊ ከፌስቡክ ወደ ቤተ እምነት

በፌስ ቡክ ብቻ ሳይሆን ሰልፊ በመድረኮችም መታየት ከጀመረ ሰንበትበት ብሎአል፡ በፊት በፊት በተለይ ሃይማኖታዊ በሆኑ ቦታዎች (መድረኮች) ይታዩ የነበሩት የመላክት ምስሎች ወይም የቅዱሳን ሰማእታን ወይም የቅድስት ድንግል ማርያም ተብለው የሚጠሩ ምስሎችን ነበር፡ (በኦርቶዶክስ) ማለቴ ነው። በፕሮቴስታንቱ ደግሞ በመድረኮቻችን ጎልተው የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ቢበዛ ቢበዛ መስቀል ይታይ ነበር አሁን ግን ነገሩ እንደዚህ አይደለም የሰባክያኑ ምስል በትልቁ ተለጥፎ እናያለን በአንዳንድ የቤተ እምነት መድረኮች ብቻ ስይሆን በጎዳናዎች ላይ ባሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ በትልልቁ የተለያየ ስያሜ የተሰጣቸው ሰዎች ይታያሉ “ሰልፊ” ይሏል ይሄ ነው።
ከአንድ ወዳጄጋ ሰለ ተለያዩ ጉዳዮች አንስተን ስንወያይ በአጋጣሚ በኢትዮጵያ በአንድ ፕሮግራም ዝግጅት ላይ የሆነውን በማዘን አጫወተኝ፡ ነገሩ እንዲህ ነው ለፕሮግራሙ ዝግጅት የተሠራውን ፖስተር (Poster) ተጋባዥ የሆኑቱ (አገልጋዮች) አስቀድመው እንዲያዩት በተደረገበት ጊዜ (ለፕሮግራሙ የተጋበዙ በርከት ያሉ ዘማሪያን ሰባኪያን ስለነበሩ)፡ ከእነዚህ ተጋባዦች (ሰባክያን) አንዱ ይሄ በፍጹም አይሆንም በማለት ቅሬታውን ለአዘጋጆቹ ገለጠ ነገሩ ግራ የገባቸው ወገኖች “ምን ተፈጠረ?” ብለው ሲጠይቁት ይሄ ወንድም “እንዴት አድርጋችሁ ነው የኔን ፎቶ ከሌሎች እኩል አሳንሳችሁ በማስታወቂያው ላይ የምትሰሩት? ይኔን ፎቶ ጎላ አድርጋችሁ ነው ማሰራት ያለባችሁ።” የሚል ትእዛዝ በመስጠት የፕሮግራሙ ጋባዦች እንደገና ፖስተሩን  የአገልጋዩን ፎቶ ጎላ በማድረግ በድጋሚ ለማሰራት እንደተገደዱ ሰማሁ።
መቼም ከጀመርኩት አይቀር አንድ ካነበብኩት ልጨምር ያነበብኩት ከፌስብክ ሲሆን የገጹ ግድግዳ ባለቤት (ጸሃፊ) “www.facebook.com/pages/ምስባከ-ጳውሎስ-Pauls-Pulpit” መሆኑን በቅድሚያ በማሳውቅ ጽሁፉ እንዲህ ይላል…
ወጣቶቹ መኪና ላይ ትልቅ ስፒከር ጭነው በማስታወቂያ ከተማውን ቅወጣ ተያይዘዋል፡፡ እየደጋገሙ ሕዝቡን ሲያደነቁሩበት የነበረው ማስታወቂያ “ሐዋርያው ዳንኤል ከለንደን ተመልሷል” የሚል ነበር፤ ከዚያም ሰዎች እርሱ ወደሚተውንበት ቦታ እንዲመጡ ይጋብዛሉ፡፡ ማስታወቂያው ለብዙ ክርስቲያኖች አስደንጋጭ ነበር፤ ቁልቁለቱን እየወረድንበት ያለው ፍጥነት የማይታመን ነው፡፡ ይህን ማስታወቂያ ሲሰሙ ከነበሩ ወገኖች አንዷመብራት ወዳቆመው መኪና ጠጋ አለችና “የጌታን መመለስ እያወጃችሁ መሆኑ ነው?” ስትል ማስታወቂያ ነጋሪዎቹን ጠየቀቻቸው፣ ተገቢ ጥያቄ ነበር፡፡ እነርሱ ግን የአቶ ጌታቸውን ልጅ መመለስ ነበር ሲያውጁ የነበሩት፡፡ በዚህ ዘመን የጌታን ስም ከሚጠሩ ሰዎች የሚብሱ የወንጌል ጠላቶችን እናገኛለን ብዬ መቼም አላስብም፡፡ (ከምስባከ ጳውሎስ የተገኘ)

የእኛን ግዝፈት አልቀን ለማሳየት የሚደረገው ሙከራ! አንድ ሰባኪ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ “ፓስተርና ፖስተር መለየት አቅቶኛል” እውነቱን ነው። ለነገሩ በነጳውሎስ ዘመን የሆነ ታሪክ አለ በሐዋርያት ሥራ (14:8-18) በእነ ጳውሎስ እጅ የተደረገውን ተአምራት ሕዝቡ በተመለከተ ጊዜ “አማልክት በሰው ተመስለው ወደ እኛ ወርደዋል!” ብለው ሊሰዉላችው በፈለጉ ጊዜ ልብሳቸውን በመቅደድ እነሡ እንደማናቸውም ሰዎች መሆናቸውን በተደረገው ተአምር የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሆነው አምላክ ጣት እንጂ የነሱ ምንም ነገር እንደ ሌለበት አሳይተዋል እነጳውሎስ “ሰልፊ” የሚባለው ቃል በእነርሱ የመዝገበቃላት የሌለ አገልጋዮች ናቸው።

ለነገሩማ ጳውሎስ ስለ ስልፊ ሲያስረዳን እንዲህ አልነበር ያለን “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ከእንግዲህ እኔ አልኖርም…” ካለን በኋላ በዛው በገላትያ መጽሐፍ “ነገር ግን ዓለም ለእኔ ከተሰቀለበት እኔም ለዓለም ከተሰቀልኩበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት፡ ከእኔ የራቀ ይሁን።

ከተወሰኑ ወራት በፊት እጅግ አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተ በሩሲያ የተጀመረ ከዛም በሌሎች ብዙ ሃገራት ተቀባይነት ያገኘ አደገኛ፡ሰልፊ (Daredevil) ወይም “ተዳፋሪ ሰልፊ” በጣም  እጅግ ከፍ ያሉ አደገኛም የሆኑ ሕንጻዎች ጫፍ ላይ በመውጣት ራሳቸውን ሰልፊ በማንሳት ትኩረትን እይታ እንዲያገኙ የሚሹ ወጣቶች በሶሻል ሚዲያ ላይ ፎቶአቸውን በመለጠፍ ለሕዝብ እይታ፡በዜና ማሰራጫ ጣቢያዎች ተስተውለዋል። እነዚህ ወጣቶች ትኩረት እንዲሰጣቸው የሚያደርጋቸው ከበስተጀርባ ያለው ነገር ነው። የቆሙበት ወይም የተንጠለጠሉበት። ሰልፊና እራስን ከፍ ማድረግ ጎላ አድርጎ ማሳየት አይመሳሰሉባችሁም? እኔ በጣም ይመሳሰሉብኛል፡:

እኛን ራሳችንን አጉልተን እና አግዝፈን ለማሳየት የምናደርጋቸው ጥረቶች አሉ በአለባበስ፣ በአነጋገር፣ በምንነዳው መኪና በቤታችን በንብረታቸን ወይም በተለያዩ መንገዶች። እንግዲህ ከግል ማንነታችን ጀምሮ እስከ አገልግሎታችን ልናየው ይገባል። አንዳንድ አገልጋዮች ክርስቶስ ኢየሱስን አስታከው ራሳቸውን ጎላ አድርገው ሊያሳዩን ይሞክራሉ (ይሰብኩናል) ወይም በእነሱ የተደረገውን ገድል ይዘክሩልናል፡ መቼም ጌታ የሠራውን ብንናገር በራሱ ክፋት ባይኖረውም በውስጠ ታዋቂነት ሰልፊ ኖሮት ሲነገር ግን ደስ አይልም (በዘመነኛው ቋንቋ አይመችም!) መቀባታቸውን ከእነርሱ በቀር ሌላ ቢጸልይ እግዜር የማይሰማ እንደሆነ ከዚህ የተነሳ ሰው እነሱን ተሳልሞ በእነሱ ደጅ ካላለፈ አይደለም የእግዚአብሔርን ፊት በጓሮው እንኳ እንዳልደረስን አድርገው ሊያሳዩን የሚሞክሩ ተበራክተዋል።  ግን መጽሐፉ የሚለው “ስለዚህ እናንተም የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ ከቁጥር የማንገባ አገልጋዮች ነን ልናደርገው የሚገባንን ተግባር ፈጽመናል በሉ።” (ሉቃ 17:10)

“ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል ራሱን የሚያዋርድ ግን ይከብራል፡” (ማቴ 23:12)
እግዚአብሔር በየትኛውም ነገራችን ለክብሩ እንድንኖር ይፈልጋል እኛ እንድንታይ ሳይሆን በእርሱ ሆነን እሱ በእኛ እንዲታይ ይሻል፡ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ተናገረው “”ከእኔ ይልቃል” (ዮሐ 1:15) ካለ በሁዋላ “እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባል።” (ዮሐ 3፡30) ዮሐንስ ጎልቶ ሊታይ የሚገባውን  እንዲጎላ የምድረበዳ ድምጽ ብቻ እንደሆነ ተናግሮ ወደ ክርስቶስ አመልክቶ አለፈ።

ወገኖች እኛ (ሰልፊያችን) ምን ይመስላል?

The post ሰልፊ (እኔው፣ ከኔው፣ ለኔው፣ በኔው) first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ደቀ መዝሙር https://deqemezmur.com/2022/09/29/discipleship/ Thu, 29 Sep 2022 23:12:38 +0000 https://deqemezmur.com/?p=2043 “ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።” ሉቃ 14፡27 ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የተናገረው ቃል ነው። ይህ ቃል ዛሬም ሊከተሉት ለሚወዱት ሁሉ ተገቢውን ጥያቄ ያነሳል፡ ራስን በመካድ ለእርሱና ለሱ ብቻ ለመኖር ውሳኔን አድርገን እንከተለው ዘንድ ይህ ጥሪ ለእያንዳንዳችን ደርሶናል ምላሻችን ግን ምንድን ነው? በተለይ ባለንበት ዘመን በየቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ በየኮንፈረንሱ የምንሰማቸው ስብከቶች […]

The post ደቀ መዝሙር first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>

“ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።” ሉቃ 14፡27

ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የተናገረው ቃል ነው። ይህ ቃል ዛሬም ሊከተሉት ለሚወዱት ሁሉ ተገቢውን ጥያቄ ያነሳል፡ ራስን በመካድ ለእርሱና ለሱ ብቻ ለመኖር ውሳኔን አድርገን እንከተለው ዘንድ ይህ ጥሪ ለእያንዳንዳችን ደርሶናል ምላሻችን ግን ምንድን ነው? በተለይ ባለንበት ዘመን በየቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ በየኮንፈረንሱ የምንሰማቸው ስብከቶች (ትምህርቶች) ምን ላይ ያተኮሩ ናቸው ብላችሁ አስባችሁ ታውቁ ይሆን? ከርዕሶቻቸው እንኳ ብንነሳ “የጥርመሳ ዘመን” “የቅባት ዘመን” “የከፍታ ዘመን” ወዘተ… እያለ ይቀጥላል። ይሄ ማለት ግን ጥቂቶች የሚሆኑ የክርስትና አንኳር ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ የሉም ማለት አይደለም። ነገር ግን አብዛኛው ያደላው የኛ የአማኞች ሕይወት ለምድር የተፈጠረ ብቻ ያህል አድርገን እንድናስብ የሚያደርጉን መብዛታቸው እጅግ ያሳዝናል። ክርስትና ዋጋ ያስከፍላል !! የሚለው የኢየሱስ አስተምህሮ ከብዙዎች አንደበት የራቀ ይመስላል ወጣት የሆነውን ትውልዳችንን እንዲለማመድ እየተደረገ ያለው ነገር ከቀደሙ አባቶች ሕይወት ጋር ሲነጻጸር እጅጉን የራቀ ነው። ይሄ ጉዳይ ሊያሳስበን ይገባል ልል ነው ብቅ ያልኩት። እንደው የአቅም ለማበርከት መቼም ያለንበት ዘመን የሶሻል ሚዲያ መነጋገሪያ የሆነበት ዘመን ላይ ነው፡ ይሄንኑ ቴክኒዮሎጂ በመጠቀም ድምጼን ላሰማ ብዬ ነው። ጠንካራ ደቀ መዝሙርነት ያስፈልገናል አንድ ሰው እንዳለው ነው “ቤተ ክርስቲያንን ደቀ መዛሙርት ያልሆኑ ደቀ መዝሙሮች ሞልተዋታል” አለ።  

እንግዲህ ደቀ መዝሙርነት ዋናው እና ወሳኙ የክርስቲያን መለያው ነው። መስቀሉ ማንነታችን ነው። የሞቅታና የይሆንልሃል አስተምሕሮዎች የትም እያደረሱን አይደለም ያሉት። እውቁ ጀርመናዊው መጋቢ እና የነገረ መለኮት መምህር ዲትሪክ ቦንሆፈር “ብዙ ሰዎች በትክክለኛ ፍላጎት የምንናገረውን ለመስማት ወደ ማምለኪያ ስፍራችን ይመጣሉ ነገር ግን በብዛት ጥሩ ያልሆነ ስሜት እየተሰማቸው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ ምክንያቱም ወደ ኢየሱስ እንዳይመጡ በጣም ውስብስብ (አስቸጋሪ) ስለምናደርግባቸው ነው።” ብሎ ተናገረ የጌታ ኢየሱስ መልዕክት በጣም ግልጽ ነበር ሰዎች እንዲወስኑ ጥያቄ የሚፈጥር ሊከተሉት አለዛ ላይከተሉት ደቀ መዝሙራዊ ጥሪ ያቀርብላቸው ነበር። “ኢየሱስም፦ ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው።” ማቴ 8:20 ይሄ እንግዲህ የኢየሱስ ጥሪ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው በዚህ በማቴዎ 8 ላይ ባለው ታሪክ የምናየው ለዚህ የአይሁድ መምህር “ወደ ምትሄድበት እሄዳለሁ” ብሎ ማለቱ በጣም ቀላል ነበረ ነገር ግን ወደ ዋናው ውሳኔ እንዲመጣ ሲጋበዝ ያን ጊዜ ነው እውነተኛ ውሳኔ መወሰኑም አለመወሰኑም የሚታየው ኢየሱስ አይደለም ልከተልህ የሚሉትን ይቅርና አብረውት ያሉትን “ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ። እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ።” ዮሐ 6፡67  እንደው ዛሬ ጌታ እኛን ተመሳሳይ ጥያቄ ቢያቀርብልንስ? ለምን እንደተከተልነው ገብቶን ይሆን? እንደ ፈሪሳዊው አብሬህ እሄዳለሁ ማለቱ ላይከብድ ይችላል መወሰኑ ግን በጣም ወሳኝ ነው አብሬው ነኝ፡ ብለን ልናስብ ይሆን ይሆናል ነገር ግን እንደ ደቀ መዛሙርቱ  ሌሎች አማራጭ የሚመስሉ ነገሮች ጋር ስንደርስስ? እንደ ጴጥሮስ “ከአንተ ወዴት እንሄዳልን?”  ለማለት የሚያስችል የሕይወት ውሳኔን አድርገን ይሆን? ራሳችንን ክደን  መስቀሉን ተሸክመን መከተል አማራጭ የሌለው ጥሪ ነው። በይሆንልኛል የሂሳብ ስሌት ሰርተን ሳይሆን “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።” ማቴ 10፡25 የሚለውን ሂሳብ ሰርተን መከተል ነው። እንግዲህ ጎበዝ ወገባችንን ጠብቅ ትንፋሻችንን ሰብሰብ አድርገን የጀመርነውን ጉዞ በሚገባ ለመቀጠል እንበርታ ተስፋችን እኛ ከምናስበው ይበልጣል ጥሪያችን ክቡር ነው፡ መድረሻችን ከፍያለ ነው፡ ሰለዚህ እንበርታ።  ደቀ መዛሙርት በመሆን ሌሎችንም ደቀ መዛሙርት እናድርግ፤

The post ደቀ መዝሙር first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>
ማምለክ ወይንስ ማድመቅ? https://deqemezmur.com/2022/05/13/%e1%88%9b%e1%88%9d%e1%88%88%e1%8a%ad-%e1%8b%88%e1%8b%ad%e1%8a%95%e1%88%b5-%e1%88%9b%e1%8b%b5%e1%88%98%e1%89%85/ Fri, 13 May 2022 23:49:08 +0000 http://deqemezmur.com/?p=1044     መቼም መዘመር መልካም ነው ለጌታ የሚገባውን ማቅረብ ይገባናል መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው። ግን ግን አንዳንዴ ጥያቄ እንድጠይቅ የሚያደርጉኝ፡ ነገሮች አሉ እንደው እንዳላየ ሆኜ ለማለፍ ካልፈለኩ በቀር፡ አምልኮ ጭፈራችን ነው ወይንስ ሕይወታችን? አካሄዳችን ወዴት ነው? ምን እያደረግን ነው? በእኛና በዚያኛው (በዓለማዊው) ሰፈር ያለው ልዩነት ምን መሆን አለበት? የመገናኛ ብዙኃን (Social network) በሰፊው ግልጋሎት ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮ […]

The post ማምለክ ወይንስ ማድመቅ? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>

 

 

መቼም መዘመር መልካም ነው ለጌታ የሚገባውን ማቅረብ ይገባናል መጽሐፍ ቅዱሳዊም ነው። ግን ግን አንዳንዴ ጥያቄ እንድጠይቅ የሚያደርጉኝ፡ ነገሮች አሉ እንደው እንዳላየ ሆኜ ለማለፍ ካልፈለኩ በቀር፡ አምልኮ ጭፈራችን ነው ወይንስ ሕይወታችን? አካሄዳችን ወዴት ነው? ምን እያደረግን ነው? በእኛና በዚያኛው (በዓለማዊው) ሰፈር ያለው ልዩነት ምን መሆን አለበት?

የመገናኛ ብዙኃን (Social network) በሰፊው ግልጋሎት ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮ እየጨመረ እያደጉ ያሉ ብዙ ጠቃሚ አስተማሪና ግንዛቤ ሰጪ ነገሮች ማግኘት ችለናል። ይሄ እውነት ሆኖ እያለ ግን በዛው መጠን የሚጎዱ ነገሮችም የሞሉበት ሁኔታ አለ። በዚህ ሃሳብ እያለን የምንገለገልበት የዩቱብም ሆነ የፌስ ቡክ ገጾች የሚያስተላልፉት መልእክት ለአድማጫቸው የሚደርሱት የታሰበውንም ሆነ ይልተጠበቀ ውጤት የሚያመጡ ናቸው። 

   እንደ ክርስቲያንነቴ (ወንጌላዊ አማኝ) እንደመሆኔ በወንጌላዊ አማኞች መካከል “አምልኮ” እየተባለ የሚሆነው ነገር እጅጉን እያሳሰበኝ፡ ከመጣ ሰንብቷል። አምልኮ የሚለው ሃሳብ ከስሜት ያልተለየ የሆነ ይመስላል  (ምንም እንኳ አምልኮ ያለ ስሜት ባይሆንም)። ጭፈራ እና ማምለክ ልዩነቱ ብዙ በማይታይበት አንዳንዴ እግዚአብሔርን ለማክበር የተሰበሰበ ጉባኤ ሳይሆን ጥሩ የሆነ ዳንኪራ የሚረገጥበት ቤት እስኪመስል ዘማሪው (አስመላኪው) አምላኪው የሚሆኑትንም የሚያደርጉትንም ለማን? እና ለምን? እንደሚያደርጉት በማይለዩበት መልኩ ሲዘሉ እናያለን። ይሄንን የታዘቡ ብዙዎች አሉ ብዬ እላለሁ ከአንዳንድ አስተያየቶችም እንደሚነበበው ወንጌላውያን አማኞችም ሆኑ ወንጌላውያን አማኝ ያልሆንኑት የሚሉት በርካታ ነገሮች አሉ። የአንዳንዶች ሁኔታ በሚታዩ የተለያዩ “የአምልኮ” ተብለው የተሰየሙ የቪድዮ ክሊፕ ግር ያሰኛል፡ መዘምር አይሉት መዝፈን ውዝዋዜ አይሉት አክብሮት ያሰቅቃል፡ ያሳፍራል፡ በተለይ አንባቢዎቼ እንዲረዱልኝ፡የምፈልገው የሃይማኖተኝነት ወግ ይዞኝ፡አይደለም ነገሩ አሳስቦኝ፡ነው። ወዴት እየሄድን ነው?  

 “የማታመልክ ቤተ ክርስቲያን በመዝናኛ መያዝ አለባት። ቤተ ክርስቲያንን ወደ አምልኮ የማይመሩ መሪዎች መዝናኛን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።” ኤ ደብሊው ቶዘር A. W. Tozer

ተመልካች አለን ተመልካቾቻችን አይምሮ ያላቸው ማገናዘብ የሚችሉ ናቸው። ክርስትናችን በውስጥ (አማኞች)፡ በውጭ ደግሞ የማያምኑት የሚያዩት ነገር ያለበት ሕይወት ነው። ለዚህም ነው ኢየሱስ “እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።” (ማቴ 5:16)   “ብዙ ፍሬ በማፍራት ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብትገልጡ በዚህ አባቴ ይከብራል።” ዮሐ 15:8 ብሎ የተናገረው።

       በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ የምናደርገውንም ሆነ የምንኖረውን ኑሮ “ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” (1 ቆሮ 10:31) እንደሚል ምንም እንኩዋን ነጻነት ያለን ሰዎች ብንሆንም ነጻነታችን ግን ልቅነት እንዳልሆነ ልናስተውል ይገባል “ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር አይጠቅምም…” (1 ቆሮ 6:12) በጸጋው የምንኖር ሰዎች መሆናችን ባይዘነጋም ጸጋው ግን ልቅም አይደለም ሕግም አይደለም የራሱ መጠን አለው በአንዱ ጫፍ የምናጠብቀ ወይም በሌላኛው ጫፍ የምናላላው እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባል ባይነኝ። 

             በዘመናችን ያሉ እውቅና ያገኙ የአሕዛብ ልማድ፡ ባሕሎች ቤተ ክርስቲያንን ዘልቀው እየገቡ ይገኛሉ (Pop-culture) እንለያቸው (Distinguish) እንለያያቸው (Separate) የእግዚአብሔርን እውነት ዓለማዊ ቀሚስ አልብሰን በማቅረብ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ መሞከር ካህን የነበረው አሮን ሕዝቡ ባቀረበለት ጥያቄ መሰረት እንዲመለክ የሰራውን ጥጃ እንደማቅረብ ይታያል ብዬ እፈራለሁ፡ (ዘፀ 32:5-6) ከግብጽ የወጣው የእስራኤል ሕዝብ በለመደው መልኩ (በምርኮ ምድር እንደተለማመደው) በልቡ የነበረውን አምላክ ብሎ ለሚለው ሲሰዋ የምናይበት ታሪክ ነው የዚህ ታሪክ ፍጻሜ እጅግ አሳዛኝ፡ እንደነበረ ከታሪኩ ማስተዋል እንችላለን።

 ስሜታዊነት (ሁሉንም ባይሆን) ነገር ግን ጎልቶ በሚታይ መልኩ ወጣቶቻችንን የተጠናወተ ይመስላል (እድሜዬ በወጣቱ ክልል እንዳለ ይታወቅልኝ) በእግዚአብሔር ማንነት ያልተ ገራ ያልተያዘ አይምሮ እና ማንነት ለአጓጉል ስሜታዊነት ያጋልጠናል አጓጉል ስሜታዊነት ወደ አጓጉል ስህተተኛነት ይወስደናል፡ በእኛና በዚያኛው ሰፈር (ዓለማዊነት) መካከል መስመር አለ ይሄ መስመር ደምቆ መሰመር አለበት ባይ ነኝ፡ ዳዊት እርቃኑን በእግዚአብሔር ፊት ዘምሮአልና እኛን ማን ይከለክለናል? ባይ እንደማይጠፋ እርግጠኛ ነኝ። ዳዊት እርቃኑን መዘመሩ ሳይሆን ልቡም የሚያመልክ የነበረ ሰው መሆኑ ከውድቀቱም እንኳ የምንማራቸው ነገሮች አሉ (መዝ 51) ሕይወት አምልኮ ነው! እንጂ ዝማሬ ወይም ኅይማኖታዊ ተግባራቶቻችን በራሳቸው ሙሉ አምልኮ መሆን አይችሉም።  

ይህንን ሁሉ ማለትህ ጥሩ ነው ታዲያ ምን ይሁን ሒስ ብቻ ነው? ወይንስ መፍትሄ አለህ ወይ? ለሚሉ ይሄንን ለመሰንዘር እሞክራለሁ።

አምልኮ እና መዝናኛን (Entertainment) መለየት

“የማታመልክ ቤተ ክርስቲያን በመዝናኛ መያዝ አለባት። ቤተ ክርስቲያንን ወደ አምልኮ የማይመሩ መሪዎች መዝናኛን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።” ኤ ደብሊው ቶዘር A. W. Tozer

      አምልኮ የሆነ ተግባር አይደለም ነገር ግን ማንነት እንጂ።

       ባለንበት ዘመን አምልኮአችንን ይዘቱን ልንፈትሽ ከዛም ባለፈ መልኩ ትኩረትልንሰጠው ይገባል እላለሁ ምክንያቱም ትኩረት ካልሰጠነው በቆይታ መጽሐፍቅዱሳዊ መልኩን ይለቅብናልና ነው። አሁንም ቢሆን ያለው ልምምድ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አምልኮ ያማከለ ለመሆኑ ምን ያህሎቻችን እርግጠኞች ነን? በመድረኮቻችን የሚንጸባረቁት የተዋናይና የታዳሚ አይነት ይዘት ያላቸው ልምዶች መታየት ከጀመሩ ሰንበት ያሉ ይመስለኛል። የመድረክ አገልጋዮች ሃላፊነትን ከተቀበሉት አደራ አንጻር ምን እያደረጉ እንደሆነ ተረድተው የሚተገብሩት ጥቂቶች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ጉባኤውን ሞቅ አድርገን መያዝ ነው ለአብዛኞቻችን የሚታየን በጉባኤው ላይ ሙሉ አክብሮትና ሙሉ መገዛት የሚገባውን ጌታ ወደ ጎን አድርገን በሱ ስም እኛው መሟሟቁላይ ነው ትኩረታችን፡፡ ከማልረሳቸው ትዝታዎች መካከል በቤተ ክርስትያን እኔና ሌሎች ወገኖች በምናገለገልበት ፕሮግራም የመምራት ተራው የነበረ አንድ ወንድም ለአገልግሎት ልምምድ ላይ በነበርንበት ሰአት የያዛቸው የአዝማቾች መብዛት ከዛም አልፎ አዝማቾቹ አንድ አይነት የሙዚቃ ቁልፍ እና ሪትም አላቸው እንጂ ያላቸው የመልእክት ይዘት የተለያየ ነበርና አንዲት እህት ምነው? ብትለው የሰጣት መልስ “አየሽ ጉባኤውን ለማግኘት እንዲህ ነው ማድረግ ያለብን። በዚህ ዝማሬ አዝማች እህት እከሊትን በዚህ ዝማሬ አዝማች ደግሞ ወንድም እከሌን በዚህኛው ደግሞ እማማ እክሌን በዚያኛው ደግሞ አባባ እከሌንና ጋሽ እከሌን አገኛቸዋለሁ።” ብሎ እርፍ።

     እንግዲህ እዚህ ላይ ነው የአምልኮአችን ይዘት መዝናኛ ነው? ወይንስ እግዚአብሔርን ማክበሪያ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያለብን።

           በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ በሆነ መልኩ በአንዳንድ የሕይወት ክልላችን ላይ  በዚህ መልኩ ቢሆን ወይንም በዚያ መልኩ የሚል ቀጥተኛ ትእዛዝ ባይሰጠንም: እንደሚባለው አንዳንድ ግራጫማ የሆኑ ክልሎች አሉ፡ እንዴት እናስተናግዳቸው? ምንድን ነው መመዘኛቸው? 

         ነገር ግን በጉባኤም ሆነ በግል አምልኮአችን ልንከተለው የሚገባ መርህ ይሰጠናል፡ ጳውሎስ ይሄንን በፊሊጵስዩስ መልእክቱ “በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ እውነት የሆነውን ሁሉ ክቡር የሆነውን ሁሉ ትክክል የሆነውን ሁሉ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ መልካም የሆነውን ሁሉ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደነዚህ ስላሉ ነገሮች አስቡ።” (ፊሊ 4:8) ይለናል።

  • የነገር መመዘኛችን “እውነት የሆነው ነው “እውነት ለሁሉም አይመችም ብዙዎች አይስማሙበትም ከብዙሃኑጋ ሳይሆን ከማይለወጠው እውነት እሱም ከቃሉ ጋር። ኢየሱስ በዮሐንስ ወንጌል (7:18) እውነተኛነት የሚለካው ስለ እኛ ወይም ስለምን ቀበልው ክብርና ማንነት ሳይሆን የተላክንበትን በመፈጸም የላኪውን ሥራ ስንሠራ እንደሆነ ይናገራል፡ እውነት በእኛና በምናመልከው አምላክ (ዮሐ 8:34)፣ በምንኖርበት ዓለም (ኤፌ 5:9) ፣ ጠላትን በምንዋጋበት ጊዜ (ኤፌ 6:14) በዚህ ሁሉ ወሳኝ፡ነው ስለዚህ የነገር መለኪያው እውነት እንደ ቃሉ እንጂ እነደ ሁኔታዎች እንደ ብዙኃኑ መሆን የለበትም። “ቃልህ እውነት ነው በእውነትህ ቀድሳቸው፡” (ዮሐ 17:17) ይሄ እውነት የሚያደርገን ለእግዚአብሔር እንድንለይ የእርሱ እንድን ሆን ያደርገናል፤ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህር በዚህ ክፍል የተናገርው ነገር አለ እሱም ሰዎች ባለንበት ዘመን “እውነት ይሆን?” ብለው አይጠይቁም ነገር ግን “ይሰራልኛል ወይ?” እና “ምን ስሜት ይፈጥርልኛል?” የሚለው ነው። ነገር ግን ስሜታችን የሚመቸውን ሳይሆን በእውነተኛ ቃሉ አማካኝነት ልናስተናግደው የሚገባ መሆን አለበት ወይም ልምምዳችን በቃሉ መፈተሽ አለበት እንጂ በሌላ አባባል ልምምዳችን ቃሉን አያረጋግጥልንም ቃሉ ግን ልምምዳችንን ያረጋግጥልናል።
  •  የነገሮች መመዘኛ ክቡር የሆነውን” በሌላ አባባል ሊከበር የሚገባው ልከነቱ ርካሽ ያልሆነ ክቡር ባልሆነ ነገር ላይ አይምሮአችንን አናስይዝም ምድራዊ የሚያልፍ በእግዚአብሔር ፊት ስፍራ የሌለው ማንኛውም ነገር “ዜግነታችን ሰማያዊ ስለሆነ” (ፊሊ 3:20) ሃሳባችንም በሰማያዊው መመዘኛ የተለካ መሆን አለበት፡ ዘላቂነት የሌለው ቢሆን እንኳ ራሳችንን መጠየቅ ያለብን “ለጥቂት ይጠቅማልና፡” (1 ጢሞ 4:8) ጳውሎስ እንዳለውና በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለው ወይ? ለዘላለማዊው መንደርደሪያ ይሆናል ወይ?  ዘላለማዊውን ታሳቢ ያደረገ ዋጋ አለው ወይ? ምንም አይደለም ተብሎ የሚታለፍ ጥቂት የሚል ነገር በክርስትና ስለሌለ የተከበረ ነገር ማለት የተከበረ ነው። ምን አደረግን? ሳይሆን ለምንድን ነው የምናደርገው? ለስሜታችን ሳይሆን ለመንፈሳችን ለተቀበልነው ላመንነው እውነት የተከበረ መሆኑ የምናሳይበት ነው መሆን ያለበት። ክቡር የምንለው “ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ” (ፊሊ 2:4) ራሳችንን ያማከለ መሆን የለበትም።
  • የነገሮች መመዘኛ “ትክክል የሆነውን ሁሉ”  የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ”ትክክል” የሚለው ቃል “ጽድቅ” ከሚለውጋ እንደሚዛመድ ያስረዳሉ። ትክክልን ማየት ያለብን በእግዚአብሔር የቅድስና መስፈርት የሚመጥን ሲሆን ትክክል እንለዋለን። “ትክክለኛውንና ቀና የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰዎቹን እንዲያዝ መርጨዋለሁ፡” (ዘፍ 18:19) በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ  የሆነ ፍትህ ያልተጓደለበት (መዝ 82:2) በእግዚአብሔር ፊት ሚዛኑ ያልተጭበርበረ መለኪያው ትክክል የሆነ (ምሳ 11:1 ፣ 16:11) ይህ ትክክለኛነት በእግዚአብሔር በእርሱ የሚመራ ነው፡ (ኢሳ 26:7) ፈሪሳውያን ራሳቸውን ትክክል እንደ ነበሩ ይቆጥሩ ነበር ነገር ግን በመለኪያው ሲታይ አልነበሩም (ሉቃ 18:9-14) ልንኖረው ልንከተለው የሚገባን የትክክል መስፈርቱ እኛ አይደለንም በአጠቃላይ መብታችንን የምናስከብርበትን ሳይሆን ለትክክለኛው ነገር መብታችንን የምንተውበትነ ነው የሚናገረው (ሮሜ 14:13-17)።
  • የነገሮች መለኪያ “ንጹሕ የሆነውን ሁሉ” ሞራላዊ ንጽሕና ምንም አይነት ክፋት (ነውር) የሌለበት ሰውነታችንን የማያረክስ በውስጥ ማንነታችንም በውጭውም እንደ ጢሞቴዎስ ለሚያዩን “በእምነትና በንጽሕና አርኣያ ሁንላቸው።” (1 ጢሞ 4:142) ደግሞም ያዕቆብ “በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕና ነውር የሌለበት” (1:27) እንደሚናገር በኤፌሶን 5:3 “በመካከላችሁ ከቶ አይነሳ” ብሎ እንደሚላቸው ይሄ ንጽሕና በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው በተለይ (በፊሊ 1:17) ክርስቶስን ሲሰብኩ በንጽሕና እንዳልነበር እንደሚናገር የራስን ጥቅም ወይም ስውር ሃሳብ ያላነገበ ሆኖ የሚገኝ የእኔነት እርሾ የሌለበት (ማቴ 6:1-2 ፣ 1ቆሮ 5:6 ፣ገላ 5:9)
  • የነገሮች መለኪያ “ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ” እንደ አማኝነታችን ተቀባይነት ያለውን ከውስጥ፡ መነሻ ሃሳቡም ሆነ ለሌሎች ስናደርገው አስደሳች ሆኖ ሲገኝ፡ (በ 1ቆሮ 13፡ 4-7) ባለው መርህ ላይ የተመሰረተ ከላይ ካነሳነው እውነት ጋር የሚሄድ። ይህ ተወዳጅ የምንለው ርህራሄ ያለው ለሌሎች አሳቢ የሆነ፡ ይሄ ተወዳጅ የሆነው ጽድቅ የሞላበትን ሰላም ያመጣል ወይ?
  • የነገሮች መለኪያ “መልካም የሆነውን ሁሉ” ይሄን አይነቱ መልካምነተ በሌሎች ዘንድ እግዚአብሔርን ባስቀደመ መልኩ በእኛ ሲገለጥ፡የሚከበር ስፍራ የሚሰጠው፡ ነው። ሲደመጥም የሚወደድ በጨው እንደ ተቀመመ እንደሚል፡

“በጎነት ቢሆን ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉ ነገሮች አስቡ”። እንግዲህ በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር ክብር ሊሆን የሚገባው “እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን  ሁሉ አስቡ።” ብሎ ስለሚል ለየትኛውም ነገር መነሻ መስፈርት ይሆነናል በመንፈሳዊው ይሁን ምድራዊው፤ ምንም እንኳ “በእናንተም ሆነ በሰዎች የፍርድ ሸንጎ ቢፈረድብኝ፡ እኔ በበኩሌ ግድ የለኝም…በእኔ ላይ የሚፈርድ ጌታ ነው።” (1ቆ 4:3, 4) ብሎ ጳውሎስ ቢናገርም በሌላ ቦታ ግን በተቀበለው ሃላፊነት አንጻር “በዚህ በምናከናውነው የቸርነት ሥራ አንዳች ነቀፋ እንዳይገኝብን እንጠነቀቃለን። ምክንያቱም ዓላማችን በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን በሰውም ፊት መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ነው።” (2ቆሮ 8:20-21)  

ፍርድ አይደለም ተጠያቂነትና ኅላፊነት ነው!

እንደ ክርስቲያን ነገሮች እየተጠቀምንባቸው ነው? ወይንስ ነገሮች እኛን እየተጠቀሙብን ነው? ለየትኛውም እርምጃችን ምላሽ እንሰጥበታለንመልካምም ሆነ ክፉ፡ የትኛውም እርምጃችን በልባችን ካለ እውነተኛ ንጽህና የመነጨመሆን አለበት ራስወዳድነት የሌለበት (እኔን ይመቸኝ፡እንጂ ስጋ መብላቴ ማንም አያገባውም) በሚልመንፈስ ሳይሆን ለወንድማችን መልካምነት እና ለእግዚአብሔር ክብር መዋል አለበት።

“ታዲያ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? ለምንስ ወንድምህን ትንቃለህ? ሁላችንም በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት እንቀርባለንና… ስለዚ እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ፊትመልስ እንሰጣለን።” (ሮሜ 14:10ና 12)    

The post ማምለክ ወይንስ ማድመቅ? first appeared on ደቀ መዝሙር.

]]>